የወሎ ዩኒቨርሲቲ ገመናዎች : ከ6ቱ ሙስሊም ተማሪዎች እገታ እስከ 6 የኦሮሞ ተማሪዎች ግድያ!

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ገመናዎች : ከ6ቱ ሙስሊም ተማሪዎች እገታ እስከ 6 የኦሮሞ ተማሪዎች ግድያ

#ላለፈው 1 ወር ባደረግነው ጥናት የተገኘ መረጃ ስለሆነ አንበው ጽሁፉን ያጋሩልን።
#መረጃውን በማቅረብ ቁጥራቸው በርከት ያለ የወሎ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና ተማሪዎች ተሳተፍውበታል።

I. መግቢያ

ሰሞኑን በማህብራዊ ሚዲያው ከፍተኛ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ የወሎ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር አሉበት የሚባሉ ድክመቶች እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚመለከት ሆኖ ተስተዉሏል። ከግራም ከቀኝም የተለያዩ ሀሳቦች የተስተናገዱ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው በተያዘው የትምህርት ዓመት ከፍተኛ የሆነ የጸጥታ ችግር ከታየባቸው ግቢዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቅስ ከመሆቡ ጋር ተዳምሮ ጉዳዩን በቅርበት ገምግሞ የሚስተካከሉ ጉድለቶች ካሉ የሚስተካከሉበትን፣ ሊስተካከል የማይችል የአመራር ብልሹነት አለ ተብሎ ከታመነ ደግሞ አመራሩን በግዜ መቀየር እና ያለፉትን ችግሮችት (በተግባር የተፈጠሩ ችግሮች ሊሆኑ ይችላሉ ወይም በማህበረሰቡ ውስጥ ተፈጥረዋል ተብሎ የሚታመኑ ችግሮችም ብቻ ሊሆኑ ያችላሉ) በመሰረታዊንት ሊፈታ በሚችል አግባብ እንደገና ማዋቀር አስፈላጊ ይሆናል። በዚህ ረገድ ለሚመለከተው አካል መነሻ ሊሆን የሚችል መረጃ ዩኒቨርሲቲውን ለረጅም ግዜ ካገለገሉና እያገለገሉ ካሉ ሰዎች አጠናቅረን አቅርበናል።

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከ ዩኒቨርሲቲው ተልዕኮ አንጻር

በሀገራችንያሉ ዩንቨርሲቲዎች በመማር ማስተማር፣ ምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ላይ ተልእኮ ተቀብለው የተቋቋሙ ተቋማት ናቸው። ነገር ግን ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከተመሰረተ ጀምሮ ከነዚህ ተልኮዎች በተቃራኒ ቆሞ አንድ ድኬድ አሳልፏል። ዩኒቨርሲቲዎች ከተቋቁሙባቸው አንዱ አላማ የአካባቢውን ህዝብ እንድጠቅሙና እንድደግፉ ቢሆንም ወሎ ዩኒቨርሲቲ ግን የአካባቢውን ማህበረሰብ በተለያየ መልኩ በግልጽና በህቡእ ሲበድል ኑሯል ዛሬም እየበደለ ነው። የኒቨርሲቲው በአካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብና በዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ሙስሊሞች ላይ የሚያደረሰው በደል ተቋማዊ መልክ የያዘ ሆኖ አገኝተነዋል።

