የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ሊሰጡት የነበረ መግለጫ ተሠረዘ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ሊሰጡት የነበረ መግለጫ ተሠረዘ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ዛሬ አዲስ አበባ
ታም ማሊኖውስኪ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ሊሰጡት የነበረ መግለጫ ተሠረዘ፡፡

ትናንት፣ ረቡዕ ታኅሣስ 5/2007 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የገባው በዴሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ታም ማሊኖውስኪ የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቡድን ዛሬ ረፋድ ላይ መግለጫ ሊሰጡ በዕቅድ ተይዞ እንደነበር ታውቋል፡፡ፕሮግራሙ ለምን እንደተሠረዘ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ መግለፅ አለመፈለጉን ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ሚስተር ማሊኖውስኪና የቡድናቸው አባላት በሰብዓዊ መብቶችና በአስተዳደር ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚነጋገሩ ተገልፆ ነበር፡፡

ይኸው በረዳት ሚኒስትር ማሊኖውስኪ የተመራ የሰብዓዊ መብቶች ቡድን በተጨማሪም ከሲቪል ማኅበረሰብና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተጠሪዎች ጋር ሊገናኝ በዕቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም ስብሰባዎቹ ይካሄዱ አይካሄዱ እንደማይታወቅም የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ መረጃ አክሎ ጠቁሟል፡፡

ቡድኑ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚቆየው እስከ ከነገ በስተያ፤ ቅዳሜ ታኅሣስ 8 እንደሚሆን ታውቋል፡፡