የጌዲዮ ጉዳይ; Obboo Waaqoo Waajii Duubee hidhame; Midaa Qanyiitti Kaabinoonni OPDO samaa jirti

የጌዲዮ ጉዳይ; Obboo Waaqoo Waajii Duubee hidhame; Midaa Qanyiitti Kaabinoonni OPDO samaa jirti

Via Girma Gutema Bitootessa 15, 2019

1. እዚህ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚለጠፉትን በችጋር የተጎሳቆሉ የናቶችና ህጻናት ምስሎችን ማየት የሁሉንም ሰው ልብ የሚያደማ ነው። ሆኖም ግን በጌዲዮ የተፈጠረውን ይሄን አሳዛኝና ውስብስብ መንስኤ ያለውን ችግር ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ መጠቀል ትክክል አይደለም። የዚህ አስከፊ ችግር ምንጩ ውስብስብና ሚስኪኑን ደሃ ህዝብ እንደ ኢንስትሩሜንት በመጠቀም የኢኮኖሚ ብሎ የፖለቲካ ጥቅሞችን አላግባብ ለማጋበስ ካካባቢው በወጡ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ሊህቃን ከህዝቡ ኋላ ሆነው የሚተውኑት ሸፍጥ ስለመሆኑ ግን ብዙው በጉዳዩ እያዘነ ያለው ሰው የሚያውቀው አይመስልም።

2. ጌዲዮ ከፍተኛ የሆነ የመሬት ጥብት ያለበት አካባቢ መሆኑ የታወቀ ነው። ይሄ ቢሆንም በረጅም ጊዜ የብልጣብልጥነት እቅድ የቡና እርሻዎቻቸውን ስለጫወታው ብዙም ግንዛቤ የሌለውን ደሃ ህዝብ ኢንስትሩሜንታላይዝ በማድረግ ለማስፋፋት ከኋላ አቀናጅቶ ህዝቡን የኦሮሚያ ስቴት ግዛት ውስጥ አስገብቶ በማስፈር በህዝቡ ጀርባ ላይ ተንጠልጥለው ቁማር የሚጫወቱ ሃብታም የቡና ነጋዴዎችና የፖለቲካ ብሎም ራሳቸውን የሾሙ ሃይማኖታዊ “ነብያት” ሸሪኮቻቸው እየሄዱበት ባለው በዚ መንገድ የጌዲዮ አካባቢ የመሬት ጥበት ይፈታል ብሎ መቀበል ግን የሚያስኬድ አይደለም። ይሄን አካሄድ መቀበል ማለት ኦሮሞዎች ይሄ ዓይነቱ የተቀናጀ የብልጣብልጥነት ደባ በደቡብ/ጌዲዮ ስግብግብ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ሊህቃንና ሌሎች ሸሪኮቻቸው ሲካሄድባቸው ዝም ብለው ማየት ነበረባቸው የሚል ኢፍትሃዊ አቋም መውሰድን የሚጠይቅ ነው። ይሄ ደግሞ አግባብ ሊሆን አይችልም ተቀባይነትም የለውም።

3. ጌዲዮ በፌዴሬሽኑ ውስጥ ከኦሮሚያ ራሱን ነጥሎ “ደቡብ” የሚባል ሌላ የፌዴሬሽኑ አባል ስቴት ውስጥ እስከገባ ድረስ፣ ሌላ የተቀነባበረ የብልጣብልጥነት አሻጥር እንኳን በጉዳዩ ውስጥ ባይኖርበት “የመሬት ጥበት” በሚል ምክኒያት ከአንድ ስቴት ወደ ሌላ ስቴት የሚደረግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የህዝብ ሰፈራ (mass population settlement) በህግም፣ በህገ መንግስትም፣ በሞራልም (በተለይም ኦሮሚያ ባልተስማማበት ሁኔታ) ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም።

