የደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 5ዓመት 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በነገው ዕለት እንደ ሚያካሂድ ተገለፀ፡፡

የደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 5ዓመት 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በነገው ዕለት እንደ ሚያካሂድ ተገለፀ፡፡
ምክር ቤቱ በሚያካሂደው አስቸኳይ ጉባኤ ላይ የተለያዩ አራት አጀንዳዎችን መሠረት ያደረገ ሲሆን በዋናነት አንደኛ አጀንዳ ሆኖ የቀረበው ፡ የደቡብ
ኦሞ ዞን እራሱን ችሎ በክልል የመደራጀት ህገ መንግታዊ ጥያቄ በ2011 ዓ/ም ተቀብሎ በማፅደቅ ለክልሉ ም/ቤት በማቅረብ ምላሹ ያለበትን ደረጃ በመምከር የራሱን አቋም እንደሚገልጽ የምክር ቤቱ ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ናኪያ አናኩሲያ ተገልጿል፡፡

አክለውም በዚህ አስቸኳይ ጉባኤ ላይ የዞኑ ተወላጅ የሆኑና በደቡብ ክልል ደረጃ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች ና የምክር ቤት አባላት በጉባኤው ተሳታፊ እንደሚሆኑ ገልፀዋል፡፡

South Omo Zone Public Relation Office