የፌደራል ስርዐቱን የሚቃወሙ “የልሙጥ አንድነት” አቀንቃኝ ሀይሎች ብዙ ጊዜ ፌደራሊዝሙ እንደ “ዩጎዝላቪያ” ይበታትነናል ሲሉ ይደመጣል፡፡

የፌደራል ስርዐቱን የሚቃወሙ “የልሙጥ አንድነት” አቀንቃኝ ሀይሎች ብዙ ጊዜ ፌደራሊዝሙ እንደ “ዩጎዝላቪያ” ይበታትነናል ሲሉ ይደመጣል፡፡

ይህ የዕውቀት ማነስ ካልሆነ በስተቀር ዩጎዝላቪያን የበታተናት የብሔር ፌደራሊዝም ሳይሆን እነዚህ ብሔሮች ይህንን መብት በመቀማታቸው በሂደት በተነሱ ጦርነቶች ነበር፡፡ ታሪኩን ባጭሩ ላስቃኛችሁ:-
——–
በ1918 የመጀመሪያው የአለም ጦርነት መጠናቀቁን ተከትሎ ስድስት ብሔር ተኮር ነፃ ግዛቶች ክሮሺያ፣ ሰርቢያ፣ ስሎቬኒያ፣ ቦስኒያ፣ ሜቄዶንያ እና ኮሶቮ በገጋራ በመሆን ዩጎዝላቪያ የምትባል ብሔር ተኮር ፌደራላዊ ሀገር መሠረቱ፡፡ እናም እስከ ሁለተኛው የአለም ጦርነት ማብቂያ እናየቀዝቃዛው ጦርነት መጀመሪያ 1945 ዓም ድረስ ፌደሬሽኑ በጥንካሬ ተጓዘ፡፡
———–
ከ 1945 ዓም በኃላ ሀገሪቱ የሶሻሊስት ርዕዮተ አለምን በማቀንቀን የብሔሮች መብት የሚጨፈለቅባት፣ የሰርቦች እና ክርስትያኖች የበላይነት የሚንፀባረቅበት “ልሙጥ ሀገር” የመሆን አካሄድ ጀመረች፡፡ በዚህ አካሄድ ብትቀጥልም በ1980 ዎቹ መጨረሻ ላይ እነዚህ ጭቁን ብሔሮች እና የቦስኒያ ሙስሊሞች ነፃ ለመውጣት የትጥቅ ትግል ጀመሩ፡፡
————
በዚህም በ1991 ክሮሺያ በመቀጠል ስሎቬኒያ እያሉ 2008 ላይ ኮሶቮ ነፃ ሀገር መሆንዋን ስታውጅ ዩጎዝላቪያ በይፋ ወደ ሰባት ሀገርነት ተበትና ፈረሰች፡፡ በፌደሬሽኑ ውስጥ የበላይነት የነበረው የሰርብ ብሔርም ቤልግሬድን በዋና ከተማነት ይዞ ሰርቢያ የምትባል ሀገር ተመሰረተች፡፡
———–
ከዩጎዝላቪያ ተሞክሮ ኢትዮጵያ መማር ያለባት የብሔር ፌደራሊዝምን ችግሮቹን አርሞ ማስቀጠል ሀገራዊ አንድነታችንን እንደሚያስቀጥል፣ ፌደሬሽኑን በማፍረስ የአንድ ብሔር የበላይነት ያለበት ልሙጥ ሀገር ለመገንባት መሞከር ደግሞ ሀገራችንን የመፍረስ አደጋ ላይ እንደሚጥላት ልብ ሊባል ይገባል፡፡

Haweni Dhabessa