ምናልባት የሴት ተማሪዎችን እገታ በናይጀሪያ በቦከሃራም ይሆናል የሰማችሁት። ነገር ግን በሃገራችንም 6 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች በወሎ ዩኒቨርሲቲ ታግተው ነበር። ወላጅ ይማሩልኛል ብሎ ሴት ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲውንና መንግስትን አምኖ ወደ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ቢልክም ወሎ ዩኒቨርሲቲ ግን እነዚህ ምንም የማያቁ ሴት ተማሪዎችን ጅልባብ ለበሳችሁ በሚል ተልካሻ ምክናየት የማይታወቅ ቦታ አግቶ የተለያዩ የጾታና የማንነት ጥቃት ካስደረሰ በህዋላ መጨረሻም ወደ አድስ አበባ ማዕከላዊ እስር ቤት በለሊት እንደወሰዳቸው ይታወቃል። ይህ መቸም ድፍን ወሎ ብቻ ሳይሆን ድፍን ኢትዮጵያ ያወቀው ጸሃይ የሞቀው ሚስጢር ነው። ይህ ተቋም ከመጣው የመንግስት አካል ጋር በመለጠፍ የአካባቢውን ሙስሊም ማህበረሰብ እያሳደደና እየበደለ ነው። ተቋሙ የተገነባው ብዙ ሙስሊሞች ተፈናቅለው በገበሬ ማሳ ላይ ቢሆንም እነዚህ የአካባባቢው ተወላጆቸ በተለይ ሙስሊሞቹ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በጸሃፊነትና በጽዳት እንኳ አይቀጠሩም። መሬቱን ለዩኒቨርሲቲው መገንቢያ የተቀማው የአካባቢው ማህበረሰብ ሴት ልጆቹን አረብ ሀገር ሽጦ ነው እየተዳደረ እያለው። ዩኒቨርሲው የስራ እድል መፍጠር ቀርቶ ጽዳት እንኳ ከጎጃምና ከሳይንት እያመጣ ነው የሚቀጥረው። አንድ ወዳጄ የተዛበውን እንደነገረኝ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ሰው ሃይል ውስጥ የሚሰሩት ሰዎች የማህበረቅዱሳን አመራር ሲሆኑ ስማቸውም መምሬና ቄሴ ነው። በነገራችን ላይ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሙስሊም ከኮሌጅ ድንነት በላይ እንዳይሾም የወሎ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ቤተ ክርስቲያ ውስጥ ተስማምተው ወስነው የዩኒቨርሲቲው ”ያልተጸፈ ህግ“ ሁኗል። ባለፈው አመት ተባባሪ ፕሮፌሰር ሀሰን በሽርና (PhD) እና እረዳት ፕሮፌሰር ፋሲል ዋለልኝ በውድድር የምክትል ፕሬዝዳንትነትን (የጥናትና ምርምርና አየስተዳደር) ቦታ በሰፊ ልዩነት ቢያሸንፉም ባልተጻፈው ህግ መሰረት እንዳይሾሙ ተደርጓል። ምንም እንኳ ዩኒቨርሲቲው የሚገኝበት ደቡብ ወሎ ዞን ከ80% በላይ ሙስሊም ቢሆንም በዩኒቨርሲቲው ታሪክ ሙስሊም ፕሬዳንት ወይም ምክትል ም/ፕሬዛዳንት ሆኖ አያውቅም። ይህ የሆነው ሰው ጠፍቶ ሳይሆን በሴራ ነው።

የሃይማኖቱ አጀንዳ በተወሰነ ደረጃ መቀዛቀዝ አሳይቷል ብለው ያሰቡት የወሎ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች አጀንዳቸውን ወደ ብሄር አዙረው ባለፈው አመት ከ6 በላይ የኦሮሞ ተማሪዎችን አስገድለዋል። ጎንደርና ጎጃም ላይ እንኳ የኦሮሞ ተማሪዎች በሰላም እየተማሩ ወሎ ላይ ይህ መሆኑ ነገሩ በዩኒቨርሲው አመራር የተሰራ ሴራ መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው። በኦሮሞ ተማሪዎች የተካሄደውን ግድያ የመሩት ከጅማ ዩኒቨርሲቲ የሄደው ዶ/ር አያሌው ታለማና በእንግሊዘኛ ት/ት ክፍል መምህር የሆነው ዘላለም የሚባለው የአብን ሰው ናቸው። በጣም የሚያሳዝነው 6 የኦሮሞ ተማሪዎች ተገለው አስገዳዮቹ እነ አያሌው ታለማና ዘላለም መሆናቸው እስከ ፌደራል መንግስት ድረስ በይፋ እየታወቀ ጥፋተኛ ተብለው የተባሩት ግን የኦሮሞ ተማሪዎችና መምህራን ናቸው። የሙዚቃ ትምህርት ክፍል መምህር የነበረው ዩሃንስ (የወለጋ ልጅ እንደሆነ ሰምቻለሁ) ተማሪዎችን ወደ ከሚሴ አሸሽተሃል ተብሎ ነው የተባረረው። በጣም የሚያሳዝነው አቶ ዩሃንስ መባረሩ ሳይሆን በም/ፕሬዝዳንቱ በዶ/ር አማረ ምትኩ የተሰደበው ስድብ ነው። ዶ/ር አማረ ዩሃንስን “ጥንብ ጋላ” ምናባህ ታመጣለህ ብሎ ነበር የሰደበውና ከቢሮው ያባረረው። ይህንን መረጃ በሙዚቃ ት/ ት ክፍል መምህር ከነበረው ግለሰብ ማጣራት ትችላላችሁ። ዩሃንስ የወለጋ ልጅ ከመሆኑ ውጭ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ካባረረው በህዋላ የት እንዳለ መረጃው የለኝም። ዩሃንስ ብዙ ልጆች ስላሉት ስለሚሸገር በዚህ አጋጣሚ የኦርሞ ልጆች ያለበትን አጠያይቃችሁ እንድትረዱት በአክብሮት እጠይቃለሁ።

