የኦሮሞ የነፃነት ትግል (ኦነት) ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ሁለተኛ ዙር፥ ክፍል ስድስት

የኦሮሞ የነፃነት ትግል (ኦነት) ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ሁለተኛ ዙር፥ ክፍል ስድስት

ብርሃኑ ሁንዴ, Waxabajjii 15, 2019

በሁለተኛ ዙር ክፍል አምስት ፅሁፍ ውስጥ የኦነግ አመራር ከቴክኒክ ኮሚቴ ጋር የሰጠውን መግለጫ በሚመለከትና ሌሎች የተለያዩ አንዳንድ ጉዳዮችን አንስቼ ነበር። ከነዚህ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ እየተቃረበ ያለው የአገሪቷ ብሔራዊ ምርጫ ሲሆን፣ ባሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ውስጥ እየታየ ባለው ሁኔታ ውስጥ ኦነግ ይህንን ምርጫ አሸንፎ የተነሳለትን ዓላማ ከግብ ማድረስ ይችል ይሆን? የሚል ጥያቄ አንስቼ አንዳንድ ነገሮችን ለማብራራት ሞክሬ ነበር። በዚህኛው ክፍል ስደስት ፅሁፍ ውስጥ ባሁኑ ወቅት በአገሪቷ እየተደረገ ያለውን በሚመለከት እያስተዋልኩ ያለሁትን አቀርባለሁ።

የኦሮሞ ሕዝብ ትዕግስት እንደ ሞኝነት መታየት የለበትም

የኦሮሞ የዋሕነትና ትዕግስት አንዳንድ ጊዜ እንደ አለማወቅ ወይም ሞኝነት የሚወሰድ ይመስላል። ይህ ደግሞ የሚታየው ከባዕድ በኩል ብቻ ሳይሆን ኦሮሞም ሆነው እንደዚህ የሚያስቡ ቁጥራቸው ጥቂት አይደለም። የኦሮሞ ሕዝብ ስያነሳቸው ለነበሩት ጥያቄዎች መልስ እየጠበቀ እንደሆነ የሚታወስና የማይካድ ነው። ይሁን እንጂ እስቲ ይህ ለውጥ ወደ ዲሞክራሲ ይሻገር ብሎ በትዕግስት ስጠብቅ፣ ባንድ በኩል ይህ ሕዝብ ጥያቄዎቹን እነደዘነጋ ወይም እንደተወ ተደርጎ ይታያል። በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ሕዝብ ለጊዜው ዝምተኝነትን ስመርጥ የተታለለ መስሎአቸው በጥያቄዎቹ ላይ በመዝለል የባዕድን ፍላጎት ለመጠበቅና ለማሟለት ይጥራሉ።

እንደዚህ የሚያስቡት ግን ደግመውና ደጋግመው ራሳቸውን መጠየቅ አለባቸው። ትዕግስት ከወሰን ካለፈ ወደ ሌላ ነገር ሊወስድ እንደሚችል መገንዘብ በጣም አስፈላጊ ነው። ይህንን ጉዳይ ያነሳሁበት ምክንያት በኦሮሞ ሕዝብ ትግል ከመጣው ለውጥ ጋር ስለሚያያዝ ነው። እውነት እንናገር ከተባለ ይህ ለውጥ በኦሮሞ ሕዝብ እንቅስቃሴ ተገኘ እንጂ ለዚህ ሕዝብ የተቀየረ ነገር የለም ቢባል ሀሰት አይሆንም። ይህ ራሱን አድሷል የሚባልለት የኢሕአዴግ መንግስት ኦሕዴድ (OPDO) በመንግስት ውስጥ ቁልፍ ቦታዎችን አግኝቶ አገሪቷን እያስተዳደረ ስለሆነ የኦሮሞ መንግስት ነው ይባላል እንጂ የኦሮሞ ሕዝብ ከዚህ ያገኘው ጥቅም አለ ብዬ ለማስብ ይቸግረኛል።

የኦሮሞ ሕዝብ ከዚህ ለውጥ ያገኘው ጥቅም ምንድነው?

