የኦነግ መግለጫ:የብልጽግና ቡድን የኦነግ አመራር እና የድርጅቱን አባላት ከድርጅቱ ሊሳን የኦሮሞ ነፃነት ድምፅ ጋዜጠኞች ጭምር እንደገና አስሯል ፡፡

የኦነግ መግለጫ:የብልጽግና ቡድን የኦነግ አመራር እና የድርጅቱን አባላት ከድርጅቱ ሊሳን የኦሮሞ ነፃነት ድምፅ ጋዜጠኞች ጭምር እንደገና አስሯል ፡፡

ታህሳስ 20/2020 ዓም

የብልጽግና ፓርቲ ቡድን ደጋግመው ግጭቶችን እና አለመረጋጋትን ማስፋታቸው ሀገሪቱን ወደ ከፍተኛ አደጋ እያመራት ይገኛል፡፡ ባለፉት ሁለት ተኩል ዓመታት ውስጥ የብልጽግና ፓርቲ በመባል የሚታወቀው የዶ / ር አብይ አህመድ ገዥ ፖርቲ ቡድን በርካታ የተቃዋሚ አመራሮችን ፣ አባላትን እና ደጋፊዎችን እያሰረ ፣ እየገደለ እና እያሸበረ ይገኛል ፡፡
በተለይም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች ፣ አባላትና ደጋፊዎች የታሰሩ ሲሆን አብዛኛዎቹ አሁንም በሚታወቁ እና ባልታወቁ እስር ቤቶች ውስጥ እየተንገላቱ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ገዢው ቡድን የፖለቲካ እስረኞችን እንዲፈታ እና ቀውሶችን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ እያሳሰቡ ባሉበት ወቅት ፣ ገዢው ቡድን የጭካኔ ድርጊቱን አጠናክሮ በመቀጠል የሀገሪቱን የፖለቲካ ችግሮች በጦር ኃይል መፍታት መርጧል፡፡ የገዢው ቡድን የፀጥታ ኃይሎች የኦነግ አመራሮች፣ አባላትን እና ጋዜጠኞችን ጨምሮ 10 (አስር) የኦነግ አባላትን ዛሬ ታህሳስ 20 ቀን 2020 ዓም ለእስር ዳርገዋል፡፡
 
የገዢው ቡድን የፀጥታ ኃይሎች ወደ ኦነግ አባላት መኖሪያ ቤት በመግባት ቤቶቻቸውን እና የግል ሰነዶቻቸውን በመፈተሽ ኮምፒውተሮቻቸውንና ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎቻቸውን ቀምተዋል ፡፡
የታሰሩት የኦነግ አባላት ዝርዝር እንደሚከተለው ነው-
 
1) ሞሃመድ ራጋሳ (ፍራኦል ጃላታ)- የኦነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የኦነግ ቃል አቀባይ
2) ሙራታ ሳባ (ማልካ ዳኑ) – የኦነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል
3) አያቱ ቡልቻ (SBO) – ጋዜጠኛ (SBO)
4) ኢብሳ ጋዲሳ (SBO) – ጋዜጠኛ (SBO)
5) ዶ / ር ጋዳ ኦልጅራ – የኦነግ ሊቀመንበር ጽ/ቤት አስተዳዳሪ
6) የሮሳን አዩ (የፊንፊኔ አከባቢ ድርጅታዊ ጉዳዮች ዓላፊ)
7) ቱማሳ (አሳፋአ ፍቃዱ) – የድርጅታዊ ጉዳዮች አባል
😎 ጉርሙ አይያና – የኦነግ ካድሬ
9) ገሲሳ ኩሳ – የድርጅታዊ ጉዳዮች- ማንዲ ዙሪያ
10) ሊዲያ አሊ ሚሲንሳ – የሴቶች ማህበር አባል
 
ታፊነው የተወስዱ ስሆን እስካሁን ድረስ የት እንዳሉ አልታወቀም ፡፡
በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ በጽንፍ ግጭት ተጠምዳለች ፡በኦሮሚያ ያለው የፀጥታና ደህንነት ሁኔታ እየተባባሰ እና የከፋ እየሆነ ይገኛል፤ በትግራይ ክልል የተካሄደው ጦርነት እና በስበቡ የተፈጠረው ስብአዊ ቀውስ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው :በቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈጠረው ግጭት ከባድ ነው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ትርምስ ውስጥ ናቸው ፡፡ በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ያለው የድንበር ግጭት እና የመሳሰሉት አገሪቱን ወደ አጠቃላይ ትርምስ እና መበታተን ውስጥ አስገብቷታል ፡፡ እነዚህ ውስጣዊ ቀውሶች እና ከጎረቤት ሀገሮች ጋር ያሉንውጥረቶች ቢኖሩም ገዥው ቡድን እራሱን “ለብሔራዊ ምርጫ” 2021 እያዘጋጀ ነው ፡፡
 
