የኦሮሞ አርቲስቶች ቡድን ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ በሚሊኒየም ኣዳራሽ

“ሱናሚዉ”
የኦሮሞ አርቲስቶች ቡድን ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ በሚሊኒየም ኣዳራሽ

(ራዲዮ ኣፉራ ቢያ)
በኦሮሚያ ቄሮ ተቀጣጥሎ መላዉን ሃገሪቷ ያናወጠዉን ሱናሚ ካስነሱት መሃል ቀዳሚ የሆኑት የኦሮሞ ኣርቲስቶች ቡድን በፕሬዝዳንት ኢሳያስ ለሚመራዉ የኤርትራ ልኡካን በሚሊየነም ኣዳራሽ በሚደረገዉ የአቀባበል ስነ ስርአት ላይ የሙዚቃ ትርእቱን እንደሚያቀርብ ታወቀ። 
በሚቀጥለዉ እሁድ ለፕረዝዳንት ኢሳያስ ኣፈወርቂና በርሳቸዉ ለሚመራዉ የኤርትራ ልኡካን ቡድን ለመቀበል በሚሊየነም አዳራሽ በሚደረገዉ ስነ ስርአት ላይ ታዋቂዉን የኦሮሞ ሙዚቃ አቀንቃኝ አሊ ቢራን ጨምሮ እነ ሃጫሉ ሁንዴሳ፤ ቀመር ዩሱፍ፤ ኢቲቃ ተፈሪ፤ ገላና ጋሮምሳ፤ ታደለ ሮባ፤ ታደለ ገመቹና ጌታቸዉ ሐይለ ማሪያምን የመሳሰሉ በርካታ ሙዚቀኞች እንድሚያቀነቅኑ ታውቋል።
አሊ ቢራ በሙዚቃዉ ኣንዲነትንና ወዳጅነትን ለዘመናት (ሃቲ ኬኛ ቶኮ)እያለ ሲያቀነቅን ለህዝቦች ልእልናና ህልዉና የበኩሉን ኣስተዋጾ ከማንም በተሻለ መልኩ ሲያቀርብ የነበረ የጥበብ ሰው ነዉ።
ሓጫሉ ሑንዴሳ፤ ገላና ጋሮምሳና ኢቲቃ ተፈሪ በመባል የሚታወቁት የዚህ የሱናሚው የቁቤ ትውልድ ኣርቲስቶች በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን የኦሮሞ ህዝብ ያፈራቻቸዉ ስመ ጥርና እጅግ ተወዳጅ ኣርቲስቶች ዛሬ በኢትዮጵያ ዉስጥ ለምናየዉ የለዉጥ ጉዞ መስዋእትነት የከፈሉ ብርቅ ኣርቲስቶች መሆናቸዉ ይታወቃል።
ከጥቂት ሳምንታት በፍት የኤርትራ ልኡካን ሸገር ሲገቡ በአቀባበሉ ላይ አንጋፋዉ አርቲስት መሃሙድ ኣህመድ ከወቅቱ ጋር ሊሄድ የሚችል “ሠላም ሠላም” በሚል የቆየ የሙዚቃ ስልት ለምሽቱ ድባብ ግርማን ያጎናጸፈዉ መሆኑ ይታወቃል።

ለመጀመሪያ ጊዜ የኦሮሞ ወጣቶችን አለም ኣቀፍ የተቃዉሞ ትግል በተመለከተ ከጥቂት አመታት በፊት የኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ላቀረበላቸዉ ጥያቄ የቄሮን ትግል ከሱናሚ ጋር በማመሳሰል ነበር የገለጡት::

እኛም ይህን ለክብራቸዉ በተዘጋጀዉ ልዩ ስነ ስርአት ላይ ዝግጅቱን የሚያቀርበዉንና በዚያ ሱናሚ ዉስጥ ጉልህ ድርሻ የነበራቸዉን ወጣት ኣርቲስቶቻችንን ሱናሚው ቡድን ብለን ጠርትነዋል