በወያኔዎች የበላይነት አገዛዝ ስር ኦሮሞ ሲታሰር፣ ሲሰቃይ፣ ሲገደል፣ ሲደፈር፣ ከአገሩ ሲስደድ፣ ንብረቱና መሬቱ ሲቃማ ወዘተ ነበር። የኦሮሞ ሕዝብ ከባድ መስዋዕትነትን ከፍሎበት ካስገኘው ለውጥ በኋላ ያለውንም ሁኔታ ካየን፣ ይነስ ይብዛ እንጂ እነዚህ የተዘረዘሩት እየታዩ ናቸው። ምናልባት ከአገር መሰደድ ቀንሶ ሊሆን ይችላል። በዚያ በሕዝባዊ አመፅና እንቅስቃሴ ወቅት የኦሮሞ ሕዝብ ስያነሳቸው ከነበሩት ጥያቄዎች ውስጥ አንድም አልተመለሰም። እነዚህ ጥያቄዎች መልስ ማግኘታቸው ቀርተው ይህ ሕዝብ ዛሬ በሰላም ወጥቶ መግባትም አልቻለም። ሰላሙና ደህንነቱ አልተጠበቁም። ይህ ለምን ሆነ? ብለን ጥያቄ ካነሳን፣ መልሱ ባጭሩ ይህ አሁን ያለውም መንግስት ያው ድሮ የለመደውን አሰራርና አካሄድ እየተጠቀመበት ነው ያለው እንጂ ለሕዝብ ጥያቄ ጆሮውን ሰጥቶ በጥሞና አዳምጦ ለችግሮች መፍትሄ ለማግኘት ፍላጎት ስለሌለው ነው።

ሀበሾች በኦሮሞ ላይ ለምያደርጉት የስም ማጥፋት ፕሮፖጋንዳና እየገለፁ ላሉት ፍላጎታቸው ግን ይህ መንግስት ተኝቶ የሚያደርም አይመስልም። ከኦሮሞ ሕዝብ የወጡት የኦሕዴድ ከፍተኛ የአመራር አባላት መጀመሪያ አካባቢ ወደ ስልጣን ሊመጡ ስሉ በነበረበት ወቅት የኦሮሞን ሕዝብ ስያሞግሱ፣ የኦሮሞን ብሔርተኝነት የሚያንፀባርቁትን ንግግሮች ስያሰሙ፣ ጌታችን ይህ ሕዝብ ነው እያሉ ይህንን ሕዝብ ስያባብሉና ስያታልሉ ነበር። ዛሬ ግን ሁኔታዎችን ካመቻቹ በኋላ ይህንን ሕዝብ ረስተው፤ ለባዕድ ግን በተቻላቸው መንገድ ሁሉ እየሰሩላቸው ይገኛሉ። ኦሮሞ ስያነሳቸው የቆየውን ጥያቄዎች ትተው የባዕድን ፍላጎት ግን ለማሟላት ሌት ተቀን ይሰራሉ። ይህ ጉዳይ በደንብ ሲታይ እነዚህ ሰዎች ኦሮሞ መሆናቸው ራሱ ጥያቄ ውስጥ ይገባል። በስጋና ደም ኦሮሞ መሆናቸውን ጥያቄ ውስጥ ማስገባቴ አይደለም። ነገር ግን ትኩረታቸውና ፍላጎታቸው የት እንደሆኑ ለመገመት አያስቸግርም ማለት ፈልጌ ነው።

ሀበሾች በተለይም ደግሞ የድሮ ስርዓት ናፋቂዎች፤ የአንድን ብሔር የበላይነት በሕዝቦች ላይ ለመጫን የሚፈልጉት ኃይሎች የኦሮሞን አንድነት የምጠሉበትና የኦሮሞ ነፃነት ትግልን የሚቃወሙት ኦሮሞ ይህችን ኢትዮጵያ የሚትባለዋን አገር ያፈርሳል ብለው ስለምያስቡና ስለምያምኑም ነው። የሚደንቅና አልፎም የሚያሳዝን ግን በኦሮሞ ሕዝብ ስም የተቋቋመው ድርጅትና መሪዎቹ ሀበሾች እያደርጉ ያሉትን የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ እውነት አድርገው ወስደው፣ ለነሱ ተባባሪ መሆናቸው ነው። እስቲ አንዳንድ ምሳሌዎችን እንይ። በአማራ ክልልና ሌሎች ቦታዎች ሰዎች ተደራጅተው፣ ታጥቀውና ተሰማርተው ኦሮሞን ጨምሮ በሌሎች ሕዝቦች ላይ ጉዳት እያደርሱ ይገኛሉ። መንግስት ግን ይህንን በዝምታ አንዳለፈ በመሬት ላይ የታየ ሀቅ ነው። የኦሮሞ ግን እንደ ልዩ ጉዳይ ታይቶ ለኦሮሞ ነፃነት ትግል ብለው ኑሮአቸውን ጫካ ያደርጉትን ሽፍቶች በማለት ይዘመትባቸዋል። ጦርነት ይከፈትባቸዋል። እነዚህ ባጫካ ያሉት ልጆች የሚያነሱት አግባብ ያለው ጥያቄ እንኳን ታይቶ፣ በሰላማዊ መንገድ ለችግሮች የጋራ መፍትሄ ለማግኘት ይህ መንግስት ሙከራም አላደረገም። በኃይል ተጠቅሞ እነዚህን ልጆች ለማጥፋት የወሰን ይመስላል።

