የኮሎኔል አብይ አህመድ የተስፋ መቁረጥ የክተት ጥሪ!!

የኮሎኔል አብይ አህመድ የተስፋ መቁረጥ የክተት ጥሪ!!

ደሴ ሰዓት እላፊ ታዉጇል፣ ከምሽቱ 2.00 ሰዓት በኋላ ንቅንቅ የለም፣ ደብረ ታቦርና ባሕር ዳር በድንጋጤ እየታመሱ ናቸዉ አቶ አገኘሁ ተሻገርና ግብረ አበሮቻቸዉ በዚህ ሁኔታ ተሸብረዉ ተደጋጋሚ ክተት መጥራት ስላልቻሉ ኮሎኔል አብይ አህመድ፣ ሽመልስ አብዲስና ተመስገን ጥሩነህ ከፍንፊኔ አሁን ክተት የመጥራቱን ሥራ ተያይዘዉታል፤ ፍንፊኔም ብዙ ትርምስ አለ ይባላል፣ የጤፍ፣ የዘይት፣ የሽንኩርት፣ የስኳር፣ የጨዉ ወዘተ. ገበያ ደርቷል ሰልፍ ነዉ ይባላል።
ኮሎኔል መንግሥቱ ሃይለማያም ያኔ በስዉር ሊፈረጥጡ 3 ሳምንታት ሲቀራቸዉ በመንግሥት ሚዲያዎች የሻዕቢያና የወያኔ ወንበዴዎችን ብዙ ረገሙ፣ አስረገሙ፣ የፈረደባቸዉን የፍንፊኔ ኗሪዎች በግዳጅ በየሳምንቱ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዉ እንዲኮንኑ ትዕዛዝ አስተላለፉ፣ ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ ሆነና የፍንፊኔ አካባቢ ኗሪዎችን አስታጠቁ፣ ።”ወንበዴዎች” ብዙ ተረገሙ! ተኮነኑ! ግና ትጥቁም ያዉ ማገዶ ሆኖ ቀረ፤ ኮሎኔሉም በዚህ መሃል ነበር ማንም ሳይሰማ ያ ሲከሱትና ሲረግሙት የነበረዉ የአሜሪካ መንግሥት ወደ ዝምባብዌ የጫናቸዉ አሁንስ ምን ይከተል ይሆን?
የተረገዘዉ 9 ወር በላይ ከደረሰ ያልተጠበቀ አደጋ ካላጋጠመ መወለዱ አይቀርም