የኪነ ጥበብ ምሽት ብለው በብሄራዊ ቴአትር የሚያደርጉት ዝግጅት ሁሌ ተመሳሳይ የፖለቲካ አስተሳሰቦች የሚቀነቀኑበት መድረክ ነው

የኪነ ጥበብ ምሽት ብለው በብሄራዊ ቴአትር የሚያደርጉት ዝግጅት ሁሌ ተመሳሳይ የፖለቲካ አስተሳሰቦች የሚቀነቀኑበት መድረክ ነው

SOURCE: THE FINFINNE INTERCEPT


የኪነ ጥበብ ምሽት ብለው በብሄራዊ ቴአትር የሚያደርጉት ዝግጅት ሁሌ ተመሳሳይ የፖለቲካ አስተሳሰቦች የሚቀነቀኑበት መድረክ ነው። የኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ምሽት ይበሉት እንጂ በዋናነት እነ #ዳንኤል_ክብረት የሚፈልጉትን ሰው እየጋበዙ ያቺኑ የተለመደች ያንድ ወገን ትርክት ሰዉን የሚግቱበት ምሽት ነው። ከዚህ በፊት የተካሄደው ላይ ጠ/ሚ አብይ ተገኝቶ እንደነበር ይታወሳል።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ከቀረቡት ንግግሮች አንዱ ሰርፀፍሬ ስብሃት ያቀረበው ይህ ንግግር ነው። ሰርፀ ስለ አዲስ አበባ አንስቶ “ቀጭኔ የሚጋልብበት ጫካ ነበር። ገበሬም አልነበረም። ቦታ ልቀቅ የተባለም ሰው የለም ” ብሎ ይሞግታል። አዲስ አበባ ገበሬዎችን እያፈናቀለች የተገነባች ከተማ መሆኗን ለማወቅ ወደ ኋላ ሄዶ የቱለማን (የገላን ፥ ኤካ ፥ ጉለሌ ፥ ሜታ ፥ አቢቹን ወዘተ) ታሪክ ማጥናቱ እንኳን ቢቀር ዛሬ ወደ ከተማዋ የተጠቃለሉትን የፊንፊኔ ዙሪያ አካባቢዎች ሄዶ ማየት ይበቃው ነበር። አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም ሆኖበት እንጂ። ያልኖረበትን ዘመን ለሱ በሚስማማው መልኩ ይተነትንና መልሶ “ያልኖርንበትን ዘመን ታሪክ የት መቼ እንዴት እያልን መጨቃጨቅ አይጠቅመንም” ይላል።

ከተማ ብዙ ህዝቦች ያላቸውን አዋጥተው የሚመሰርቱት ቦታ ነው ይላል። በመርህ ደረጃ ይሄ ልክ ሊሆን ይችላል። ግን እስኪ ስለ አዲስ አበባና ስለ ኪነ-ጥበብ ብቻ እንኳን እናንሳ። እንደዛ ከሆነ የኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ምሽት ተብሎ ተመሳሳይ ሰዎች በተመሳሳይ ቋንቋ በየወሩ እየመጡ ሰበካ የሚያቀርቡት ለምንድን ነው? መቼ ነው የሲዳማ ግጥም፤ የሶማሊ አጭር መጣጥፍ፤ የወላይታ አጭር ተውኔት፤ የቤኒሻንጉሉ የታሪክ አረዳድ፤ የጋምቤላው ጭውውት ከነ ቋንቋውና ለዛው ቀርቦ የሚያውቀው? ሌላው ቢቀር እዛው አፍንጫቸው ስር ያለውን ታዋቂ የአፋን ኦሮሞ ገጣሚ #ለታ_ቀነኢን እስኪ በዚህ የኪነጥበብ ምሽት አንድ ግጥም አቅርብልን ብለው ያውቃሉ? የፖለቲካ አቋሙ ምንም ይሁን ምን። ያው የኢትዮጵያ የጥበብ ምሽት ስለሚሉት ብዬ ነው።

በእነሱ እይታ ብቻ የኢትዮጵያ አመሰራረትና የነገስታቱ ገድልም ይሆን ስህተት ከሚቀርብ እስኪ የሀመሩ ወይም የኮንሶው ወጣት ምን አይነት አረዳድ አለው ብለው ለመስማት ሞክረው ያውቃሉ? ሰርፀፍሬ የሱ ማንነት ቋንቋና የታሪክ አረዳድ ብቻ የሚንፀባረቅባትን ከተማ የሁሉም እንደሆነች አድርጎ ሊሸጥልን ይሞክራል። ፕሪቪሌጅ ብዙ ጊዜ ፕሪቪሌጁ ላለው ሰው አይታየውም ይባላል።