በቀጠናው በአሁኑ ወቅት በተስፋፋው ውስጣዊ ግጭትና ውጥረት የከፉ ሆነው እያሉ ምርጫ ይደረጋል ብሎ ማሰብ ይህ የይስሙላ ብቻ ሳይሆን አስገራሚ ሐስትም ነው ፡፡ በዚህ ፈታኝ በሆነው ሁኔታ ውስጥ የብልጽግና ፓርቲ ሁሉንም ተቃዋሚ አባላትን በማስወገድ ያለ ምንም ዓይነት ገለልተኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተሳትፎ ለአንድ ፓርቲ ምርጫ ራሱን በከፍተኛ ሁኔታ እያዘጋጀ ይገኛል ፡፡ ይህ በግልጽ ወደ ፍፁም አምባገነንነት የሚያመራው ሂደት መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ላለፉት 50 ዓመታት በፍፁም የብረት እፍኝ አገዛዝ ውስጥ ነበሩ ፡፡ ላለፉት ሁለት ተኩል ዓመታት የገዥው ፓርት ከሁሉም የከፋ አምባገነን ሆኗል ፡፡ ገዥው ፓርቲ የሚያካሂደው ‹አንድ ቋንቋ አንድ ሀገር› ያለውን ርዕዮተ ዓለማዊ ዓላማውን ለማሳካት እና ተፎካካሪ የሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የማይሳተፉበት ምርጫን ለማሸነፍ ያለሜ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡
 
ኦነግ የኢትዮጵያን ሕዝብ እና ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ለማሳውቅ የምፈልገው ኢትዮጵያ ረዘም ላለ ጊዜ ወደ ተቀናጀ ግጭት ፣ ሙሉ ትርምስ እና አጠቃላይ ውድቀት አፋፊ ላይ ያለች ሀገር እንድትሆን የገዥው ፓርት እያደረገ መገኘቱን ነው፡፡ እነዚህ አዳጋች ሁኔታዎች በግልፅ ይታያሉ ፡፡ ስለሆነም ገዥው ቡድን እነዚህን እስረኞች እና የቀድሞ ፖለቲካ እስረኞችን እንዲፈታ ለዓለም ማህበረሰብ አስቸኳይ እና ከባድ እርምጃዎችን እንዲወስድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ፡፡ በተለይም ለኢትዮጵያ አጋሮች ለአውሮፓ ህብረት ፣ ለአፍሪካ ህብረት እና ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ይህንን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን ትልቅ አደጋ ለመግታት አስፈላጊ በሆነ ሁኔታ ግፍት በማድረግ ጣልቃ እንዲገቡ ጥሪ እናደርጋለን ፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ህዝቦች በተለይም የኦሮሞ ህዝብ እና የኦሮሚያ ዜጎች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ፣ ሰላማዊ ውይይት እንዲካሄድ እና ሀገሪቱን ከዚህ አደጋ እንድንታደግ በአንድነት እንዲስሩ ጥሪ እናቀርባለን ፡፡
 
ድል ለሰፊው ህዝብ!
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር
ታህሳስ 20፣ 2020
ፊንፊኔ ፣ ኢትዮጵያ
ABO


(በጉደታ ቱፋ)
ኦህዴድ ኦነግን ገፋች አልገፋች ትርጉም የለዉም፡፡ ኦህዴድ ካልነቃች ህዝቧንም ራሷንም ማስበላቷ ነዉ፡፡ ኦሮሞን ለመሰልቀጥ ያሰፈሰፈዉ ነፍጠኛ መጀመሪያ ኦህዴድን ነዉ የሚሰለቅጠዉ፡፡ ፖለቲካ የገባዉን ኦሮሞ ሁሉ ጽንፈኛ ብላችሁ ገፍታችሁ እናንተም ተበልታችሁ ኦሮሞን አታስበሉ፡፡ አማራ ከለማኝ፣ ከደብተራ እሰከ ምሁር ተብየዉ ቡድን ራሱን አደራጅቷል፡፡ እናንተ የኦሮሞን ምሁራን በመጠራጠር ለማጥፋት ስትሰሩ የአማራ ብልጥግና የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤን አደራጅቶ ከአማራ ምሁራን ጋር አብሮ እየሰራ ነዉ፡፡ እናንተ የኦሮሞን ባለሃብት ኦነግ-ሸኔ እያላችሁ ስታሳድዱ፣ የአማራ ብልጥግና ከአማራ ባለሃብት ጋር በመሆን የአማራን የታጠቀ ኃይል በልዩ ሁኔታ በማደራጀት ላይ ናቸዉ፡፡
እመኑኝ የአማራ ኃይል ኦሮሞን ለማጥፋት የኦሮሚያን መንግስት እየመራ ያለዉን ኦህዴድን ነዉ መጀመሪያ የሚያጠፋዉ፡፡ ሌሎቻችን ለማጥፋት የሚንቀሳቀሱት እናንተ ቁርስ ካደረጉ በኋላ ነዉ፡፡ ለራሳችሁ ስትሉ ከኦሮሞ ላይ የጭካኔ በትራችሁን አንሱ፡፡
በነጋራችን ላይ፣ ኦህዴድን የሚንማጸነዉ መስዋዕትነት ለመቀነስ እንጂ ኦሮሞ ዳግም በአቢሲኒያዉያን አይሸነፍም፡፡