የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እስክንድር ነጋና የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ሌሎች አመራሮች በሚመጣው ምርጫ ለፓርቲው በእጩነት ተመዝግበው መወዳደር እንደሚችሉ ውሳኔ ሰጥቷል።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እስክንድር ነጋና የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ሌሎች አመራሮች በሚመጣው ምርጫ ለፓርቲው በእጩነት ተመዝግበው መወዳደር እንደሚችሉ ውሳኔ ሰጥቷል።

… ዛሬ በሚጀመረው በርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ የመክፈቻ የጸሎት መርሀ ግብር ላይ ለመገኘት እና ከብፁዓን አባቶቻችን ቡራኬ ለመቀበል በዚያውም “ታፍኛለሁ በማለታቸው ብቻ ከቤተ ክህነቱም ከቤተ መንግሥቱም የተለየ ጫና እየተደረገባቸው የሚገኙትን ቅዱስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ” እኛ ልጆችዎ ከጎንዎ ነን” ለማለት ከመላ አዲስ አበባ ከአራቱም አቅጣጫዎች ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ባለማዕተቦቹ የተዋሕዶ ልጆች ከየአቅጣጫው እየተመሙ ነው።
በሁሉም አቅጣጫ ወደ ቅድስተ ማርያም የሚወስዱ መንገዶች በሁሉ በዚህ መልኩ ዝግ ሆነዋል። …
ከዘመዴ ቴሌግራም የተውስድ…

Birds of the same feathers flock together.
የጥፋት እና መከራ መካሪዎች


የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እስክንድር ነጋና የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ሌሎች አመራሮች በሚመጣው ምርጫ ለፓርቲው በእጩነት ተመዝግበው መወዳደር እንደሚችሉ ውሳኔ ሰጥቷል። ይህ ውሳኔ ሌሎች ፓርቲዎችም ጥያቄ እንዲያነሱ በር የሚከፍት ነው። እንደሚታወቀው ኦፌኮና ኦነግ ከምርጫው ራሳቸውን ያገለሉት በርካታ እጩዎቻቸው በመንግስት የፀጥታ ሃይል ታፍነው እስር ቤት በመወረወራቸውና እነዚህን እስረኞች በእጩነት ማቅረብ ባለመቻላቸው ነው።
ለምሳሌ ኦፌኮ ባወጣው መግለጫ ከላይኛው እስከ ታችኛው እርከን ድረስ ያሉ እጩ ሊሆኑ የሚችሉ አባሎቹ በመታሰራቸውና ምርጫውን ለማስተባበር ከተመረጡት አምስት ሰዎች ውስጥ አራቱ በመታሰራቸው ፓርቲው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከምርጫው ተገፍቶ መውጣቱን ተናግሯል። አራቱ አስተባባሪዎች ኦቦ በቀለ ገርባ ፣ ጃዋር መሃመድ ፣ ሃምዛ ቦረናና ደጀኔ ጣፋ ነበሩ።
 
በአጭሩ የእስር እርምጃውን በተመለከተ በባልደራስና በእነዚህ ፓርቲዎች መካከል የነበረው ልዩነት የ magnitude ነው። እነዚህ ፓርቲዎችም የታሰሩባቸው ሶስት ወይም አራት አመራሮች ብቻ ቢሆኑና በእጩዎቻቸው ላይ ሰፊ የእስር ዘመቻ ባይካሄድባቸው ኖሮ ከምርጫው ተገፍተው አይወጡም ነበር። በሌላ አነጋገር ባልደራስም ሶስት አመራሮች ብቻ ሳይሆን በርካታ እጩዎቹ ቢታሰሩበት ፓርቲው ከምርጫው ራሱን የማግለል እድሉ ሰፊ ይሆን ነበር።
የዛሬው የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ በሌሎች ተመሳሳይ ኬዞች ላይም ተፈፃሚ ስለሚሆን ኦፌኮና ኦነግ እጩዎቻቸው በምርጫ ቦርድ እንዲመዘገቡና ምርጫው ተራዝሞ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ። እዚህ ላይ ሁለቱ ፓርቲዎች “መሳተፍ እንችልም ብለው ራሳቸውን አግልለው የለም ወይ?” የሚል ጥያቄ ከተነሳ መልሱ ከላይ እንደገለፅኩት ያንን እንዲወስኑ ያደረጋቸው በቁጥር እጅግ በርካታ እጩዎቻቸው መታሰራቸውና በቦርዱ በእጩነት መመዝገብ ባለመቻላቸው መሆኑን መከራከሪያ ማድረግ ይቻላል።
 
ቦርዱ ይህን ጥያቄ አልቀበልም ቢል ወደ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ወስዶ መከራከር ይቻላል። የጠቅላይ-አግላይ ሃይሉ አይነተኛ መሳርያ የሆኑት የምርጫ ቦርድም ሆነ ፍርድ ቤቶች ለኦፌኮና ኦነግ ፍትሃዊ ውሳኔ ይወስናሉ የሚል እምነት የለኝም። እጬዎቻችን በመታሰር ላይ ናቸው ብለው አቤቱታ ሲያቀርቡ እንኳን የቦርዱ አመራር ጥያቄያቸውን በሃይለ-ቃል ሲያጣጥል ተመልክተናል። ፓርቲዎቹም ከእንግዲህ ይህን ለማድረግ ፍላጎት ላይኖራቸው ይችላል። ሆኖም ቦርዱንና ፍርድ ቤቱን በዚህ መንገድ መፈተን ቢቻል ጥሩ ነው። የፕ/ር መርጋ በቃናን አመራር የሚያስናፍቅ ስራ በመስራት ላይ የሚገኙት የቦርዱ አመራሮችም ምርጫውን አራዝመው ሁሉን ያካተተ ፉክክር የሚታይበት ምርጫ ለማድረግ ይህን እድል ቢጠቀሙ ቢያንስ ስማቸውን ያድሱበታል።
 
በነገራችን ላይ ኦፌኮና ኦነግ ራሳቸውን ለማግለል ከመወሰናቸው በፊት ቦርዱ ውስጥ የሚገኙ አንድ ሃላፊን እነ ጃዋር ጥፋተኛ እስካልተባሉ ድረስ በተመራጭነት የመመዝገብ መብታቸውን 1162 አይከለክልም ብላቸው “አስቂኝ ጥያቄ ነው የምትጠይቁት። ካሸነፉ በኋላ ፍርድ ቤት ካለቀቃቸው ቦታውን ምን ሊያደርጉት ነው?” የሚል ምላሽ ተሰጥቶኝ ነበር። እነ እስክንድር ከእስር ሳይፈቱ ቢያሸንፉ ቦታው እንዴት ሊሆን ነው የሚለውን አብረን የምናየው ይሆናል። ሰበር ሰሚ ዛሬ የወሰነው ውሳኔ ግን በቀላሉ የሚታይ አይደለም።