የነ ሰርፀ የኪነጥበብ ምሽት ላይ የቋንቋ inconveniece ስለሚኖር ነው ሌሎች ያልተጋበዙት እንኳን እንበል። በከተማዋ ባጠቃላይ እነዚህ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች የኪነ ጥበብ ዝግጅት የሚያቀርቡበት መድረክ አለ? ነው ወይስ በነሱ ቋንቋ ቅኔ የለም አባባል የለም ግጥም የለም ጭውውት የለም ታሪክ የለም ውዘተ። የአገሪቱ ቁጥር አንድ የሆነው ህዝብ እንኳን እዚች ከተማ ላይ ደህና ባህላዊ ምግብ ቤት (Kaku Mame) ካገኘ አመት ቢሆነው ነው። የትእግስት ወይሶ የወላይታ ምግብ ቤትም ከተከፈተ ጥቂት ወራት ቢሆነው ነው። ከአዲስ አበባ ይልቅ አንዳንድ የአሜሪካና የአውሮፓ ከተሞች ላይ በቁጥር የበለጡ ለምሳሌ የኦሮሞ ምግብ ቤቶች አሉ። ለሰርፀ ግን እሱ የሚፈልገውን እስካገኘ ድረስ ይሄ ጉዳዪ አይደለም።

ቀጥሎ ደግሞ ዱላ ይዘው ወጥተው የመብት ጥያቄ ያነሱ ቄሮዎችን ይወርፋል። ዱላውን የያዙት ለምንድን ነበር የሚለውን ወደጎን እንተወውና ሰርፀፍሬ የሚዘነጋው አንድ ነገር እነዚሁ ቄሮዎች ህይወታቸውን ሰውተው ዛሬ የሚታየውን አንጻራዊ ነፃነት ባይሰጡት ኑሮ መድረክ ላይ ወጥቶ እንደዚህ አይነት ፖለቲካዊ ጉዳይ ላይ አስተያየት ባልሰጠ ነበር። እስኪ ህወሃት እግር ከወርች አገሪቱን ጠርንፎ በሚያስተዳድርበት ጊዜ መድረክ ላይ ወጥቶ ያለምንም መሳቀቅ ፖለቲካዊ ነክ ጉዳዮች ላይ የሰነዘረውን ትችት ያሳየን። ያኔ አድርባይ ያልሆነ ለእውነት የሚቆም ደፋር የጥበብ ሰው እንለዋለን (ያው ጥበቡ ባይኖርም)። ወጣቶቹ ላይ ያቀረበው ትችትም ሰሚ ሊያገኝ ይችላል።

ለምሳሌ በእውቀቱ እንኳን እንደዚህ አይነት ትችት ቢያቀርብ ቢያንስ በግጥሞቹ በቀልድ እያዋዛ መንግስትን የሾርኔ ሲወጋ ስለነበር ልክ ባይሆን እንኳን ያምርበታል። ሰርፀ ከየሺ ጋር የታለንት ሾው ላይ ፒቹ ከፍ አለ ዝቅ አለ እያለ ከመዳኘት ባለፈ ያቀረበው ረብ ያለው ትችት ካለ ያየ ያጋራኝ። የሰርፀ ንግግር #የመስፍን_በቀለን የቅርብ ንግግር ነው ያስታወሰኝ። አሜሪካ ሄዶ ጠፍቶ በቅርብ ሲመለስ “የኢትዮጽጵያን መሬት በድጋሜ አያለሁ ብዬ ገምቼ አላውቅም ነበር” ብሏል። “ነይ በክረምትም” ፖለቲካ ነበር እንዴ? ሰርፀም ዛሬ ቄሮን በመተቸት ደፋር የጥበብ ሰው እራሱን ሊያደርግ ሲሞክር ግርምትን መፍጠሩ አይቀርም። Short memory ነው ያለን የምትለው አባባል ብዙ ሰው እውነት ይመስለዋል። አንድ አመት ትናንት ናት። ጭራውን ሸጉጦ ከመንግስት ጋር ሲጎናበስ የነበረ ሰው ዛሬ ነፃነቱን በፕሌት የሰጡትን ቄሮዎች የማብጠልጠል ሞራል የለውም።

PS: ትችቱ የኪነ ጥበብ ሰው ፖለቲካ ላይ ለምን አስተያየት ይሰጣል ወይ ይተቻል አይደለም። የንግግሩ ጭብጥ ላይ ነው።

1 Comment

 1. Well; ‘kan dhiqani tuu nama dhiqa jetee okkotteen’! The pseudo artists, pseudo journalists, the pseudo politicians, pseudo elites (luminaries), pseudo Ethiopians, extremists always lack professional excellence, passion and tenacity to leave their comfort zones and engege the multiethnic Ethiopians. Consequently, they always hide their deceptive motives by attaching the term ‘Ethiopia’ as a prefix to their activities.