4. በመሰረቱ በዚህ ዘመን የመሬት ጥበት ችግር የሚፈታው ህዝብን ከአካባቢው አንስቶ በገፍ ወደ ሌላ ቦታ ላይ በማስፈር አይደለም። ያለነው በ21ኛው ከፍለዘመን ውስጥ በመሆኑ፣ ሌሎች አካባቢው በፍጥነት ለምቶ በትንሽ ቦታ ላይ ብዙ ሰዎች ሰርተው መኖር የሚችሉበትን እንደ focused urbanization, accelerated industrialization, efficient utilization and effective management of land resources… እና መሰል የፖሊሲ አማራጮችን ስራ ላይ ማዋልን ነው በጉዳዩ ላይ ጥናት ያካሄዱት ምሁራን የሚመክሩት። ይሄ ከኛ ሃገር የድህነት ሁኔታና ከችግሩ አጣዳፊነት አንጻር fancy proposal ነው ብሎ መከራከር ይቻል ይሆናል፤ በምንም መመዘኛ ግን ካካቢቢው የሚያጋብሱትን ሃብት መልሰው እዛው ኢንቬስት በማድረግ የችግሩ መፍትሄ አካል ከመሆን ይልቅ ሃብቱን ፊንፊኔ ወይም ሃዋሳ ላይ ኢንቬስት እያደረጉ ያካባቢውን ህዝብ ያደኸዩት ስግብግብ የጌዲዮ/ይርጋጨፌ ቡና ነጋዴዎችና ሌሎች ተባባሪዎቻቸው ከኋላ በሚያቀናጁት ህገ ወጥ የኦሮሚያ መሬቶች ላይ የሚደረግ ሰፈራ በጌዲዮ አካባቢ ላለው የመሬት ጥበት መፍትሄ ተደርጎ ሊወሰድ በፍጹም አይችልም። ደግሞም በሌሎች አካባቢዎች የተትረፈረፈ ባለቤት አልባ (terra nullius) መሬት የለም። አይ የለም ችግሩን ለመፍታት ህዝብ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ማስፈር የግድ እንደ አንዱ የመፍትሄው አካል ተደርጎ መትግበር አለበት የሚባል ከሆነ ደግሞ የጌዲዮ ሊህቃን የግድ ከኦሮሚያ ጋር መደራደር መቻል ያለባቸው ይመስለኛል። ምናልባትም ከኦሮሚያ ጋር ለመሆን ይህ ነው የሚባል የቋንቋም ሆነ የባህል ቤሪየር የሌለባቸው ጌዲዮዎች በራሳቸው ፍልጎት በሚጀምር ድርድር ወደ ኦሮሚያ መምጣት የሚችሉ ከሆነ የተጠቀሰው የህዝብ ሰፈራ ባንድ ስቴት ውስጥ የሚደረግ (intrastate state population settlement) እንጂ ካንዱ ስቴት ወደ ሌላው (interstate population settlement) የሚደረግ ስለማይሆን፣ ሰፈራው እንደ አንዱ የመፍትሄው ተግባር ተደርጎ ሊታይ ይችል ይሆናል።

5. አሁን በጊዜአዊ IDP shelters ውስጥ ተቸግረው የሚገኙት ሰዎች ለቀው የመጡባቸው ቦታዎች ከዚህ ቀደም በተደረገ ህዝበ ውሳኔ (referendum) ጭምር ወደ ኦሮሚያ የተካለሉ ናቸው። ይሄን ሃቅ ደግሞ የደቡብ መንግስት ባለስልጣናትም የሚክዱት አይደለም። እንዲህም ሆኖ ግን በኦሮሚያ መንግስት በኩል ቱጃር የጌዲዮ/ይርጋጨፌ ቡና ነጋዴዎቹ ከኋላ የሚዘውሩት ይሄ ችግር ቀድሞም እንዳይፈጠር፤ ከተፈጠ ደግሞ ደሃው ህዝብ እንዲ ቪክቲማይዝድ ሳይደረግ ችግሩ ሊፈታ የሚችልበት የመፍትሄ አቅጣጫ ላይ በበቂ ሁኔታ እንዳልተሰራበት ለማናችንም ግልጽ ነው። ስለሆነም አሁን እነዚህ እናቶችና ህጻናት ላሉበት አስከፊ ችግር የኦሮሚያ መንግስትም የራሱን ተገቢ ድርሻ ማንሳት ተገቢ ይሆናል።

