የኦሮሞ የፖድርጅቶች ለቲካ ስምምነት ፈጥረዉ ኦሮሚያን በጥምር መምራት በኦሮሚያ ብሎም

የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች ስምምነት ፈጥረዉ ኦሮሚያን በጥምር መምራት በኦሮሚያ ብሎም በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ሊያመጣ ይችላል

Deressa Ebba Geneti

የፖለቲካ ሽኩቻ ጉዳይ በተለያዩ ኃይሎች መካከል ፉክክርና በመጨረሻም ሥልጣን የመቆጣጠር ጉዳይ ብቻ ነዉ፣ በተረፈ የተለየ የፍቅርም ይሁን የጥላቻ ዓላማ ሊኖረዉ አይችልም። በየተሰለፍንበት ፓርቲ ወይም ድርጅት ሆነን የራሳችንን አሞግሰን የሌሎቹን የምናጥላላበትም ለዚሁ ዓላማ ነዉ። ይኸ ሥራችን ለድል ካላበቃን ግን ለአንድ አፍታ ብቻ ሳይሆን እንቅልፍ አጥተን አላማችንን ለማሳካት የተሻለ አንጻራዊ መንገድ መፈለግና አቅጣጫ መቀየስ ምርጥ የፖለቲካ ጠበብትነትና ሊቅነት ነዉ።

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ እንደ ጋሪ ፈረስ ወደ አንድ አቅጣጫ ብቻ ኢላማ አድርጎ ተቃራኒዎቼን ሁሉ ደምስሼ ማሸነፍ አለብኝ በሚል ቀኖና ወይም ዶግማ  ተለጉሞ መሄድ ለረዥም አመታት የዘለቀ ሲሆን፣ በዚህ ሂደት ህዝቦችን እየበላ መሄድን እየጨመረ ሄደ እንጂ ማንም ለድል የበቃ የለም።

ለዚህም ነዉ ይመስለኛል፣ ኢሕአዲግ እንደ ፓርቲ ከነበረበት አምባገነናዊ አገዛዝ ትንሽም ቢሆን ፈቅ ያለዉና፤ በማድረጉም ደግሞ እነሆ ነፍሱን አድኖ የሚገኘዉ፤ ነገር ግን ዛሬ ባገኘዉ ዕድል ተጠቅሞ አመራሩን ከሌሎቹ ጋር ስልጣን እኩል ተጋርቶ አገሪቱን በማረጋጋት ሰላም እንደ ማስፈን ሥልጣኑን ለብቻዉ ሙጭጭ ብሎ በመያዝ ከየአቅጣጫዉ እንደገና ዉዝግብና ጦርነት ዉስጥ ገብቶ ይገኛል።

ሩቅ ሳንሄድ ይኸን የኢሕአዲግን ሁኔታ ብንመለከት፣ ኢሕአዲግ እስካሁን ከመጥፋት የዳነዉና ዛሬ እንዲያዉም መልሶ ነፍስ ሊዘራ የቻለዉ፣ ድርቅ ብሎ በትዕቢት ማሸነፍ አለብኝ የሚለዉን የግብዞች ግትርነት ለአጭር ጊዜም ቢሆን ትቶ ስለተለሳለሰና በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነት ሊያስተርፉለት የቻሉ አንዳንድ እርምጃዎች በመውሰዱ ነዉ።