II. ወሎ ዩኒቨርሲቲ እና መማር ማስተማር

ቤቴ መጽሀፍት: አብዛኛዎቹ የወሎ ዩኒቨርሲቲ መምህራኖች ቤተ መጸሃፍት የት እንዳለ እንኳ አይቁትም። የወሎ ዩኒቨርሲቲ መምህራኖች በ Snow Ball Sampling ስነ ዘዴ መሰረት ተሰባስበው በዘመድ ስለሚገቡ የፖለቲካ አጃንድ ማራገብና፣ በጎጥና በሃይማኖት ተደራጅተው መባላት እንጅ የንባብ ባህል ጭራሽ የላቸውም። ላይብረሪም ለነሱ ምናቸውም አይደለም። አብዛኛዎቹ መምህራኖች ከሰርተፊኬትና ከድጎማ ተነስተው በርቀት ማስተርስና ፒ ኤች ዲ የያዙ ያለ ብቃት በዘመድና ባገር ልጅነት የተቀጠሩ ስለሆነ የማንበብም ሆነ የመመራመር ልምድም ብቃቱም ፍላጎቱም የላቸውም። የዩኒቨርሲቲው የድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች በአካል ዩኒቨርሲቲው ግቢ ቢገኙም ሲሰሩ የሚውሉት ግን የግል ስራቸውን ነው ። ለምሳሌ ያክል ጸሃፊዎቹ ሲጽፉ የሚውሉት የማህበረ ቅዱሳንንና የአብንን እቅድና ሪፖርት ነው። ጽፈው ፕሪንት የሚያደርጉትም እዛውዩኒቨረስቲው በዩኒቨርሲቲው ሃብት ነው። ህንጻዎችን በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው ያለው gtz የገነባቸው ህንጻዎች ብቻ ናቸው። አንድ የማኔጅመንት ህንጻ ተጀምሮ ይሄው 6 አመት በጀት ይወራረድበታል። አልፎ አልፎ አንዳንድ ትምህርት ክፍሎች አንድ የመምህራን ቢሮ ቢኖራቸውም አብዛኛዎቹ ት/ት ክፍሎች ግን አንድ ቢሮ ለሁለት ነው የሚጋሩት። ይህም ማለት አንድ ቢሮ ቢያንስ ለ30 መምህራን ማለት ነው ቢሮዎቹ ቢበዛ 4 ወንበር ነው ቢይዙ፥ ሬሾው 4/30 ማለት ነው ወይም አንድ ወንበር 9 ሰው ያስተናግዳል። ሌላው የዩኒቨርሲቲው ገመና የተማሪዎችን ድጋፍ በተመለከተ ነው። ዩኒቨርሲቲው ብዙ አይነ ስውራን ተማሪዎችን ቢቀበልም ብሬል እንኳ አልገዛላቻውም። አንድ የቋንቋ ተማሪ ብሬል ይገዛልኝ ብሎ ጠይቆ ተማርክ አልተማርክ ምን ለውጥ ልታመጣ “እውር” ብሎ አንድ ያረጀ የጃጀ መምህር እንደሰደበው የአንይ እማኞች አድርሰውኛል። ሌሎች ችግርተኛ ተማሪዎችን የወደቁበት የሚያያቸው የለም። ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለጋዜጠኛችና ለአክቲቪስቶች እየከፈለ ስሙን በበጎ አድራጎት ስራ ቢያስጠራም እውነታው ግን ዩኒቨርሲቲው ለራሱ ተማሪዎች እንኳ ምንም ማድረግ ያልቻለ የጡረተኞች መጠራቀሚያ ነው።

