የፊንፊኔ ጉዳይ የኦሮሞ የአገር ባለቤትነት ጉዳይ ነው

የፊንፊኔ ጉዳይ የኦሮሞ የአገር ባለቤትነት ጉዳይ ነው

ብርሃኑ ሁንዴ, Onkoloolessa 5, 2018

Shaggar
Neighborhood in Finfinne (now named Addis Ababa) before occupation about 1880

የፊንፊኔ ጉዳይ አብዛኛውን ጊዜ ሲነሳ ቢቆይም ባሁኑ ጊዜ ግን ልዩ ትኩረት ያገኘ ይመስላል። ይህንን ጉዳይ በሚመለከት የተለያዩ ውዥንብሮችም እየተፈጠሩ ናቸው። በተለይም ደግሞ የኦሮሞን ነፃነትና የአገር ባለቤትነትን የማይቀበሉ ኃይሎች በፊንፊኔ ጉዳይ ላይ የሚችሉትን ሁሉ ለማድረግ ቆርጠው የተነሱ ይመስላሉ። እነዚህ ኃይሎች ኦሮሞ በፊንፊኔ ላይ ያለውን የአገር ባለቤትነትን የሚቃወሙበት በተለያየ መንገድ ቢገለፅም፣ ዋና ዋና የሆኑትን ምክንያቶች እንደ ምሳሌ ለመግለፅ፥

 1. እያወቁ ግን የፊንፊኔን ታሪክ ለመደበቅ ብለው ይህቺ ከተማ የአማራ እንደሆነች አድርገው ለመግለፅ ይሞክራሉ። ይህን የሚያደርጉበት ምክንያት ደግሞ እውነት ስላላቸው ሳይሆን አፄ ሚኒሊክ በኦሮም ላይ የፈፀመውን ጥፋት ላለመቀበል ነው። ምክንያቱም ፊንፊኔ ከዚያ ታሪክ ጋር የተያያዘች በመሆኗ ነው።
 2. ፊንፊኔ ወደ እናቷ ኦሮሚያ ከተመለሰች ልክ በዚህች ከተማ የሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ሰዎች ተገፍተው እንደሚወጡ በማየት ነው። የኦሮሞ ሕዝብ የትኛውንም ብሔርና ብሔረ ሰብ እንደማይነካና እንደማይጎዳ፤ ባዕድን እንኳን ወደ ራሱ አስጠግቶ እንደሚያኖር፤ ሰላም ወዳድ ሕዝብ መሆኑን እያወቁ ግን ካላቸው ጥርጣሬና ፍርሃት የመነጨ በመሆኑ የፊንፊኔን ጉዳይ በሌላ መንገድ ይተረጉማሉ።
 3. ፊንፊኔ የስልጣንና የትግል ማዕከል በመሆኗ፣ ሁሉም ፊንፊኔን የፖለቲካና የኢኮኖሚ የእስትራቴጂ ቁልፍ ቦታ እንደሆነች አድርገው ያያሉ። የኦሮሞን የአገር ባለቤትነትን የሚቃወሙት ኃይሎች ፊንፊኔን ማጣት ማለት ኢትዮጵያን እንደ ማጣት አድርገው ስለሚያዩትና ስለምያምኑት፣ ፊንፊኔ በጭራሽ ኦሮሚያ ስር እንዳትገባ መራራ ትግል ማድረግ ይፈልጋሉ።

የፊንፊኔን ጉዳይ ለመቃወም የፈለጉትን ምክንያት ቢያቀርቡም፣ ቢወደደም ቢጠላም፣ ቢታመንም ባይታመንም፣ ለኦሮሞ ግን የፊንፊኔ ጉዳይ የአገር ባለበትነት ጉዳይ ነው። የኦሮሞ የነፃነት ትግል ዋና ዓላማው የኦሮሞን የአገር ባለቤትነትን ማራጋገጥ በመሆኑ፣ የኦሮሚያ እምብርት የሆነችውን ፊንፊኔን መተው አይችልም። በመሆኑም በፊንፊኔ ጉዳይ ላይ በኦሮሞ በኩል ኣንዳችም ቅድመ ሁኔታ መወሰድ የለበትም። ፊንፊኔ በታሪክም ሆነ በሕግ በኩል ሲታይ የኦሮሚያ አካል ናት። ኦሮሚያ እምብርቷን ከውስጧ አውጥታ መኖር አትችልም። በመሆኑም ፊንፊኔ ወደ እናቷ መመለስ የግድ ይሆናል።