ስለዚህ የኦሮሞ ድርጅቶችም ሌሎቹን ተፎካካሪዎች/ተቀናቃኞች አጥፍቼ እኔዉ ብቻ በአሸናፊነት መዉጣት አለብኝ የሚለዉን ግትር ሀሳብ፤ እስካሁን ተሞክሮ ብዙ ኪሳራ ያስከተለ እንጂ ያልሰራላቸዉ ስለሆነ ቆም ብለዉ አስበዉና፣ በተለይ ኦዴፓና ኦነግ በኦሮሞ ሕዝብ ፈቃድ ሳይሆን በጉልበት ሌላኛዉን ደምስሼ አጥፍቼ እኔ ማሸነፍ አለብኝ የምትልዋን ግትርነት እርግፍ አድርገዉ ይጣሉዋት፤ በፍጹም አያዋጣቸዉም። አሁን ባለንበት ሁኔታ አብዛኛዉ የኦሮሞ ሕዝብ ፍላጎትና የሚወደው ምን እንደሆነ ያልገባቸዉ ከሆነ ቶሎ ዉለዉ ሳያድሩ ልብ ብለዉ ያስተዉሉ። አንዳቸዉ ሌላኛዉን በኃይል አጥፍተዉ ማሸነፍ አዳጋች ነዉ፤ በዚህ ግትርነት ከቀጠሉ ተጠፋፍተዉ፣ ለሌሎቹ የኦሮሞ ሕዝብ የፖለቲካ ባላጋራዎች ሁኔታዎችን አመቻችተዉ የኦሮሞን ሕዝብና ኦሮሚያን እጅጉን መግዳትና ማድማት ብቻ ሆኖ ይቀራል። ስለዚህ የሚያዋጣዉ አንድና አንድ ብቻ መንገድ ሁለቱ ድርጅቶች ተስማምተዉ ኦሮሚያን ከሌሎቹም የኦሮሞ ድርጅቶች ጋር በመስማማት በጥምር መምራት ነዉ። ባደጉት ወይም ሰለጠኑ በሚባሉት አገሮች ፓርቲዎች በምርጫ ተወዳድረዉ አንድ ፓርቲ ለብቻዉ ምርጫዉን አሸንፎ ሥልጣን መዉሰድ ባልተቻለበት ሁኔታዎች ሁሉ ፓርቲዎች ተመካክረዉ በመቻቻል የጥምር መንግስት መስርተዉ አገር ይመራሉ። ዲሞክራሲያዊ መንገድ ስለሆነና ማንም የማይከስርበት ስለሆነ ይኸን አማራጭ መከተል የሁሉም አሸናፊነት ነዉ የሚሆነዉ። በአካባቢያችን አዲስ የፖለቲካ ባህል ሆኖ ሊታይ ይችላል ግን ወሳኝና ፍሬያማ ነዉ።

በተለይ ኦዴፓ፣ አምባገነኑ ኢሕአዲግ በ2007 ዓ. ም ባካሄደዉ ብሔራዊ ምርጫ ሌሎቹን ሁሉ ከጨዋታ ዉጭ አድርጎ 100% አሸነፍኩ ባለዉ ምርጫ መሰረት ወደ ስልጣን በመምጣታቸዉ እኛ ብቻ ነን የአገሪቱ የሕግ የበላይነት ማስከበር ያለብን በማለት በሌሎቹ ላይ አላስፈላጊ ተፅዕኖ በመፍጠር ችግሮች እየተባባሱ እንዲሄዱ ከማድረግ ተቆጥበዉና ኦነግን ጨምሮ ከሁሉም የኦሮሞ ድርጅቶች ጋር ኦሮሚያን በጋራ ለመምራት የሚቻልባትን መንገድ ጊዜ ሳይሰጠዉ ከዛሬዉ ሁኔታዉን ማመቻቸት አጋጣሚ የጣለባቸዉ ግዴታቸዉ ነዉ፤ ይኸን ለማድረግ ምንም የሚያስቸግርና የሚያግድ ነገር የለም፣ የሚያስፈልገዉ ፍላጎትና ቁርጠኝነት ብቻ ነዉ።

ኦዴፓ ይኸን እርምጃ መዉሰድ ከቻለ ሌላ ምንም አስታራቂ ሽማግሌ ወይም አባገዳ እያሉ የአይጥና የድመት ጨዋታ መጫወት ይቀርና ሰላምና መረጋጋት በኦሮሚያ ያለምንም ጥርጥር ይሰፍናል። በኦሮሚያ ዉስጥ በአንድ ድምጽ መናገር የተቻለ ዕለት በኢትዮጵያ ስም የሚካሄዱት አንጃ ግራንጃዎች የእምቧይ ካብ ይሆኑና በኢትዮጵያም የሰላሙ አየር እንደሚነፍስ እሙን ነዉ። አዲስ ኮንትራት ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ሊሆን ነዉ።

