የጫሂዎቹ ጫጫታ ለኦሮሞና ትግሬ ግብ የሚኖረው ጠቄሜታ፤ ፊንፊኔን በተምሳልነት ምልከታ

የጫሂዎቹ ጫጫታ ለኦሮሞና ትግሬ ግብ የሚኖረው ጠቄሜታ፤ ፊንፊኔን በተምሳልነት ምልከታ

By ፋልማታ ሳባ

አጅግ ብዙም ያልቆዬ ጊዜ ርዝማኔ ውስጥ አንድ ፀሀፊ (ስማቸውንም ጭምር አላስታውስም) እነኚህ እንደ ማሽላ የሚፈነዱ (pop corn politician) ቶለቲከኞች ሲላቸው ነበር፡፡ ሰውየው አስተውለው ጥሩ ብለዋል፡፡ ማንነታቸውን ሳያውቁ የሌላውን ማንነት ለመተንተን የሚጥሩትን፣ ሳይገባቸው የሚተረጉሙትንና አህያ ሳይኖራተውን የሌላውን በቅሎ የሚንቁትን “ያልገባቸው” ከማለት ሌላ ምን ልንላቸው እንችላላን? ኦሮሚያን ወደ ምስራቅና ምዕራብ መከፋፈል ያስፈልጋል በሚል አንድምታ አንድ የታሪክ ፕሮፈሰራቸው (ቤታቸው ሀይሌ) ቦረናና ባሬንቱ አንድ አይደሉም፣ ሆነውም አያውቁም፤ ነገር ግን እኛ ሳንነቃ ኦነግ (አቶ ሌንጮ) እና ህወሃት (ሟቹ መለስ) ስለሸወዱን ኦሮሚያ የምትባል ሀገር (ክልል) በስህተት ተፈጠራች፣ ያኔ ማንም ይኸን አላሰበም፡፡ አሁን ላይ የኦሮሞ ሀገር የት ነው ስንላቸው በቀላሉ የኦሮሚያን ካርታ ያሳዩናል ሲሉን ነበር፡፡

እስኪ አሁንም አዲስ አበባችሁ እንዳያመልጣችሁ አትተኙ እባካችሁ ልባለቸውና ልለፍ፡፡ ይኸን ከቀድሞው ዝባዝንብኬ ሀሳባቸው ናሙና ጠቀስኩ እንጅ እነሱ ስለ ኦሮሞና ትግሬ የሚያወሩት ተረት ተረት ብዙ ነው፡፡ የኦሮሞና ትግሬ ጉዳይ ስም የማይወጣለት ከሆነባቸው፣ ከተቸገሩና ሲጨንቃቸው (የሚያቀርቡባቸው የሀቅ ትችት ሲያጡ) በአደባባይ የማይወራ (taboo) ነው ብለው በማለፍ አስተሳሰባችንን ሊያደነዝዙ ይሻሉ፡፡ እንኳን ስለ ሌላው ብሔር ይቅርና ስለራሳቸው የአይሁድ ዝርያ ነን በማለት የሚያወሩትም በታሪክ ያልተደገፈ እና ፍርክሰክሱ እየወጣ ያለና ራቆታቸውን በጥቂት መንደር ወስጥ ተሸጉጠው የምናገኛቸው ስለመሆናቸው ሁሉም ዛሬ ላይ ገሃድ ነው፡፡ ዘመኑ የሚንለክ ዘመን አይደለምና የቁቤ ትውልድ እነኚህ እንደ አባት አርበኛ ከመቶ ዓመት በኃላም ይፎክራሉ እንደ እያለ ጠይቆና ንቆ ሊያልፋቸው ተገደደና ግመልዋ ጉዞዋን ቀጠለች፡፡