እነዚህን ልጆች ለማጥፋት ሲባል በሚደረገው ጦርነት ውስጥ የሚጎዳው ሰላማዊ ሕዝብ ነው። እዚህ ላይ አንባቢዎች እንድገነዘቡ የምፈልገው እኔ ለነዚህ ልጆች መናገሬ አይደለም። እነዚህ ልጆችም ከጥፋት ነፃ ይሆናሉ ብዬም አላስብም። ይሁን እንጂ እነዚህ ልጆች ለሽፍታነት ብለው ከቤታቸው እንዳልወጡ አምናለሁ። ይህ መንግስት ለምን በነዚህ ልጆች ላይ ጦርነት እንደከፈተ የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም፣ እኔ ግን እንደ ራሴ አመለካከት ሶስት ዋና ዋና ምክንያቶችን እገምታለሁ።

አንደኛ፣ ከዚህ በላይ እንደተገለፀው፣ ለሀበሾች ፕሮፖጋንዳ ትኩረት በመስጠት፤ የኢትዮጵያን አንድነት ማስጠበቅ በሚል ስም እነዚህን ልጆች ለማጥፋት፤ የኦሮሞ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ጥያቄ እንዳይነሳ ለማድረግ፣ ይህ የኦሮሞ ሕዝብ የመወስን መብቱ እንዳይረጋገጥ ለማድረግ ተብሎ ይህ ጦርነት የተመረጠ ይመስላኛል።
ሁለተኛ፣ በሰላማዊ መንገድ እንታገላለን የሚሉትን የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች በጉያው ስር አስገብቶ በመቆጣጠር፣ በትጥቅ በኩል የምንቀሳቀሱትን ደግሞ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት፣ የኦሮሞ የአገር ባለቤትነት ጥያቄ እንዳይነሳና መልስ እንዳያገኝ ለማድረግ ዓላማ አድርጎ የምንቀሳቀስ ይመስላል።
ሶስተኛ፣ የሕግን የበላይነት ማስጠበቅ በሚል ሽፋን ይህንን መንግስት የሚቃወሙትን ኃይሎች ከተቻለ መሉ በሙል ለማስወገድ፣ ካልተቻለ ግን ለማዳከም፤ ለራሱ ግን የበላይነቱን አረጋግጦ እንደ ፈለገ ለመሆን የወሰነ ይመስላል።
“የምትችለውን ደብድብ ሲባል ሞኝ ባል ገብቶ ሚስቱን ደበደባት” እንደሚባለው ተረት፣ ይህ በኦሮሞ ሕዝብ ስም የተቋቋመው ድርጅትና ይህ ድርጅት እያመራ ያለው መንግስት ለኦሮሞ ሕዝብ የሚቆረቆር ቢሆን፤ እውነትም እንደሚባለ የኦሮሞ መንግስት ቢሆን ኖር፤ እውነተኛ የኦሮሞ ብሔርተኝነት በወኔአቸውና ልባቸው ቢኖር ኖሮ፤ የኦሮሞ ሕዝብ ችግርና ስቃይ ቢታያቸው ኖሮ፤ የኦሮሞ ቁስል ብያማቸው ኖሮ፣ ዛሬ የታጠቁ የባዕድ ኃይሎች ኦሮሞን በምጎዱበት ጊዜ ለዚህ ሕዝብ ከመድረስ ይልቅ በተቃራኒው ግን የኦሮሞን ልጆች ሽፍታዎች ናቸው ብለው፣ እነዚህን ልጆች ለማጥፋት ያለውን ጉልበት ሁሉ በመጠቀም ጦርነት አይከፍትባቸውም ነበር። እንግዲህ ይህ ሁል ድርጊት ነው ይህንን በኦሮሞ ስም የተቋቋመውን ድርጅትና በዚህ ድርጅት የሚመራውን መንግስት ማንነታቸውን በግልፅ የሚያሳየው። ይሁን እንጂ ለፍትህና ነፃነት የሚደረገውን ትግል ለጊዜው ማዳከም ይቻል ይሆናል እንጂ ማጥፋትና ማቆም አይቻልም።