III. ወል ዩኒቨርሲቲ እና ምርምር

ምርምር ዩኒቨርሲቲው ከተሰጠው ግብ አንዱ ቢሆንም ወሎ ዩኒቨርሲቲ እስካሁን የረባ የምርምር ጆርናል እንኳ የለውም፥ ጆርናል ላይ የሚያሳትሙ መምህራን ቁጥርም እጅግ በጣም ዝቅተኛ ነው። ምንም እንኳ አካባቢው ብዙ ምርምር የሚሹ ነገሮች ቢኖሩትም ተቋሙ ግን እንደ እድር ዳኛ ነገር ከመንዳት በቀር የአንድ ትንሽ የበጎ አድራጎት ማህበር ያህል እንኳ ሚና የለውም። በሃገራችን ካሉት 50 የመንግስት ዩኒፈርሲቲዎች በወሬና በዜና ለመኖር አቅዶ እየሰራ ያለው ወሎ ዪኒቨርሲቲ ብቻ ነው። በየአመቱ የሚደረጉ የጥናት ኮንፈረንሶችም የአብን አጀንዳዎች መወያያና ማስረጫ ብሎም አበል መብያ ናቸው። አማራ አማራ አማራ ከማለት ውጭ መሬት ጠብ የሚል ጥናት አይቀርብም። ይህንን የታዘበው ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ባንድ ወቅት “ችግር ፈች ጥናቶች ላይ ከማቶከር ይልክ እንቶፈንቶ እሳቤዎችን ላይ ማተኮር ዩኒቨርሲቲውን ዋጋ ያስከፍለዋል“ ማለቱ ይታወሳል።

IV. ወሎ ዩኒቨርሲቲ እና የማህበረሰብ አገልግሎት

ዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት የሚለው ከትምርት ሚኒስተር ለዘርፉ ስራ ማስኬጃ የተመደችውን ብር ምንም ቫልዪ ሳይጨምርባት ወደ እነ አባተ አካውንት ከገባች በህዋላ 5% በማትሆን ነገር ሰደቃና ተስካር አብልተው በተለመደው መንገድ ጋዜጠኛ ገዝተው ማስጮህን ነው። ይህ ብዱን ከሰርቲፊኬት ተነስቶ በርቀት ትምርት (ከቅድስ ማርያም)ማስተር ገዝቶ እዚህ ደረሰ እንጅ ስለ ማህበራዊ አገልግሎትም ሆነ ስለ ምርምር የሚያርፈው ነገር የለም። ማህበራዊ አገልግሎት ማለት ግን ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያለውን ሃይል (የሰውና የገንዘብ) በመጠቀም ለአካባቢው ህዝብ ዘላቂ የሆነ ልማት መስራት ማለት ነው። ለምሳሌ ዘንድሮ በ2012፣ በ20 ሚሊየን ብር ተስካርና ሰደቃ ለአካባቢው ህዝብ አበላሁ ብሎ ከሚሳለቅና መሳቅያ ከሚሆን በዚህ ብር በትንሹ 5 ዘመናዊ ትምርት ቤት ለአካባቢው ህዝብ ይገነባ ነበር። ዘላቂ ልማት ማለት ይህ ነው።ለሰደቃና ተስካር ወጣ ከተባለው ከ20 ሚሊዮኑ ብር ቢያንስ 15 ሚሊዮኑ አመራሩ እንደተከፋፈለው ይሰመርበት፤