እነርሱ (ያልገባቸው) አሁን ደግሞ በፊንፍኔ ዙርያ ይጠይቃሉ፣ ያወራሉ፣ ይጮሃሉ፣ ይተረጉማሉ፡፡ ብዙ ናቸውና የጥቂቶቹን ጽሁፍ በከፊል ልተችበት ፈለግሁ፡፡ ሰሞኑን ከሀበሻ ድህረ-ገጾች ያገኘኋቸውን ሀሳቦች በጥቅል ደረጃ ላተኩርበት፡፡ እንዲያው እንዳይቀየሙኝ ከፊሎቹን ስማቸውን ጠቅሼ የጥያቄያቸውን አላግባብነት (irrelevance) ላሳይ፡፡ ግርማ ሰይፉ፣ ግርማ አሳ እና ሳቲናው ከሰሞነኞቹ የሚጠቀሱቱ ናቸው፡፡

በዘመናቸው ሕግ የሚል ሳይኖራቸው የታየውን የህግ ጭላንጭል ይተቻሉ፡፡ ተጨባጭ የሆነ ከህግና ቢሮክራሲ አንጻር የማንነታቸው ገላጭ ነውና በሚከተለው ልጀምር፡፡ አንዱ ወዳጅ በአዲስ አበባ መስተዳደር ውስጥ መሬት ልማት ክፍል ተሾመና ሂዶ ስራ ጀመረ፡፡ ሁለት ሰዎች በይዞታ ይገባኛል ጥያቄ አቤቲታቸውን ይዘው ይኸው ሰው ዘንድ ለአቤቱታ ቀረቡ፡፡ እናም ይኸ ሰው አዲስ ተሹሞ የሄደ እንደመሆኑ መጠን ነባሮቹንና በባለሞያነት ከሚንሊክ ጊዜ ጀምሮ የተቀመጡትን እስኪ ፋይላቸውን አቅርቡልኝ አላቸው፡፡ ሲመልሱለት እኛ እኮ ኑና እዚህ ስሩ ተብለን ተቀጠርን እንጂ ፋይል ይኑር አልተባልንም ብለው ለአዲሱ አለቃቸው መለሱለት፡፡ ይኸ የሚያሳየው ያለ ህግ በወሬና በማምታታት እርስ በርስ ሲጠቃቀሙ ይኖሩ የነበሩት ዛሬ ላይ ግን ሕዝቦች የተስማሙበትን ሕገ-መንግስት ሳይቀር ይጸየፋሉ፡፡ ንጉሰ ነገስቱ ስላልሰጡን ይሆን ወይስ አንቀጽ 39 በሥራ ለይ ስላልዋለ ይሆን የሚጮሁት?

ከተጠቃሾች እንዱ አንቀጽ 49(5) ጠቅሰው ሕገ-መንግሥቱ ፊንፊኔ የሚል ቃል የለውም ይሉና ፊንፊኔ በአዲስ አበባ የአንድ አካባቢ መጠሪያ ነው እንጂ አጠቃላይ አሁን አዲስ አበባ ለሚባለው አይደለም በማለት ሀሳባቸውን ያስረዝማሉ፡፡ በህልማቸው ሳይቀር ሲያስፈራራን የኖረ ነው ያሉትን ሕገ-መንግስት ለኦሮሞ መብት ማስከበሪያ እንዳይውል ግን ሕገ-መንግስቱ ተሸረሸረ በማለት ሊከላከሉት (defend) ይሻሉ፡፡ ስለዚህ ይህ አካሄድ ሊታሰብበት ይገባል ይሉናል፡፡ ሰውዬው ያልገባቸው ሕገ መንግሥት የሕዝቦች መብት ማስከበሪያ እንጂ መብት መንጠቂያ አይደለም፡፡ ነባራዊ ዕውኔታን የመግለጽ አቅሙ ያልተሟላ ሕገ-መንግሥት ሊሻሻል ይችላል፡፡ ስለዚህ በአጭሩ ነባራዊ ዕውኔታው አዲስ አበባ የሚለው የቅኝ ገዥዎች ስያሜ በነባሩ መጠሪያና ቋንቋ (native language and indigenous name) ወይም የኦሮሞው ሕዝብ በመረጠው ስም ይጠራል፡፡ ወደ ስያሜው ሀሳብ መስጫ ለመሄድ ደግሞ ኦሮሞ መሆንን ግድ ይላል፡፡ ስለዚህ የጠቀስኩትን አሳብ ያመነጩት ሰዎች በኦሮሞ ጉዳይ ብዙም መጨናነቅ የሚያሻቸው አይመስለኝም፡፡ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሱማሌ ሕዝብ ካለ የእነርሱ የሆነ ክልል አለ ማለት ነው፡፡ በሕገ-መንግሰት ውስጥ የለም ከተባለ በሂደት ማካተት ነው እንጂ ሌላ ዝባዝንኬ ማምጣት አያሻም፡፡አይፈይድምና፡፡

