የኦነግ መግለጫ:በመንግስት ሃይሎች እየተፈጸመ ያለው የጅምላ ግድያና እስራት ኣለመረጋጋትና ቀውሱን ያባብሰዋል እንጂ መፍትሄ ኣያመጣም

የኦነግ መግለጫ:በመንግስት ሃይሎች እየተፈጸመ ያለው የጅምላ ግድያና እስራት ኣለመረጋጋትና ቀውሱን ያባብሰዋል እንጂ መፍትሄ ኣያመጣም

A defiant Qeerroo (Oromo youth) rocking the Oromo Resistance flag at a rally held in the US to condemn the Ethiopian State following the assassination of Artist Hachalu Hundesa.


በመንግስት ሃይሎች እየተፈጸመ ያለው የጅምላ ግድያና እስራት ኣለመረጋጋትና ቀውሱን ያባብሰዋል እንጂ መፍትሄ ኣያመጣም

(የኦነግ መግለጫ፡ ነሓሴ 21, 2020ዓም)

የመንግስት የታጠቁ ሃይሎች በኦሮሚያ ውስጥ እያካሄዱት ያለው የግድያና የእስራት ዘመቻ ሃገሪቷን ወደባሰ ቀስና መፈራርስ ያመራታል እንጂ የሚያመጣው መፍትሄ ኣለመኖሩን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በጥብቅ ያሳስባል።

በተለይም ባለፉት ሶስት ቀናት መንግስት የታጠቁ ሃይሎችን በብዛት በኦሮሚያ በማሰማራት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችን ማሰሩና የመብት ጥያቄ ያቀረቡ ንጹሃን ዜጎች ላይ በተከፈተ ተኩስ በመቶዎች ማቁሰሉና መግደሉ ፈጽሞ ኣስከፊና ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ነው።

መንግስት በህዝቡ ላይ እያደረሰ ባለው ግድያና እስራት ላይ በኣስቸኳይ ውስጡን በማየት፡ ያለኣንዳች ጥፋት ያሰራቸውን የኦሮሞ ፖለቲካ ድርጅቶች ኣባላትና ኣመራር ኣካላትን ባጠቃላይ የኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞች በኣስቸኳይ በመፍታት፡ እየቀረበ ላለው የፖለቲካ ጥያቄ ከኦነግ፣ ከኦፌኮና ከሌሎችም የኦሮሞ ድርጅቶችና ከሌሎችም ጋር በመሆን ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ ለማስገኘት እንዲሰራ እንጠይቃለን።

በመንግስት ትዕዛዝ ተሰማርታችሁ ህዝባችሁን በመግደልና በማሰቃየት ላይ የምትገኙ የጸጥታ ሃይሎች በኣስቸኳይ ከድርጊታችሁ ታቅባችሁ ለህግ ተገዢነታችሁን እንድታሳዩ እየጠየቅን፡ መግደልና ማቁሰልን ጨምሮ ሁሉንም ኣይነት ወንጀል በማዘዝና በማስፈጸሙ ውስጥ እጃቸው ያለበት ተመርምሮ በመለየት በኣስቸካይ ለህግ እንዲቀርቡ ኦነግ ኣጥብቆ ይጠይቃል።

በመንግስት ሃይሎች በመፈጸም ላይ ያለው የጅምላ ግድያና እስራት ኣለመረጋጋትና ቀውሱን ይበልጥ እያባባሰው እንዳይሄድ የህዝቡ ስጋት መሆኑን እናሳስባለን።

ድል ለሰፊው ህዝብ!!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር

ነሓሴ 21, 2020ዓም