የደርግ ጉዞ በተሃድሶ። ጦርነት መፍትሄ አይደለም።

የደርግ ጉዞ በተሃድሶ። ጦርነት መፍትሄ አይደለም።
 
ይህንን ከሥር የምትመለከቱትን ሚሊሻና የሰሞኑን የለብ፣ ለብ ሥልጠና የተመለከተ ካድሬና አንዳንድ የጨነቃቸዉ ካቢኔዎች ለአንድ ቀን እንቅልፍ ተኝተዉ ሊያድሩ ይችሉ ይሆናል። ደርግም በዉጥረቱ ዘመን ሲያደርግ የነበረዉ ይህንኑ ነበር። ኤርትሪያ ዉስጥ ገበሬዉ ራሱን በራሱ አከባቢዉን እንዲጠብቅ ተብሎ ካሰለጠኑት በኋላ መሣሪያ አስታጠቁት። ስሙንም ባልሳሳት (ገማግል??) የገበሬዎች ማህበር ምናምን ብለዉ ሰየሙት። ይህንንም ተቋም ጄ/ል ቁምላቸዉ ደጀኔ እንድመራዉ ተደረገ። ከዚያም ገበሬዉ መሣሪያዉን ከታጠቀ በኋላ እየወሰደ ለሻቢያ ማስረከብ ጀመረ።
 
እነዚህም ሚሊሻዎች ስለጦርነትና የጦር ሜዳ ሕግጋትን/Rule of Engagement/ROE/ስለማያዉቁ የተወሰኑ ያልታጠቁ ሰላማዊ ሰዎችን ሊገሉ ይችሉ ይሆናል። ያ መንግስትን ለባሰ ዉድቀት ይዳርገዋል እንጂ ምንም ለዉጥ አያመጣም። ስለዚህ ልቡ ሞቅ ያለ ካድሬ ካለ ተረጋጋ። ጦርነት መፍትሄ ስለማይሆን የሚበጀዉ ብሔራዊ እርቅ ብቻ ነዉ። የታሰረውን ፍቱ፣ መንግስትም ከሚዋጋዉ አካል ጋር ይነጋገር። እርቅ ፍጠሩ።