ስለ 25 በመቶ መቀመጫ እና የአዲስ አበባ ከተማ ተጠሪነት ለፌደራል ክልል መሆን ያለመሆን ሳይሆን ግቡ ሀገሩን ለባላገሩ የማስረከብ ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህ የሚሸራረፈው መብት አሁን ያለንበትን የሀይል ሚዛን ወይም ይቅር ባይነታችንን ያገናዘበ ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ ፀሀፊዎቹ ደጋግመው የሚሽከረከሩበት ሀሳብ አለ፡፡ አንደኛው እንደሚከተለው ጽፈዋል፡፡ “በዚህ አይበቃም የሕገ መንግሥቱን አንቀፅ 25 “የእኩልነት መብትን” ይፃረራል፡፡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የየትኛው ብሔር አባል መሆናቸው ለልዩነቱ መሰረት መሆኑ ደግሞ ግልፅ የሕገ መንግሰት ድንጋጌ ጥሰት ነው፡፡” ይጻረራል የተባለው ስለ ኦሮሞ ልዩ መብት የቀረበውን ረቂቂ ሀሳብ ፀሀፊው ሲተቹ ነው፡፡ ፀሃፊው በሚኖሩበት የስደት ሀገር ይሔንና መሰል ጥያቄ አቅርበው ከዚያ በኃላ ስለ ስኬታቸው በምሳሌነት ለዚህ ጽሁፋቸው መነሻ ለሆነው ጉዳይ ቢጠቀሙ የበለጠ አስረጂ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ሁሉም የሀባሻ ፀሀፊዎች በሚባል ደረጃ ዞር ይሉና ስለ ኦሮም የአዞ እንባ ያነባሉ፡፡ ለምሳሌ አንዱ ጸሀፊ የሚከተለውን ጽፈዋል፡፡ ይህ ረቂቅ አዋጅ በአንቀፅ 8 “የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች መብት” በሚል ርዕስ አንድም እርባና የሌለው የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች እንደማንኛውም ሰው ሊከበርላቸው የሚገባን መብት ይጠቅሳል፤ የሚያሳዝነው በአንቀፅ 10 መርዕ አልባ “የልዩ ጥቅሙ መርሆዎች” በሚል ያስቀምጣል፡፡ ይህን ካሉ በኃላ ያስከተሉትን ዝርዝር ለአንባብ ትቼ እኔ እንዲህ ልበላቸው፡፡ ጸሃፊው ኦሮሞን ሶስተኛ ወገን (third person) አደርገው ስለሆነ የጻፉት እርሳቸው ኦሮሞ እንዳልሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ከሆነ ደግም የአዛኝ ቅቤ … ያስመስልባቸዋል፡፡ ይልቁን ደግም የኦሮሞ መብት የእኔን ጥቅም ይጎዳል ብሎ ከሚያስብ ወገን ከሆኑ ለኦሮሞ መቆርቆር ፀሃፊውን አይመለከታቸው ያስብለኛል፡፡