እኔ እንደማስበውና እንደማምንው፣ ኦሮሚያ ከፊንፊኔ የምታገኘው ልይ ጥቅም ተብሎ መቀመጡ ራሱ ስህተት ነበር። ኣበት ከልጁ ወይም እናት ከልጇ የሚያገኘው ወይም የምታገኘው ልዩ ጥቅም ምንድነው?? ኦሮሞ ከፊንፊኔ ያለው የአገር ባለቤትነት እንጂ ልዩ ጥቅም የሚባል ነገር የለም ወደፊትም አይኖርም። ልዩ ጥቅም ማግኘት ያለባቸው በከተማይቷ የሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ሰዎች ናቸው። ይህም ማለት እነዚህ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ መብታቸው መከበር የግድ ይሆናል ማለት ነው። ነዋሪዎቹ ልዩ ጥቅም ማግኘት የሚችሉት ደግሞ በመጀመሪያ ፊንፊኔ ወደ ኦሮሚያ መመለስና ከዚያ በኋላ በከተማዋ አስተዳደር ወስጥ ኦሮሞ ያልሆኑት ነዋሪዎች እንደ ቁጥራቸው ውክልና ማግኘት መቻል ማለት ነው።

በስተመጨረሻ የትኛውም ኃይል ቢፍጨረጨርም፣ ቢፈራገጥም፣ ቢፎክርም፣ ቢሸልልም፣ የፈለገውን ሁሉ ለማድረግ ቆርጦ ቢነሳም፣ ነፃነትና የአገር ባለቤትነት በነፃ ስለማይገኙ፣ ኦሮሞ ኣንድ ሆኖ፣ ኣንድነቱንና ኃይሉን አጠናክሮ፤ አስፈላጊ በሆነ መንገድ ሁሉ ራሱን አዘጋጅቶ ይህ የፊንፊኔ ጉዳይ የመጨረሻ መፍትሄ እንዲያገኝ ማድረግ አለበት እንጂ ወዲያና ወዲህ ማለት፤ ሊደረግብን የሚችለውን ቅደመ ሁኔታ መቀበል ጭራሽ የማይታሰብ ነው። ኦሮሞ ስልጣን አግኝቶ ይህችን አገር እያስተዳደረ ነው በሚባልበት ወቅት በፊንፊኔ ጉዳይ ላይ ድክመት ማሳየት ወደ ሌላ ጥፋት ሊወስደን ይችላል። እየመጣብን ያለውን አደጋ ከሩቁ ማየት መቻል አስፈላጊና ወሳኝም ነው። ኦሮሞ ከፊንፊኔ የሚፈልገው ልዩ ጥቅም ሳይሆን ሙሉ በሙሉ የአገር ባለቤትነትን ነው። ይህ የኦሮሞ ተፈጥሮኣዊና ታሪካዊ መብቱ ነው። ይህ እውነታ ለጠላትም ለዘመድም ግልፅ መሆን ኣለበት።

ተመልሰን እስከምንገናኝ ደህና ሁኑ1 Comment

 1. That is it, Obbo Berhanu Hundee! Finfinne is part of Oromia and belongs to the Great Oromo People. The logic is simple; Gondar is part of Amhara and, therfore, belongs to the Amhara people. Similarly, Makale is patt of Tigrai snd it belongs to the Tigrian people. To mention an example from far away, London, a city where more than 300 languages are spoken in schools and at home, is part of England and belongs to the English people. It is also the capital of England as well as the UK. The English people who reside in the surrounding countryside are not stoned by ungrateful city residents when they come to London for any occasion. What is extraordinarily unbelievable is that those who robbed and stole Finfinne from its owners are still daring to stand up and argue with the true owner. Equally, it is worryingly unusual for the owners to hesitate to do everything it takes to get back what has been stolen or robbed from them.

  Qeerro and qarree in particular and the Oromo people in general have paid ultimate sacrifice to get the Oromo struggle to where it is now. The victory of our people should not fall short of retrieving Finfinnee from enemies who snatched it from them by inflicting savage, inhumane suffering and destruction. As much as we are peace loving nation who love to shsre with our neighbours, we shall also be assertive and push to reclaim what is ours. Others should also be cooperative to return Finfinne to its true owners, the Oromo.

  It must be crystal clear to those who deny the Oromo people ownership of Finfinne that the Oromo will stand in unison and ascertain that the heart, Finfinne, will return to the body, Oromia, to make it whole. For this matter, Qeerro, qarree, and every section of the Oromo people must maintain the momentum of political maturity. Moreover, other peace loving Ethiopians must work hard with their Oromo brothers and sisters to help truth prevail. Also, Ethiopian politicians as well as the Ethiopian government need to engage all stakeholders and facilitate the return of Finfinne to its owners, the Oromo people. Politics of deception must come to an end in that country if the twenty first century and beyond has to be peaceful for all the Ethiopian peoples.

  Stand firm for the truth!
  OA

Comments are closed.