ከአራቱ የኢሕአዲግ ድርጅቶች ጋር ያለን ስምምነት አይፈቅድልንም የሚል ሰንካላ ምክንያት ይቀርብ ይሆናል ግን ይኸ በምንም መንገድ ተቀባይነት የለዉም፤ ምክንያቱም የተቀሩትም አራቱ ድርጅቶች በመካከላቸዉ የነበረዉን ስምምነት ጠብቀዉ እየሰሩ ሳይሆን በመካከላቸዉ ያልታወጀ ጦርነት እየተካሄደ ሲሆን ምንም የረባ የስራ ትስስርም በመካከላቸዉ በተጨባጭ አይታይም። ስምምነት በመካከላቸዉ ቢኖር በከፍተኛ ሰብአዊ መብት ጥሰት የተከሰሰ ሰዉ በዚሁ አንድ አገር ዉስጥ እየኖረ በሌለበት ክስ አይመሰረትበትም ነበር። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በኦሮሞ ስም ተደራጅተዉ ትግል እናካሄዳለን እያሉ የኦሮሞንና የኦሮሚያን ችግሮች በሰለጠነ መንገድ መፍትሄ መስጠት ሳይችሉ ስለኢትዮጵያ ታላቅነትና ጥንታዊነት ከሌሎቹ በተለየ ሁኔታ መጠበብ አንድም ግብዝነትና መመጻደቅ ነዉ አሊያም የኦሮሞን ስም መለጠፉ ለፖለቲካ ንግድ ለማስመሰል ብቻ የተደረገ ጥረት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።

ስለዚህ በኢትዮጵያም አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት መፈጠር እንዲችል የተረጋጋችና ሰላም የሰፈነባት ጠንካራ ኦሮሚያ ወሳኝ ናት።

1 Comment

 1. Well observed, Deressa Ebba Geneti!

  Oromo political parties operate in Ethiopia, and are vulnerable to the Ethiopian political culture which has been cursed with “zero sum game” (in which political calculations are based on winning all or none). Although modern terminologies are being borrowed by Ethiopian politicians and often used for public consumptions, Ethiopian politics is always marred in toxic deceptions, where most politicians waste more time on manipulating and cheating others rather than genuinely working towards achieving common good. Instead of competing peacefully, respecting what the other sides believe and expect of them, they act blindly on achieving their own interests, disregarding the interests of others. This kind of shortsightedness often led to disastrous political events, and consumed generations after generations. Oromo politicians, particularly, have been victims of Abyssinian deceptions as they failed to carefully evaluate and negotiate terms of engagements and coexistence. While Oromo politicians who were betrayed now and again either lost their lives in the hands of their Abyssinian counterparts or been imprisoned or exiled, their Abyssinian comrades enjoyed temporary victories, and inflicted untold sufferings on our people. In fact, shortsightedness has also hurt the Abyssinian sides who have focused on temporary gains at the expense of long term political settlements (this is not the purpose of my comment, though).

  It is only sane to hope that important lessons might have been learned by Oromo new breed politicians, whether they function under the umbrella of ODP or OLF or otherwise. The more opportunities they create to read each other and try to cooperate on addressing Oromo questions, the more chances they will have to succeed. On the contrary, if they aim to destroy each other and hope to gain cooperation from others in order to enjoy unsustainable political power, especially, in the current political climate, it does not take genius to predict what will follow. The great Oromo people, who are awaiting patiently, will ran out of patience and start to take matters into their hands. They will not sit down and let mediocre politicians to hand over them into the hands of their historical enemies. They will promote capable leaders from among themselves and fight back against any attempt to subjugate them again. If Oromo politicians fail to cooperate and work together, predictably and productively, to reduce uncertainty, emotions will ran high and intolerance will increase. If that is allowed to happen by Oromo politicians to gain cheap political advantage over one another, the people who have sacrificed their bright children, to come out of a century and half darkness, will be left with the option of asserting themselves by force. As Peterson (2018) asserts, ‘it isn’t precisely that people will fight for what they believe. They will fight, instead, to maintain the match between what they believe, what they expect, and what they desire. They will fight to maintain the match between what they expect and how everyone is acting’.

  Indeed, the great Oromo people believe that their country has been occupied by force and they must regain their abbabiyyumma. They expect Oromo political parties to unite around this believe and work tirelesslly in order to achieve Oromo objectives, greater freedom and abbabiyyumma. They desire to achieve their objectives peacefully in civilised manners, unless circumstances necessitate otherwise. They are watching, carefully, how political parties trading in their names, are behaving towards each other as well as other forces operating in the Ethiopian political space, with Oromo affairs in mind. They are not only being amused when Oromo politicians handle their affairs foolishly but also think of alternatives. It is for this reason that ODP and OLF as well as other Oromo political parties must keep themselves busy, and gain the trust of the Oromo people rather than wasting valuable time trying to trap each other.

  Oromo politicians, watch out; ‘in politics, being deceived is no excuse’.

  OA

Comments are closed.