ፀሃፊው አዲስ አበባ ከተመሰረተች 125 ዓመት ሲሆን፤ ኦሮሞ የሚባል ክልል የተመሰረተው ደግሞ 25 ዓመት ቢሆን ነው፡፡ ይህ ብቻም አይደለም መሬቱ ቀድሞ የኦሮሞዎች ነበር ከተባለ ከዚያ በፊት የማን ነበር? ኦሮሞዎች እንዴት በቁጥጥራቸው ውስጥ አደረጉት? ብሉ መጠየቅ ያስፈልጋል ብለውናል፡፡ ሁለት ነገሮች ተለያይተው መታየት አለባቸው፡፡ በግርግር መካከል ዳቦ ጠፋ እንዳይሆን ማለት ነው፡፡ ክልል ተመሰረተ የሚለውና መሬቱ ከ125 ዓመታት በፊት የማን ነበር፣ እንዴት የኦሮሞ ነው ተባለ የሚሉት ሁለት የሚለያዩ ጥቄዎች ናቸው፡፡ አዎን ኦሮሚያን ወደ ነበረችበት ደረጃ የመመለሱ ትግል ባለፉት 25 ዓመታት የተሻለ ውጤት አስመዝግቧል፡፡ ቀሪው ይቀጥላል፡፡ ከሚኒልክ በፊት አዲስ አባባ ይኖር የነበረው ማነው የሚለው ጥያቄ ውሀ አይቋጥርም፡፡ በጣምም ግልጽ ነው፡፡ ታሪክን በማንበብና ስለ ዓለም ሕዝቦች መስፋፋት ስናጠና ኩሽን በተለይ ደግሞ ኦሮሞን በአፍርካ ቀንድ በነባር ነዋሪነት እና ሀበሻን ከቀይባህር ማዶ በሳባ ዝርያነት እናገኛለን፡፡ በተረፈ ለመመለስ ግን ጠያቂያችን ማንና በምን ደረጃ (status) ላይ ሆነው እንደሚጠይቀን በቅድሚያ ለማረጋገጥ እንገደዳለን፡፡

ሌላው ፀሀፊ የሚከተለውን ይሉናል፡፡ ”በነገራችን ላይ ኦህዴዶችም ሆነ ኦነጎች፣ ኦሮሞ ፈርስቶችና ዉጭ ያሉትም ሆነ አገር ዉስጥ ያሉ የኦሮሞ አክራሪዎች ትልቁ ግባቸው አዲስ አበባን እና አካባቢዋን በሃይል Oromized ለማድረግ ነው። በአዲስ አበባም ሆነ በሸዋ የሚኖረው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ራሱን ኦሮሞ ብሎ የማይጠራ ኢትዮጵያዊ ጉዳይ ለነርሱ ጉዳያቸውም አይደለም። “ፊንፊኔ የኦሮሞ ናት፤ሌላው በኦሮሞው ፍቃድ ነው የሚኖረው” የሚል እምነት ነው ያላቸው። በአዲስ አበባ የሚኖር 10% የሚሆን የሜጫ ቱሉማ ኦሮሞ የሚሉት አፋን ኦሮሞ ተናጋሪ፣ መብቱ እንዲከበርለት በሚል አዲስ አበባ ወደ ኦሮምያ እንድትጠቃለል ሲጠይቁ፣ 90% የሚሆነው አፋን ኦሮሞ የማይናገረው ሕዝብ ኦሮሚያ ዉስጥ በመግባቱ መብቱ እንደሚረገጥ ግን ሊታያቸው አልቻለም።” ወደ ሌላ የኦሮሞ ከተማም ይዘሉና ከክሳቸው ያወጡት መረጃ በሚመስል እገሌ ይሄን ያህል ነው እገሌ ያን ያህል ነው በማለት የመኖርያ ፈቃድንና የነባርነትን ጉዳይ ለማዘባት ይጥራሉ፡፡ መኖር ሌላ የባለቤትነት ጉዳይ ሌላ፡፡