ተመልሰን እስከምንገናኝ በደህና ቆዩ

Via: Dábessá Gemelal


Jirra jedhu ilmaan isin leenjisaafi barsiisaa turtanii biraa harka diinaa buutan jabaatanii gurmuu fi damee baayyee godhatanii isin eegaa jiru.
Kaayyoon keessan latee firii godhatee kunoo bifa kanaan Miseensonni Jajjabee isin simachaa jiru.
Yaadannoo Miseensota WBO kanneen mana hidhaa Wayyaaneetti dararamaa turanii kaleessa ba’aniif.

Waliifnuu Gaaddisaa

June16,2018


Lachuu diiggaa oromoo fi Oromiyaati fida!

ሰዉየዉ ምን ነክቶት ነዉ ለነፍጠኞች ሥምል የሚዉለዉ??ራሡ ነፍጠኛ ይሆን እንዴ?

የሰውዬውን ማንነት አሁንም ያልገባው ኦሮሞ ካለ እሱ ቂል መሆን አለበት
“ዲቦራ የምትባል ልጅ አለችኝ ..ግማሽ ጎንደሬ ግማሽ ጅማ የሆነች” አለ። “ጅማ “የሚባል ብሔር ወይም ዘር የለም፤ ማንነቱን ስለሚደብቅ ኦሮሞ ወይም ኩሎ አላለም፡፡ ይህ ሰው ኦሮሚያ ውስጥ ተወለደ እንጂ ከኦሮሞ አልተወለደም። kurr!! Oromoo guurii gurraa fudhadhu!!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ባራክ ኦባማ የአሜሪካ ፕረዝደንት ሲሆን ጥቁርነቱን አልካደም፡፡ እንዲያውም የነጮች የበላይነት በሰፈነበት አሜሪካ ፡እሱ በእናቱ በኩል ነጭ ቢሆንም ነጭነቱን ሳይሆን ጥቁርነቱን አጉልቶና ከፍ አድርጎ በኩራት ስለጥቁሮች ለጥቁሮች ሲሟገት ነበር። የታላቋና ሀያሏ አሜርካ ፕረዘደንት ሆኖ በኬንያ ገጠር ውስጥ በመገኘት ፤ ጥቁር የሆኑ አያቶቹንና ዘመዶቹን በመጎብኝት ፤ ኩሩ የጥቁር ልጅ መሆኑን ለአለም አስመስክሯል። ሰው ማንነቱን ሳይክድ ክብር ማግኘት እንደሚችል በገሃድ አስመስክሯል ኦባማ። “የኛው” ኮልኮሌ አብይ አመድ ክብር ለማግኘት ማንነቱን መካድ፤ ሌሎችን መምሰል፤ በጠላት ፊት ኦሮሞን ማጥላላት እንደ ስልጣኔ ወስዶታል። የወሎ ኦሮሞ በድርብ ጭቆና ውስጥ ነው ያለው፡፡ በተለይም ሰሞኑን በወራሪው የአማራ/አብን መንግሥት የወሎ ኦሮሞ በገፍ ፤ በግፍ ወደ እሥር ቤት እየተጓዘ ነው። ኮሎኔል አብይ አህመድ ደሴ ደርሶ በድርብ ጭቆና ቀንቡር ስር እየተማቀቁ ያሉትን ኦሮሞችን ዞር ብሎ አላየም። ይህ ሰው ምንም አይነብ ኦሮሞነት አይሰማውም። የኦሮሞ ስቃይና መከራ ትንሽ እንኳ አይቆረቆረውም። እኔ በበኩሌ ይህ ሰው በአባቱ በኩል ኦሮሞ ነው የሚባለውን እንኳን እጠራጠራለሁ።

This guy came to the power in the name of Oromo people, but nothing to do with Oromo. I think that is why he even hates Oromo, Because he has to hide himself behind Oromo, Wow!!

