የክልሎች ልዪ ሀይል ወደ ወለቃይት እየተላከ ነው; እባካችሁ ጦርነት, ሞት, ስደት ይብቃ !

የክልሎች ልዪ ሀይል ወደ ወለቃይት እየተላከ ነው; እባካችሁ ጦርነት, ሞት, ስደት ይብቃ !

ህግ ያለበት ሀገር ቢሆን; ወልቃይት ላይ እየተደረገ ባለው ፍልሚያ እንኳንስ የክልሎችን ልዪ ሃይል ይቅርና የሀገር መከላከያ ስራዊትም በሁለት ክልሎች መካካል በሚነሳው የድንበር ይገባኛል ጥያቄ, አንዱን ክልል ወግኖ ጦርነትን ከሌላው ጋር አይገጥምም:: በወልቃት እየተደረገ ባለው ግጭት ልዪ ሃይልን ከኦሮሚያ, ከሲዳማ, ከሶማሌ እና ከሌሎችም ክልሎች ለመላክ እየተዘጋጃችሁ ያላችሁ የመንግስት ሃላፍዎች ከተጠያቂነት አታመልጡም:: በየክልሉ ይህንን ጉዳይ እየተቃወማችሁ ያላችሁ ባለስልጣን ደግሞ ድምፅችሁን የበለጠ ማስማት እና ለሞት እየተጋበዙ ያሉትን ወጣቶች መታደግ አለባችሁ:: መከላከያ ሊያቆመው ያልቻለውን TDF ልዪ ሃይል ፍፀሞ ሊያቆመው አይችልም:: ከሁሉ በላይ ደግሞ ይህ ጉዳይ በእናንተ jurisdictions ስር ያለ ጉዳይ አይደል:: አይመለከታችሁም::
 
የድንበር ይገባኛል ጥያቄ የሚፍታበት የራሱ የሆነ የህግ አግባብ አለው:: በደቡብ ክልል እና በኦሮሚያ መካከል; በኦሮሚያ እና ሶማሊያ ክልል መካካል ተመሳሳይ ችግሮች በፍደሬሸን ምክርቤት እና በህዝብ መርጫ ተፍተዋል:: ዛሬም ቢሆን ይህ ችግር በዚያው መልኩ ነው መፍትሄ ማግኘት ያለበት:: የወልቃይት ጉዳይ “የሀገር ደህንነት” ጉዳይ ነው እያሉ ህዝቡን ለማወናበድ የሚፍልጉ ስዎች; ዘመኑ የተክኖሎጂ እና የኢንፎርሜሽን መሆኑን የዘነጉ ናችው:: ህዝቡ በቂ እውቀትን ከተለየ ሚድያ እንደሚያገኝ የረሱ እና ልክ እንደ ድሮ ተነድቶ የሚሄድ ህዝብ ያለ ነው የሚመስላቸው:: የወልቃይት ጉዳይ እንኳንስ ለኢትዮጵያ ለአማራም የደህንነት ጉዳይ ሊሆን አይችልም:: ስለዚህ ወጣቱን ለማይረባ ጦርነት መስዋዕት አታድርጉት:: በሃይል የያዛችሁትን መሬት ሊቀቁ:: ከዚያ በህጋዊ መንገድ ህዝቡ በየትኛው ክልል መካለል እንደሚፍልግ በህዝበ ውሳኔ referendum ይወስን::ጦርነት ሞት ስደት ይብቃ::
እግዚአብሔር ህዝቡን ይባርክ::
ቄስ ተመስገን

Via: Temesgen Mengesha Dabsu