የፓርላማ አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ እየጠበቁ ነው

የፓርላማ አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ እየጠበቁ ነው

Last week we reported ANDM and OPDO members of parliament have decided to boycott parliament until the PM and military chief come and explain to them who gave them permission to deploy the army to regions. TPLF koas were trying to spin the issue saying parliament was still in session. Now 2nd week into the boycott they are forced to admit!!

ሰበር ዜና!
የኢሃዲግ ፓርላማ በይፋ ተከፋፈለ!
የኦህዴድና የብአዴን ፓርላማ ተቀማጮች ሃይለማሪያምን ሃገሪቱ የገባችበትን ትርምስ በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጥ አዘዙት!

የኦህዴድና ብአዴን የፓርላማ ተቀማጮች ከድርጅቶቻቸው ጋር ስብሰባ ተቀምጠው አቋም ይዘዋል። የለማና የነገዱ ቡድን የፓርቲወቻቸውን ሙሉ ድጋፍ እንዳገኙ ይህ ይፋ አድርጎታል።

ለጥያቄያቸው መልስ ሳያገኙ መደበኛ ስብሰባ አናደርግም ብለዋል! የፓርቲወቻቸው ትእዛዝ ወርዶላቸዋል።

ህወሃት እና ገሚሱ ደኢህዴግ በአንድ በኩል ብአዴንና ኦህዴድ በሌላ በኩል የሞት ሽረት እሽቅድምድም ገብተዋል። ብአዴንና ኦህዴድ የፓርላማ አብላጫ መቀመጫ ስላላቸው ወያኔ ትልቅ ስጋት ውስጥ ገብቷል።

ይህ ክንውን የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ፍጥጫ የተሞላበት ስብሰባ ጎን ለጎን እያደረገ በሚገኝበት ወቅት በመሆኑ ትርምሱን አባብሶታል!

የሪፖርተር ጋዜጣ ይህን ትርምስ ይፋ አድርጎታል። በኢህአዴግ ዘመን እንዲህ ያለ ክስተት ታይቶ አይታወቅም። አዲስ አበባ የለውጥ ማእበል እየናጣት ነው።
AsnakewAbebe

የፓርላማ አባላት

(ethiopianreporter) –የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አገሪቱን ሥጋት ላይ በጣላት ብሔር ተኮር ግጭትና የፖለቲካ ቀውስ ላይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ማብራሪያ እንዲሰጧቸው ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ፡፡

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የምክር ቤቱ አባላት ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ አግኝቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ እስኪገኙ ድረስ መደበኛ ስብሰባዎችን ማካሄድ ተገቢ አይደለም የሚል አቋም ይዘዋል፡፡

በርካታ መሆናቸው የተገለጸው የምክር ቤት አባላት ረቡዕ ታኅሳስ 4 ቀን 2010 ዓ.ም.፣ በየተወከሉባቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ውይይት ማካሄዳቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በዚህም ከኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል የኦሕዴድና የብአዴን አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ ተገኝተው ወቅታዊ ግጭቶችንና የፖለቲካ ቀውሱን አስመልክቶ እንዲያብራሩ፣ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎችም ዝርዝር ምላሽ እንዲሰጡ አቋም ይዘው ጥያቄ ማቅረባቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

አባላቱ ላቀረቡት ጥያቄ ከምክትል አፈ ጉባዔዋ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ ምላሽ እየተጠበቀ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት ሐሙስና ማክሰኞ ታህሳስ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. መካሄድ የነበረበት የፓርላማው መደበኛ ስብሰባ አለመካሄዱ ታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች በፕሮግራማቸው መሠረት ኃላፊነታቸውን በመወጣት ላይ መሆናቸውን ምንጮች አክለው ገልጸዋል፡፡

በምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት ሥነ ምግባር ደንብ መሠረት የምክር ቤቱ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩን በወር አንድ ጊዜ ጠርተው ትኩረት ባደረጉበት የሥራ አፈጻጸማቸው ላይ ማብራሪያ መጠየቅ እንደሚችሉ፣ እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓመት ሁለት ጊዜ ዝርዝር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለምክር ቤቱ እንዲያቀርቡ ግዴታ ይጥልባቸዋል፡፡

ከወር በፊት የምክር ቤቱ አባላት ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማው ተገኝተው በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተቀስቅሶ ስለነበረው ግጭትና የፖለቲካ ሁኔታ፣ እንዲሁም ከመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት ለመልቀቅ ጥያቄ ስላቀረቡ ከፍተኛ አመራሮች መነሻ ምክንያት ማብራሪያ መጠየቃቸውና ጠቅላይ ሚኒስትሩም ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ ጥያቄ የቀረበለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት፣ ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌለው ለሪፖርተር ገልጿል፡፡