በመጨረሻም፣ ተዓማኒነት ካላቸው ምንጮች ባሰባሰብኩት መረጃ ላይ ተመርኩዤ ይሄን አስተያየት የጻፍኩት ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያሉትን የጌዲዮ እናቶችና ልጆቻቸውን ወቅታዊ ችግር ባለመረዳትና ባለማዘን አቃሎ ለማቅረብ ሳይሆን፣ ችግረኞቹ ያሉበትን አስከፊ ሁናቴ በፎቶ እያሰራጩ ኦሮሞዎችን ጭራቅ አስርጎ ለመሳል እየተሞከረ ባለው የታች ሰፈር ልጆች ፕሮፓጋንዳ ባለማወቅና በቅንነት ሊታለሉ ለሚችሉ ወዳጆቻችን የችግሩን አውድ (context) ለማስቀመጥ ነው። ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት ችግሩ የተከሰተበትን ነባራዊ አውድ (real context) መረዳት ያስፈልጋል ብዬ አምናለው። ችግሩን ከአውዱ ውጪ በማቅረብ የሚራገበው የማጠልሸት ፕሮፓዳንዳ አንድም አሁን እነዚህ እናቶችና ልጆቻቸው ያሉበትን ነባራዊ ችግር አይፈታላቸውም፤ ሁለትም የህዝቦችን ግንኙነት በማሻከር ጉዳት ሊያመጣ ይችላል።

በጉዳዩ ላይ በቅንነት የተሞላ ውይይት እንጂ የማጠልሸትና የፕሮፓጋንዳ ኦፒኒየኖችን በገጼ ላይ እንደማላስተናግድ አስቀድሜ መግለጽ እፈልጋለው። አመሰግናለው።


#Godina_Gujii_Bahaa
#Hidhaan_ittifufe

Via Oromiyaa Harmeekoo

“Jiraataa fi jaarsa biyyaa Godina Gujii Bahaa Aanaa Aagaa Waayyuu Gandaa Waachuu Diima kan tahe Obboo Waaqoo Waajii Duubee kan koree teknikaa WBO galchuuf dhama’aa ture hardha PDO’n galata wollaaltee badii tokko malee ukkamsitee fuutee jirti.

Nami kun haga ani beekutti nama haqa saba kanaatiif karaa dandahe maraan falmaa tureeru. Woyyaanee amma biyya ifiitti galte tanalle PDO amma isa hiite caalaa mormee dadhabsiisaa nama ture. Jijjiirama amma baanan kanas harka guddaa keessaa qaba. Sababa kanaafis hidhaa yeroo hedduu hidhameera.

Nama jireenna isaa guutuu jijjiiramaa fi bu’a ifii cinatti dhiisee bu’aa sabaatiifi falmaa turee itti jiru maqaa kijibaa irra kaayanii hidhuun aad-malee. PDO’n maqaa olaantummaa seeraa jedhuun nama yaadaan sodaattu hundaa mana hidhaatti guuruun kun akka sabaatti tahee akka dhaabaatti kisaaraa malee bu’aa tokko hin qabu.

PDO’n gaafa muddamtu nama ergataa gaafa diqqoo itti tole namuma san deebisanii hidhuun kun amala woyyaanummaati. Kanaaf nuuti dhihaa barii jijjiiramni gubbaatti dhageennu sun Gujii lamaanuu hin geenne wonni jennuuf.

Yoo afaan namaa beettan teete jaarsa kanaafi namoota guyyaa guyyaa mana hidhaatti guurtanii itti taphattan kana gadi dhiisaa karaa nageyaa fi seeraatiin biyya bulcha silaa bulchuu dadhabdaniiti kan jaarsaa fi jaartii guurtanii rakkisaa jirtaniif.”