የኮሎኔል አብይ አህመድ መጨረሻ ስሎቮዳን ሚሎሶቪችን ወይስ ሙአመር ጋዳፊን መቀላቀል???

የኮሎኔል አብይ አህመድ መጨረሻ ስሎቮዳን ሚሎሶቪችን ወይስ ሙአመር ጋዳፊን መቀላቀል???

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በምዕራቡ አጋር ኃይሎችና በቀድሞዋ ሶቪዬት ህብረት ድጋፍ አሸናፊ ሆኖ የወጣው የጆሲፕ ብሮዝ ቲቶ ቡድን በወቅቱ የነበረውን የንግስና ሥርዓት በማስወገድ ስድስት ሪፑብሊኮች (የቦስንያ ሄርዘጎቪና ፣ ክሮአት ፣ ሰርብ ፣ ማሴዶንያ ፣ ሞንቴኔግሮ እና የስሎቬንያ ሶሻሊስት ሪፑብሊክ ) እና ሁለት በሰርብ ሶሻሊስት ሪፑብሊክ ውስጥ የታቀፉ የራስ ገዝ ክልሎች (ቮጅቮዲና እና ኮሶቮ )ያላት ፈደራላዊት ሶሻሊስት ዩጎዝላቪያን መሰረተ::
.
ይሁን እንጂ በዩጎዝላቪያ በሶሻሊስት መርሆ ላይ የተመሰረተው ፈደራላዊ አስተዳደር የይስሙላ እና ወደ ተማከለ አሀዳዊ ስርአት ያደላ ነበር። ሶሻሊስታዊዉ የፌደራል ስርዓት የተማከለ አሰራር ይህንን መከተሉ ደግሞ ቀደም ሲል በንጉሳዊቷ ስርአት በነበራቸው ተፅዕኖ dominant ስፍራ ምክንያት የተመቻቸው በሁሉም ክልሎች ውስጥ ይኖሩ ለነበሩ የሰርብ ልሂቃኖች ብቻ ነበሩ።
የይስሙላው የፌደራሉ ስርአት መርህስርአት በትክክል ያለመተግበር ደግሞ በሂደት የሌሎችን ብሄር ብሄረሰቦች ተስፋና ፍላጎት ለማሳካት ስላልቻለ ከግዜ ቦሀላ ተግዳሮቶች ተደቀኑበት::
.
የቲቶ መንግስት አገሪቱን የተጋፈጣትን ችግር ለመፍታት የተዘረጋውን የይስሙላ ፈደራሊዝም ወደ እውነተኛ የፌደራል አስተዳደር ማሸጋገር ግድ መሆኑን ተገነዘበ :: አዲሱንም ሥርዓት በሕግ መሰረት ላይ ለማቆም በማለም በ 1974 ለስድስቱ ሪፑብልኮች እና በሰርብ ሪፐብሊክ ስር ታቅፈው ለነበሩት ሁለት ልዩ ክልሎች የራስን በራስ ማስተዳደር መብት ያጎናፀፈ ህገ መንግስት አጸደቀ ።
.
ሕገ መንግስቱም በሰርብ ሪፑብሊክ ውስጥ የተካተቱት ቮጅቮዲን እና ኮሶቮ በፓርላማ ድምፅ እንዲኖራቸው ስላደረገ የሰርብ ሪፑብሊክ በሁለቱ ክልሎች ላይ የነበራት ተጽዕኖ እጅጉን ቀነሰ::
ይህ መሆኑ ግን ያስቆጣቸውም ነበሩ።በዩጎዝላቪያ ውስጥ የነበራቸውን የላቀ ተፅዕኖ እንዲሸረሸር ያደረገባቸው እና ከወገኖቻቸው ጋር በእኩልነት መኖርን እንደ መበለጥ የተመለከቱት የሰርብ ልሂቃን ሪፑብልኮች ራሳቸውን በራሳቸው የማስተሳደር ስልጣን በመስጠት “የበላይነታችንን ያሳጣናል” በማለት ህገ መንግስቱን ላለመቀበል ወሰኑ።
ለዚህ ተግባራቸው ደግሞ መሪ ተደርጎ የወጣው ሰው
በጥንታዊቷ ገናና ሰርብ ትርክት በእብሪት የተሞላው
ስሎቮዳን ሚሎሶቪች ነበር።
 
