የኮንፌዴሬት መሪዎች እና የዓለም አሳሹ ክሪስቶፈር ኮለምበስ ሃውልቶች በተቃዋሚዎች ፈረሱ።

የኮንፌዴሬት መሪዎች እና የዓለም አሳሹ ክሪስቶፈር ኮለምበስ ሃውልቶች በተቃዋሚዎች ፈረሱ።

ከጆርክ ፍሎይድ ግድያ በኋላ በመላው ዓለም የተቀጣጠለው የታቀውሞ ሰልፍ ከቅኝ ገዢ እና ከባርነት ጋር ቁርኝት ያላቸው ሃውልቶች ለተቃውሞ በወጡ ሰዎች ሲፈርሱ ቆይተዋል።

በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ሪችመንድ ከተማ ቆሞ የነበረው የኮንፌዴሬት ፕሬዝደንት ጄፈርሰን ዴቪስ ሃውልት በተቃዋሚዎች ትናንት ምሽት ፈርሷል።


ተቃዋሚዎች በአሜሪካ የኮለምበስ እና ኮንፌዴሬት ሃውልቶችን አፈረሱ

(bbc)-የኮንፌዴሬት መሪዎች እና የዓለም አሳሹ ክሪስቶፈር ኮለምበስ ሃውልቶች በተቃዋሚዎች ፈረሱ።

ከጆርክ ፍሎይድ ግድያ በኋላ በመላው ዓለም የተቀጣጠለው የታቀውሞ ሰልፍ ከቅኝ ገዢ እና ከባርነት ጋር ቁርኝት ያላቸው ሃውልቶች ለተቃውሞ በወጡ ሰዎች ሲፈርሱ ቆይተዋል።

በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ሪችመንድ ከተማ ቆሞ የነበረው የኮንፌዴሬት ፕሬዝደንት ጄፈርሰን ዴቪስ ሃውልት በተቃዋሚዎች ትናንት ምሽት ፈርሷል።

‘ኮንፌዴሪሲ’ ተብሎ የሚጠራው ቡድን በደቡብ አሜሪካ በሚገኙ ግዛቶች ጥቁሮች በባርነት እንዲቆዩ ታግለዋል።

ከዛ ከቀደም ብሎ በሪችመንድ የዓለም አሳሹ ክርስቶፈር ኮለምበስ ሃውልት ተጎትቶ ከወደቀ በኋላ እሳት ተለኩሶበት በመጨረሻም ወደ ኃይቅ ውስጥ ተጥሏል። በሚኒሶታ የነበረው ሶስት ሜትር ይረዝም የነበረው የኮለምበስ ሃውልትም እንዲፈርስ ተደርጓል። በተመሳሳይ በቦስተን፣ ማሳቹሴት እና ፍሎሪዳ የኮሎምበስ ሃውልቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል። በቦስተን የነበረው ሃውልት አንገቱ ተቆርጧል።

በአሜሪካ በርካታ ሰዎች የኮለምበስን ዓለም አሳሽነት እንደ ‘ገድል’ ሲያስታውሱት ኖረዋል። በትምህርት ቤት መጻሕፍቶች ውስጥም በ15ኛው ክፍለ ዘመን “አዲሷን ዓለም” አገኘ እየተባለ አሜሪካን ስለማግኘቱ ይወደሳል።

ቀደምት የአሜሪካ ነዋሪዎች ግን ኮለምበስ በዚህ ሊመሰገን አይገባም ባይ ናቸው። ኮለምበስ ወደ አሜሪካ መምጣቱ ቅኝ ግዛትን አስፋፍቷል፤ በነባራ ነዋሪዎች ላይም የዘር ጭፍጨፋ ተፈጽሟል ይላሉ።

(BLM – Black Lives Matter) የሚል ጽሑፍ በማያሚ በሚገኘው የኮሎምበስ ሃውልት ላይ ተጽፏል

ከቅኝ ገዢ ወይም ከባርነት ጋር ቁርኘነት አላቸው የሚባሉ ግለሰቦችን ወይም ቡድኖችን የሚወክሉ ሃውልቶች ይወገዱ ሲሉ ድጋፋቸውን የሰጡ የአሜሪካ ባለስልጣናት አልታጡም።

ለምሳሌ ባሳለፍነው ሳምንት የቨርጂኒያ ግዛት ገዢ የኮንፌደሬት ጀነራል ሮበርት ሊ ሃውልት ከሪችመንድ ከተማ ይነሳል ብለው ነበር። ፕሬዝደንት ትራምፕ ግን፤ እኚህ ግለሰቦች እና ቡድኖች የአሜሪካ ታሪክ አካል ናቸው በማለት ሃውልቶቹ መፍረስ ላይ እንደማይስማሙ ጠቁመዋል።

መሰል ሃውልቶችን የማፍረስ እንቅስቃሴ በአሜሪካ ብቻ ሳይሆን በዩናይትድ ኪንግደምም ተስተውለዋል። በሳለፍነው እሁድ በእንግሊዝ ብሪስትል ከተማ የባሪያ ንግድ ላይ ተሰማርቶ ነበረውን የኤድዋርድ ኮልስቶን ሃውልት ፈርሷል። ከዛ ሃይቅ ውስጥ ተጥሏል።

ነጩ የፖሊስ መኮንን ጥቁር አሜሪካዊን በጉልበቱ አንገቱ ላይ ቆሞ ሲያሰቃየው ከቆየ በኋላ መተንፈስ አቅቶት ተዝለፍልፎ፤ ከዚያም የጥቁር አሜሪካዊው ሞት በአሜሪካ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ቁጣን ቀስቅሷል። በርካታ የዓለማችን ከተሞችም የተቃውሞ ሰልፎችን እያስተናገዱ ነው።

ሟቹ የ46 ዓመት ጎልማሳ ጥቁር አሜረካዊ ጆርጅ ፍሎይድ የቀብር ስነ-ስርዓቱ ትናንት ተፈጽሟል።

1 Comment

  1. BBC has published similar legacy of abyssinia’s menelik II in Oromia (DRO) and Belgium’s leopold II in Congo (DRC). I hardly see their difference. But Belgium removed leopold’s statue while abyssinia refurbish menelik’s statue. At least two reasons for this. 1) We Oromos are still under abyssinian colonial rule. 2) The current abyssinians embrace despotism like their forefathers while Belgians do not. Bring down menelik and his heir colonel abiy! https://www.bbc.com/news/world-europe-53017188

Comments are closed.