የዘረኞች እራሳቸው በድለው እራሳቸው ማልቀስ – የፈይሳ ሌሊሳ የቅርብ ገጠመኞች

የዘረኞች እራሳቸው በድለው እራሳቸው ማልቀስ – የፈይሳ ሌሊሳ የቅርብ ገጠመኞች

ፈይሳ ሌሊሳ ሀገሩ ሲገባ ኢትዮጵያ አልተዘጋጀችም:: ማይክራፎኖቹ ይመሰክራሉ:: ፈይሳ ሪዮ ኦሊምፒክ ላይ በግፍ አገዛዝ መንግስት አምፆ የህዝቡን ሰቆቃ ለአለም አሳወቀ::

የኢትዮጵያ ሚዲያዎች አዲስ አበባ ላይ በፈይሳ ላይ አምፀው ዘረኝነታቸውን ለአለም አሳወቁ:: ከኦሮሞ ሚዲያ ውጭ አንድም አልተገኘም:: እነዚህ የኦሮሞ ሚዲያዎች ባይኖሩ ኖሮ ፈይሳ ሌሊሳ ሀገሩ መግባቱም አይዘገብም ነበር:: ፈይሳ ከአፍሪካም ሆነ አለም በቢሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ገድሉን ተዘግቦ ያዩት ስለሆነ የሚዲያ ችግር የለበትም:: የፅሁፌ አትኩሮት ከዘገባው ውጪ ምንን ያሳዬል ለሚለው ነው::

የፈይሳ አይነት የስፖርትን መድረክ በህዝባቸው ውስጥ ያለን ሮሮ ለማጉላትና ለመታገል የተጠቀሙ ጀግኖች በአለም ታሪክ ስድስት ሰዎች ብቻ አሉ:: ቦክሰኛው መሀመድ አሊ, አትሌቶቹ ጆን ካርሎስ, ቶሚ ስሚዝ, ኳርተር ባክ ኮሊን ካፐርኒክ, ካቲ ፍሪማንና ፈይሳ ሌሊሳ ናቸው:: ከነሱ መሀል አንዱ የሆነው ፈይሳ ሚዲያውን ምን ያክል ዘረኛ እንደሆነ ቁልጭ አድርጏል!!

ለዶ/ር ብርሀኑ ነጋ የኢትዮጵያ ትርክት, ሲነግረን የነበረው የተለያዩ ድርጅቶች በዘር መቋቋም አስፈላጊነትን ይህ በግልፅ ያስቀምጣል:: ኦሮሞ ስለሆንክ በዘርህ ሚዲያ ስላንተ የማይዘግብ ከሆን, ባንኩ ካላበደረህ, ትምህርት ቤቱ መድልኦ ካደረገብህ ያለህ ምርጫ የራስህን ሚዲያ, ባንክ, ትምህርት ቤትና ሆስፒታል ከፍተህ ለህዝብህ አገልግሎት መስጠት ነው::

አሜሪካውያን ጥቁሮች የራሳቸው ትምህርት ቤትና ዩኒቨርሲቲዎች (HBCU – Historically Black Colleges and Universities / ታሪካዊ የጥቁሮች ኮሌጅና ዩኒቨርሲቲዎች), ሆስፒታሎችን, ባንኮችን, አብያተ ክርስቲያናትን ከፍተው እራሳቸውን ያገለግሉ ነበር:: አሁንም እያለገሉ ይገኛሉ:: ይህን ማድረጋቸው ደግሞ ሊቀጥራቸውም ሆነ ሊያገለግላቸው ከማይፈልግ የዘረኛ ስርአት ነፃ ሆነው የስራ ልምዳቸውን (work skills) ለማዳበር, የተቋማት ግንባታ ችሎታቸውን ለማሳደግ, አልፎም አብሮ የመስራትና ህብረታቸውን አፅንቶ ዘረኛውን የመንግስት ስርአት መለወጥ እንዲችሉ የአንበሳውን ድርሻ ተወጥቷል:: የተለያዩ አድማዎችን አድርገዋል:: መሪዎቻቸው ሲገደሉ ከተማዎችን በማቃጠል የዘረኛውን ስርአት አእምሮ, አይንና ጆሮውን ለነርሱ ጥያቄ ክፍት እንዲሆን አስገድደዋል::

ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ይህንን አይነግራችሁም:: አንድ በዛ ዘመን የነበረ ዘረኛ ነጭ ልክ እንደ ብርሀኑ ነጋ ይህን ታሪክ አይናገርም! ስለጠፋ ንብረት ግን ለቅሶ ተቀምጦ እዬዬ ብሎ ሲያለቅስ ታዩታላችሁ:: ኦሮሞዎች በዘር ለምን ተቋቅመው በለጡን ብሎ ያለቅሳል:: በስንት መከራ ኦሮሞዎች ያቋቋሙትን ተቋማት ለጥቃት እንዲጋለጡ ባደባባይ ያስዘምታል:: የአባቱ ሆቴሎች ብትሄዱ ከሰባት ቤት ጉራጌ ውጭ የሚሰራ ላታገኙ ሁላ ትችላላቹ::

በየእለቱ ኢትዮጵያዊነትን ሲግቱን የሚውሉ ፈይሳን ለመቀበል አልበቁም:: ከሰው የሚጠብቁትን ከራሳቸው ቅንጣት አያሳዩም::

ከኛ ግን እንደበግ እንኳን ሳንንፈራገጥ እንድንታረድ ይጠበቅብናል! ዘረኛን ዘረኝነቱን ካልነገሩት አያውቅም, መልሶ ሌሎችን ዘረኛ ይላል::
Via Danye Si’a