የመተርጎም መብታቸውን ለተርጓሚው እያከበርኩ የትርጉም ስህተት ሲኖር ግን የፀሀፊው ሀሳብ ብቻ ተቀባይ ነው፡፡ ኦሮሞዎች ያልነው ክርስትና ስሞች ወደ ታቦታቸው ተመልስው ፊንፊኔ በትውልድ ሰሟ ትጠራ፡ የልደት ወግና ባህሏ በነዋሪዎችዋ ተከብሮላት ኑሮ ይቀጥል ነው፡፡ ስለዚህ “አካባቢዋን በሃይል oromized ለማድረግ“ ሳይሆን ፊንፊኔን ከሴማዊ የተውሶ ድሪቶ ለማላቀቅ ነው፡፡ የፊንፊኔ አካባቢማ ያው ፊንፊኔ ነው፡፡

ለመሆኑ እነኚህ ጠያቂዎቻችን እነማን ናቸው? የራሴ ነው የሚሉት የላቸውም፡፡ ያንተን አምጣና የኛ ነው ብልን እኔ ልብላ የሚል ልክፍት ምን ይባላል፡፡ ሶማሌው፣ ሲዳማው፣ ከምባታው፣ ትግረው.፣ ወላይታውና ሌሎቹ ደቡቦች ስለ ፊንፊኔ ኦሮሚያዊነት ሳይጠይቁን እነኚህ የሚኒልክ ርዝራዞች ብቻ የሚያነሱት የቡና ላይ ወሬ መሰል በታሪክ፣ በእውኔታና በዕውቀት ላይ ያልተመሰረተ ጥያቄ የሚያስረዳን ቁምነገር ቢኖር አንድና አንድ ነው፡፡ አባቶቻችን በደም ያቀኑዋትን (colonize) እና ያስረከቡንን ኦሮሚያ ጮክ ብለን ሳናለቅስ አንልቅም ነው፡፡ ይኸ ከሆነ ደግሞ ጨዋታውና የኛ መልስ የሚሆነው ባዶ እግርህን ድሪቶ ለብሰህ መጥተህ ነበር፤ ጫማ ገዝተንል ሱፍ አልብሰንማል፡፡ ሳያልቁብህ የያዝከውን ይዘህ በጊዜ ብታመልጥ ይሻልሃል የሚል ቀዳማይ ምክር ነው፡፡ በጨዋ ደንብ ከፋም ለማም ያለፈው አልፏልና የወደፊት አቅጣጫችን ያለፈውን ስህተት የተገነዘበ እና ወደ ፊት ለሚመጣው ጊዜ ሚዛናዊ በሆነ መንገድ በጋራ መፍትሄ በጋራ ለመኖር እንጣር የሚል ድርጎ በውስጣቸው አልተፈጠረም፡፡ እንደ ተኩላ የበግ ቆዳ ለብሰው መጥተው ግልገል ነጥቀው ለመሮጥ ሲባዝኑ ብቻ ነው በተጨባጭ የሚታዩት፡፡ እናንተ ወያኔ በተላላኪው በኩል ሸራርፎ ለሚሰጠን ቁራጭ መብት ስታላዝኑ ጀግኖቹ የኦሮሞ ልጆች አስገድደው፣ አዲስ አበባ የሚለው የጌቶቻችንን ስያሜ እና የሚንልክን ድንደጋይ ተጠራርገው ወደ ሙዝየም የሚያስገቡበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡ የፊንፊኔ ሕዝብ ግን እንደ ሕዝብ ኑሮውን ይቀጥላል፡፡ ለማየት ዕድሜ ይስጠን፡፡

ከትግረ ጋር እንጂ ያለን የጋራ ስትራቴጅ አይደለም ከእነዚህ አወናባጅ ያልነው ወደን አልነበረም፡፡ እውኔታው ነው ያስገደደን፡፡ ምክር እንጂ ዘለፋ እንዳላቀረብኩ አስባለሁ፡፡ ጨው ሆይ ለራስ ስትል ጣፍጥ አለበለዝያ ዳሎል ሂዶ የሚያፈላልግህ የለም፡፡

