የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አደም መሃመድ ከሳዑዲ አቻቸው ጋር ተወያዩ
#Ethiopia– #SaudiArabia: Gen. Adem Mohammed, Chief of the General Staff of the Ethiopian National Defense Force (ENDF) met & held discussions with Gen. Fayyadh Al Ruwaili, Chairman of the Saudi General Staff. The two discussed bilateral ties in intelligence & military areas. FBC
የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አደም መሃመድ ከሳዑዲ አቻቸው ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አደም መሃመድ ከሳዑዲ አቻቸው ጀኔራል ፋያድ አል ሩዋይሊ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም ሀገራቱ በመከላከያው ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
ከዚህ ባለፈም ሀገራቱ በደህንነት እና ወታደራዊ ዘርፎች ላይ ያላቸውን ግንኙነት የጋራ ጥቅምን ባስከበረ መልኩ ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸው ነው የተገለጸው።
በሳዑዲ ሪያድ በተካሄደው በዚህ ውይይት ከሁለቱ ሀገራት የተውጣጡ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተሳትፈዋል።
በተመሳሳይ ጀኔራል አደም መሃመድ ከሳዑዲ ዓረቢያ ሰብዓዊ እርዳታ ድርጅት ረዳት ተቆጣጣሪ ጀኔራል አህመድ ቢን አሊ አል ባየዝ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
FBC (Fana Broadcasting Corporate
ለህዝብ ጥያቄ ዘላቂ ምላሽ የመስጠት ዝግጁነት