Faajjii Dhugaa

Haasawa Dr. Abiy Daseetti godhe keessatti biyyi Itoophiyaa rakkoo hamaa keessa jiraachuu isiitu mul’ata. Madaa Wayyaaneen biyya irratti dhiifte suphuun hojii dadhabsiisaa itti tahee jira. Liqii Itoophiyaarratti hambisan dabalatee waan Wayyaaneen balleessitee deemte qajeelchuun hojii ulfaataa itti tahee jira. Kanumarrattuu Oromoo waan taheef olaantummaa Oromootu jira jedhanii shakkaa jiru. Homaa nuuf hin goone jechuu malee galata irraa argachaa hin jiru. Haala walxaxaa keessa jira.

Ferhan Abdulselam

How can we forget this????

#OromoProtests– This is Oromia! Here is a latest video exposing the torture and shameful police barbarism to innocent Oromo students in Dire Dawa University.

Kun Oromiyaa dha! Viidiyoon kun hiraarsaa fi roorroo poolisiin Wayyaanee barattoota Oromoo yunivarsitii Dirree Dhawaa irratti gara laafina tokko malee raawwataa jiru saaxiluu dha.


“Empty barrel makes the most noice”. This idiom perfectly exemplify how empty and ignorant Colonel Abiy Ahmed is of the true history of Menelik versus Oromo. Egotistic buffoon like Abiy with the least knowledge are the most outspoken about their opinion when their silence would have been golden.

BIRANUU NEGGAA tuffii Uummata oromoo irra Colonel Abiyyi qabuu bifa armaan gadiidhaan yerooo ibsuu dhaga’uu caalaa kan nama aarsuu hin jiruu. sirnaa minilkiindeebisee lubbuu itti horee harkaa muraa fi Armaa muraa oromoo irran Minilkii nafxaanyaan gahe minilikiin bifa ittin faarsuun muziyeemin qophaa’aa akka jiruu dhaga’uu caalaa eedduu waanti Nama aarsuu hin jiruu. sirnii nama nyaata Minilikii deebi’ee Ilmaa isaan Hundee gadi dhabbbachuuf akka jiruu kun ifa ifaati kan obsii dha.
Ka’i dammaqiii tufaatamuu keessaa kan ofi baasuu sii qofa yaa oromoo.

Bilisumma Fi Walaabummaa


ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከደሴ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ያደረጉት ውይይት
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ሰኔ 8/2011 ዓ.ም.

He has this !!


Kefyalew Tefera Erga mana hidhaa Qaalittii irraa bahee waggaa tokko xumure.

Suuraan kun yeroo inni hiikamu balbala Qaallittii irratti.

Qaama guutuu fuutee galtee(hidhamtee) miila kee lamaan gattee galtus kaayyoo fi akeekni ati itti qaamaa hir’atte dhalootaan galma gaha.

Sirni kalee siif jaallan biraa akkas godhe ammas itti jira.

Dábessá Gemelal

Good bel Gonder!!

ኤርሚያስ ለገሰ የኦሮሞ ብሄርተኞች ናቸው ኢሳትን ያዘጉት አለ?
👉 ኢሳት ለብዙ አመት ሲዋሽ ነበር
👉የኦሮሞ ብሄርተኞች ውሸታቸውን ሲያጋልጡ ነበር
👉በመጨረሻም ኢሳት በውሸት የስራ ዘርፍ 3ተኛ ሆኖ ዉድድሩን ጨረሰው።

አሁን ጥያቄው ኢሳት ውስጥ የተሰገሰጉ #እሳቶች የተበተኑት ኢሳት #ውሸታም ሚዲያ በመሆኑ ነው ወይስ የኦሮሞ ብሄርተኞች ጣልቃ ገብነት ነው?
በነገራችን ላይ ኢሳት ኮሜንት ከመስጠት አግዶን ነበር አሁንም እንደዛው #ኩራት_ኩራት አለኝ 😆😆