ከቀረበው ረቂቅ አንጻር ኦሆድድ ማሰብና ከከንቱ ድካሙ መላቀቅ ያለበት በሁለት መቅረት የሌለባቸው ነጥቦች ነው፡፡

  1. ታሪክን ወደ ነበረበት ከመመለስ አንጻር አዲስ አበባ የሚለው የቀኝ ገዥዎች ስያሜና የሚንልክ ሀውልት ወዲያው ወደ ሙዝየም መግባት ያለባቸው ናቸው ፡፡ ነገር ግን እናንተ የሚንልክን ሀውልት ለማፍረስ ስትወጡ ወያኔዎች በቀለም እያስገጡ ስለነበረው ዘመንና ከሥፍራው የተበረራችሁበት ሁኔታ አሁንም እንዳይከተላችሁ አስቡበት፡፡ የሕዝባችሁን ፍላጎት ከተከተላችሁ ግን ሕዝባችሁም ከጎናችሁ ነው፡፡ ስለዚህ ማንም አይደፍራችሁም፡፡
  2. አፋን ኦሮሞ የፊንፊኔ አማርኛ ተጓዳኝ ብቻ ሳይሆን በፌዴራልም ተጓዳኝ መሆን አለበት፡፡ ያለ በለዚያ የፊንኒኔን ሪፖርት የፈደራል መንግስት ላይቀባለችሁ ነውና ወደ አማርኛ የመተርጎም ግዴታ ሊመጣባችሁ ነው፡፡ ከቁቤው ወጣት ትውልድ ምትም አታመልጡም፡፡

ወዶና ፈቅዶ መብታችንን እየሰጠን ያለ ስለመኖሩ እኔ አላውቅም፡፡ እኔ የማውቀው አስገድደን መብታችንን ማሰመለስ መቻል ስላለብን በትግሉ መቀጠል ስለመቻላችን ነው፡፡ ስለዚህ የጫሂዎቹ ጫጫታታ ለኦሮሞና ትግሬ ግብ የሚኖረው ጠቄሜታ አንድና አንድ ነው፡፡ መብታችንና ጥቅማችሁን በእኩል ደረጃ ሳትመለከቱ ሰጥቶ በመቀበል መርህ ከቻላችሁ የጋራ መንገድ ለመራመድ የድርድር በር ከፈታችሁ ማለት ነው፡፡ የዚህ አንዱና ወሳኝ ምዕራፍ የፊንፊኔ በነባር ስሟ ብቻ መጠራትና የአፋን ኦሮሞ ፌደራላዊነት በዚህ ረቂቂ ውስጥ መካተትና ያለመከታት ጉዳይ ነው፡፡

ሰላም ቆዩኝ፡፡

2 Comments

  1. ሉመሆኑ እነኚህ ጠያቂዎቻችን እነማን ናቸው? የራሴ ነው የሚሉት የላቸውም፡፡ ያንተን አምጣና የኛ ነው ብሉን እኔ ልብላ የሚል ልክፍታቸው ምን ይባላል፡፡ ሶማሌው፣ ሲዳማው፣ ከምባታው፣ ትግረው.፣ ወላይታውና ሌሎቹ ደቡቦች ስለ ፊንፊኔ ኦሮሚያዊነት ሳይጠይቁን እነኚህ የሚኒልክ ርዝራዞች ብቻ የሚያነሱት የቡና ላይ ወሬ መሰል በታሪክ፣ በእውኔታና በዕውቀት ላይ ያልተመሰረተ ጥያቄ የሚያስረዳን ቁምነገር ቢኖር አንድና አንድ ነው፡፡ አባቶቻችን በደም ያቀኑዋትን (colonize) እና ያስረከቡንን ኦሮሚያ ጮክ ብለን ሳናለቅስ አንልቅም ነው፡፡ ይኸ ከሆነ ደግሞ ጨዋታውና የኛ መልስ የሚሆነው ባዶ እግርህን ድሪቶ ለብሰህ መጥተህ ነበር፤ ጫማ

Comments are closed.