  Since they do not understand the meaning of freedom of expression, they use every opportunity that comes their way to disseminate lies, blackmails, hiding their crimes and inferiority complexes. Amharic speaking luminaries (individuals who inspire or influence others, especially those who are considered prominent in their particular spheres) always attempt to use stages to attack the Oromo and those they consider others. PS: I prefer to use the term ‘luminary’/’luminaries’ as the term ‘elite’/ ‘elites’, I believe, cannot describe the group crowding Ethiopian affairs. The term ‘elite’ refers to ‘a group of people considered to be superior in a particular society or organization’. That means that Amharic speaking ‘ultra Vires (individuals attempting to impose their ideology beyond their legal power or authority regarding Ethiopianism) are devoid of the ingredients of elitism. These small group of people may qualify to be considered pseudo oligarchies as they still have control over institutions of the country, including cultural institutions and are stretching to maintain the status quo.

  The currently self clarifying Amhara nationalism may bring positive era to the Amhara people and also acknowledge the rights of other Ethiopna peoples. Firstly, it may help the Amhara people to find themselves space in that country as a nation. Secondly, it may address the animosity that those acting as ‘true Ethiopians’/ ‘the unity forces’ have against the peoples of the country, as the Amhara do not need them to trade in their name any more, to dehumanise the Oromo, Tigre, Sidama, etc. Nevertheless, if the Amhara nationalists choose to be expansionist ultra nationalists (extrimsts), the outcomes will be negative in that it may lead to conflicts with others and infringes on rights of others creating xenophobia – the fear that someone will take them over.

  In order to learn from others Amhara nationalists must try to understand how nationalism went wrong in former Yugoslavia. ‘Serbian nationalism resulted in violent ethnic conflict between nationalist Serbs, Croats, Bosniaks and others, resulting in highly violent sectarian variant of Serbian nationalism’. Starting in 1992 Serbian ultra nationalists carried out ethnic cleansing and genocide on groups such as ethnic Bosnian. The irony was that those who masterminded the genocide including Radovan Karadzic and Serb military commander, General Ratko Mladic were indicted for genocide crimes against humanity at the International Tribunal Court. Former Yugoslav president Solobodan Milosevic died in his prison cell of heart attack while awaiting trial. The anti-Oromo hatemongers and media outlets must take note of the fact that their crimes of inciting conflicts will come to justice one day.

  To sum up while the Amhara have inalienable right to advance their interests including exercising the freedom of expression, those who use public stages and media outlets to disseminate lies and hatred against the great Oromo people and other peoples of Ethiopia will not escape justice. The Amhara must wake up and start to acknowledge what those who acted in their name (wrapping Amharanism in Ethiopianism) did to other Ethiopians. Their nationalism must aim at promoting the sense of identity, pride for the Amhara people rather than exporting their own internal problems particularly to Oromia and fanning conflicts. As Professor Ezqeil Gabissa once remarked, “Amhara activists must open their eyes” and engage in genuine politics. Now is the time for the peoples of Ethiopia to sit down and have honest political discourses in order to address fundamental questions. Those trading in the name of Amhara have no chance to deny themselves in public and use Ethiopianism as a cover to keep the status quo. The Amhara people must stand up to anti-Oromo individuals and media outlets and say you cannot disseminate any hatred in our name any more. They must show that they can engage with their neighbours in mutually respectful andcivilised manner and address issues. They must question people when they insult the Oromo people; they must question hatemongers and unreasonable prejudiced anti-Oromo individuals and media outlets before they buy their lies and hateful venomous propagandas.

  Above all, the Ethiopian people are ahead of hatemongers and lunatic fringes, luminaries, and can build the Ethiopia which will be mother of all together. The qeerroo and qaree who have become the targets of anti-Oromo hatemongers showed the greatest capabilities of liberating the Ethiopian peoples from TFLF repression. They are as civil as usual, as courageous is ever, patient and organised as before. They are capable of protecting the great Oromo people from any threats. It is expected from all stakeholders in that country to conduct their political activism in a civilised way. The universal declaration of human rights which entitles individuals to freedom of expression also requires the persons using the right to act responsibly. In other words, freedom of expression can be restricted if individuals’ acts hurt the rights or reputations of others; if it endangers national security or public order, public health, etc. The Ethiopian government and authorities must, therefore, ensure that hatemongers must not have free ride to hurt nations, communities and individuals in the name of freedom of expression.

  May truthfulness visit certain section of the Ethiopian peoples!

  OA

Comments are closed.