ስሎቮዳን ሚሎሶቪችና ተከታዮቹ በዩጎዝላቪያ ውስጥ የነበራቸዉን ስፍራ እንዲሸረሸር ምክንያት የሆነው የ 1974 ቱ ህገ መንግስት እንደሆነ ጽኑ እምነት ስለነበራቸው የሕጉን ዋነኛ ውጤት የሆነዉን ራስን በራስ ማስተዳደርን ለመቀልበስ የሚቻላቸውን ሁሉ ማድርግ እንዳለባቸው ወስነው እንቅስቃሴ ጀመሩ።
እነዚህ ብሄርተኛ ሰርቦች ከራሳቸው ውጭ ያሉትን ብሄሮች በሙሉ በሚባል መልኩ መተንኮስና ማጥቃት ሲጀምሩ አላማቸውም አንድና አንድ ነበረ ” ገናና እና የእነሱን የበላይነት የምታስቀልጥል የተማከለች እና አሃዳዊት ዩጎዝላቪያን የመመለስ እንቅስቃሴ ።
የSerbia አሀዳዊ ጽንፈኞች ዛሬ እኛ ሀገር ውስጥ ሁሉን ተናካሽ እንደሆነው አካል ሁሉ ዩጎዝላቪያ ውስጥ የነበሩ ብሄር ብሄረሰቦችን ፈጽሞ ማየት አይፈልጉም ነበር። የሀገሪቱ የጀርባ አጥንት ፣ መከታ ፣ ብቸኛ ተቆርቌሪ ወዘተ አድርገው እራሳቸውን በመሳል በቀድሞዋ በንጉሳዊቷ ዩጎዝላቪያ የነበራቸዉን የበላይነት መልሰው የሚያገኙበትን የስነ ልቦና ሁኔታ ለማመቻቸት በስፋት ሰሩ።
 
በፌዴራል መስሪያ ቤቶች ህዝባዊነትን ከመመስረት ይልቅ የሰርቦች ጀግነት እና ሃገር ፈጣሪነት እንዲለፈፍላቸው ብቻ ሲሰሩ ከኦርቶዶክስ እምነት ውጪ፣ የሌላውን እምነት እና ብሄር እንደ እኩል መቀበል አልቻሉም።በዩጎዝላቪያ ኦሮቶዶክስ ቤተክርስትያን እና የመንግስት መዋቅር ውስጥ በነበራቸው የበላይነትም፣ በየክፍለሃገሩ እየዞሩ፣ ሀገር ያቀናሁ ሀገር የመሰረትኩ፣ እኔ ነኝ በማለት ይሸልሉ ነበር። ዛሬ በእኛ ሀገር እንደሚፈጸመው እና እጅግ በሚመሳሰል ሁኔታ ብሄር የሚባል ነገር የለም እያሉ፣ በሄዱበት ቦታ ሁሉ በቁጥር አናሳ ሆነው ሳለ፣ እንደ እንግዳ የተቀበላቸውን እና ሄደው የሰፈሩበት፣ ማህበረሰብ የነሱን ቋንቋ እና እምነት ብቻ እንዲከተል ያስገድዱት ነበር።
 