#ማጠቃለያ
ወሎ ዩኒቨርሲቲ በዙሪያው የሚኖረው የወሎ ህዝብ ለዘመናት ያካበተውን አብሮነት እና ተፋቅሮ የመኖር ባህል የማጎልበት ኋላፊነት ያለበት ተቋም እንደመሆኑ ተቋሙ በተለይ ደግሞ አመራሩ በራሱ ውስጥ ሀይማኖታዊ ቡድንተኝነት ሊስተዋል እንደማይገባ ለማንኛችንም ግልጽ ነው። ሀይማኖታዊ ቡድንተኝነት በተግባር መከሰትን ብቻ ሳይሆን የቡድንተኝነት ስሜቱ እንዳይፈጠር ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባዉም እሙን ነው። ከዚህ አንጻር የተቋሙን ሁኔታ ስንመረምር
 ከከፍተኛ አመራሩ ጀምሮ እስከ መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች ድረስ ለዚህ አላማ ያነጋገርኳቸው ሰዎች በሙሉ (ክርስቲያኖችም ሙስሊሞችም) በዩኒቨርሲቲው አይን ያወጣ ሀይማኖታዊ አሰላለፈ የተፈጠረ መሆኑን እና በዝውውር፣ በቅጥር፣ በሹመት፣ በጥቅማጥቅም፣ እንዲሁም ሆነ ብሎ አስከመጎዳዳት የደረሰ ብልሹ አሰራር መኖሩን አብነት እየጠቀሱ ነግረውኛል። “ከፍተኛ አመራሩ አቋም ይዞ ዩኒቨርሲቲውን ከሙስሊሞች ለማጽዳት እየሰራ ነው” የሚሉት ያናገርኳቸው ሁሉም የእስልምና ሀይማኖት ተከታይ ሰራተኞች “ተደረጉ” ያሏቸውን ለማመን የሚከብዱ በደሎች በብሶት ይናገራሉ። ከህግ እና መመሪያ ውጭ ሀይማኖትን መሰረት ያደረገ ሹም ሽር፣ ዛቻዎች፣ ስድቦች፣ ከስራ መባረሮች፣ የዝውውር ክልከላዎች፣ ነጥብ በነጥብ ያነሳሉ። ከዚህም ባለፈ “ወጣ ወጣ ይላሉ” የተባሉ መምህራንን ለማስገደል ጭምር ከፍተኛ አመራሩ ከተማው ውስጥ ካሉ ጽንፈኛ ቡድኖች ጋር አሲሮ እንደነበር፣ የድብደባ ሙከራ መደረጉን፣ በለት በለት ዛቻ እና ማስፈራሪያ ይመጣ እንደነበርም ተናግረዋል።
 የዩኒቨርሲቲው አመራር ከተማው ውስጥ ካሉ ጽንፈኛ ብድኖች ጋር በመመሳጠር ከሌላ አካባቢ ለስራ በሚል ሰበብ ያመጣቸውን በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በሀይማኖት በማደራጀት ቀን ቀን በየመንገዱ ላይ የኮንትሮባንድ ንግድ ጨምሮ ሌሎች ስራዎችን ያለማንም ከልካይ እንዲሰሩ፣ አስፈላጊ በሆነ ሰዓት እና በምሽት ደግሞ የአመራሩን አና የአክራሪ ቡድኑን አንቅስቃሴ ይቃወማሉ ያሏቸዉን ግለሰቦች በማስፈራራት፣ በመደብደብ አና በመግደል ተግባር ላይ ጭምር እንዲሳተፉ አድርገዋል። የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር ባለፈው ዓመት በደሴ ካምፓስ የሞቱትን የኦሮሚያ ተማሪዎች በሙሉ ያስገደለው
 ከጅምሩ ጀምሮ ፀረ፟ሙስሊም አቋም ያለው፣ ሴት ተማሪዎቹን ያሳፈነ።
 ከከፍተኛ አመራሩ ውስጥ ብቃትም ልምድም ያላቸው ሰዎች ባሉበት ሁኔታ በምክክር ሙስሊሞች እናዳይገቡ የተሰራዊ ሴራ
 በወለድ እና አልኮል ተሳቦ ዩኒቨርሲቲው ከመምህራን ጋር አብሮ ለመስራት ባሰበው ኩባኛ አጀንዳ ተይዞ ተመክሮበት ሙስሊሞቹ እንዳይገቡ ያደረገ
 በፖለቲካው ስንመጣ ዩኒቨርሲቲው ከለውጡ በፊት የህዋሃት የግል ንብረት የነበረ ሲሆን ከለውጡ ብህዋላ ደግሞ አብን ባለቤትነቱን ሙሉ በሙሉ ወስዶ ተቋሙ የአብን ካድሬዎች መፈንጫ ሁኗል።
የአብን አመራሮችና አባላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ህግን በመጣስ ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ይቀጠራሉ። የአብን ም/ሊቀመንበር የሱፍ ኢብራሂም ከዚህ ቀደም ወሎ ዩኒቨርሲቲ በኩንትራት በሚሰራበት ወቅት በሰራቸው ተዳጋጋሚ የህግ ጥሰቶች ከዩኒቨርሲቲው ተባሮ ነበር። ነገር ግን ይህ ግለሰብ አንድም የተባረረን ሰው ሁለትም የመጀመርያ ድግሪ ውጤቱ CGPA 2 . 26 ( ሊኖረው የሚገባው ነበር3.00) ሆኖ ሳለ በህገወጥ መንገድ ተቀጥራል። በህግ የሚጠይቅ አካል ካለ ይህ ሙሉ መረጃ በጃችን አለ።

 ሌላው ተመልሼ የምመጣበት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ሜቲክ የላኮመንዛን ጉዳይ ነው። ላኮመንዛ በተባለው ድርጅት ሰበብ ከግማሽ በላይ የሚሆነው የወሎ ዩኒቨርሲቲ በጀት እንደት ወደ እነ ዶ/ር አባተ ኪስ እንደሚገባ እመለስበታለሁ።

Abebe Hagos