በሌሎች ሪፑብሊኮች የሚኖሩ ሰርቦች የፈደራል ስርአትን አምርረዉ በማውገዝ አሃዳዊ ስርአትን ለመመለስ የሚደረገዉን እንቅስቃሴ እንዲቀላቀሉ አደገኛ የሆኑ ሴራዎች ቀን ከሌት መስራት ጀመሩ።ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳጋጠመን ሁሉ በተለያዩ ሪፑብሊኮች ውስጥ የሚኖሩ ሰርቦችን ውጥረት ውስጥ እንዲሆኑ ፣ ግጭቶች እንዲፈጠሩ በማድረግ ከዚያም እነርሱ መከታዎቻቸው ሆነው በመቅረብ በሰርብ ሪፑብሊክ ዉስጥ ያላቸዉን ተቀባይነት ማጠናከር እና በሰርቦች ቁጥጥር ስር የነበረዉን የዩጎዝላቪያን ሚዲያ በመጠቀም የተዛቡ መረጃዎችን በማቅረብ በተቃርኖ በተሞሉ ትርክቶች ግጭቶችን ማባባስ ተያያዙ።
ክርዋቶችን ፣ እስሎቨኖችን ፣ ማሰዶኖዊያንን፣ የቦስኒያን ሙስሊሞች እና የኮሶቮ አልባኒያን ህዝቦች ማንነት በተቀናበረ ፕሮፖጋንዳ በማጠልሸትና በማሸማቀቅ ለህገ መንግስቱ ከመቆም እንዲያፈገፍጉ ሲያደርጉ የተለያዩ ስያሜዎችን በመስጠት እና ውንጀላዎችን በመደደር ማንነታቸዉን በማጠልሸት ከሌሎች የመነጠል ሥራ በስፋት ሰሩ ::
 
የሀገሪቱን የገንዘብ እንቅስቃሴን ጭምር ተቆጣጥረውት ስለ ነበረ ሀገሪቱ በኢኮኖሚ እንዳትረጋጋ የተለያየ ሴራዎችን በመሸረብ ህዝቡ እንዲማረር ካደረጉ ቦሀላ መፍትሄው እነርሱ ብቻ መሆናቸውን ለፈፉ።
ክሮአቶች ላይ በመዝመት መቶ ሺዎችን ጨፈጨፉ። ቤተ ክርስትያንን እንደ መሳሪያ ግምጃ ቤት እየተጠቀሙ፣ የኮሶቮ እና አልባኒያ ብሄሮችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገደሉ ፣ሙስሊሞችን በማጎርያ ካምፕ በማጎር ብዙህ ሺዎችን ገደሉ።
 
በመጨረሻ ግን ሁሉም ብሄር ብሄረሰብ ጠላቸው። አለምም ዘመተባቸው።NATO በጀት ደበደባት። በትእቢት የተገሰለው መሪያቸው ስሎቮዳን ሚሎሶቪችም ሞቱን በእስር እንዲሆን ተበየነ።
በዚህ መልክ በፌደራል ሥርዓት ስር ከወገኖቻቸው ጋር በእኩልነት መኖር ያልተመቻቸው አክራሪ ሰርቦች በአንድነት ስም የጥንቷን የሰርብ የበላይነት የሰፈነባት አሃዳዊ አስተዳደር ያላት ዩጎዝላቭያን ለመመለስ ያደረጉት እንቅስቃሴ እነሱ በሚመኟት ሰርብ አምሳል የተገነባች አንድ ዩጎዝልቪያን ሳይሆን ሰባት ነጻ መንግስታቶችን አዋለደ ።

Gumaa Saaqqataa


Kana booda eenyuu fi iyyuu wanti irra darbamu hin jiru.
konkolaataan dhagaa fi cirracha dhiisee yoo waraana fe’e gatiin isaa kana fakkaata.
yoo qabeenya kee barbaadde dirqama sitti kennamu sana didi.

This criminal against humanity soon face justice either at ICC OR on #gaddihaffi style, BUT what is the Ertrean fate as a poor and old aged nation in the Horn of Africa?. Eritreans fought a bitter war for more than 30 years for their liberation having strong support from both #Oromos and #Tegarus . Today, 30 years later , the Eritrean army considered worse than the #NAZI ARMY engaged on #GENOCIDE war against #TEGARU and #Oromos that badly damaged the reputation of Ertreans as a whole a people without moral and integrity. The future will tell us with whom they will have a cordial relationship in the Horn having acted as A #NaziArmy at 21century . We #NeverForGet