የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (እነግ) የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባቀረባቸው አስፈፃሚዎችና ታዛቢዎች ላይ ነቀፌታና ቅሬታ አቀረበ።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (እነግ) የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባቀረባቸው አስፈፃሚዎችና ታዛቢዎች ላይ ነቀፌታና ቅሬታ አቀረበ።
 
የኢትዮጲያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በዚህ አመት ለሚካሄደው ስድስተኛ ዙር ምርጫ ማስፈፀሚያ የግዜ ሰሌዳ አውጥቶ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ይታወቃል። በዚሁ መሰረት የምርጫ አስፈፃሚዎችና ታዛቢዎችን በተላያየ ሁኔታ አዘጋጅቶ ምደብ ሰጥቷል።
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በዚህ የምርጫ አስፈሚዎች ላይ ያለውን ቅሬታና ነቀፌታ ለምርጫ ቦርዱ አቅርቧል። ይህን ቅሬታና ነቀፌታም የምርጫ አስፈፃሚና በምርጫ ቦርዱ ያቀረብዋቸው ታዛቢዎች ገለልተኛ አካል መሆናቸውንና ግዴታቸውን በተማኝነት በመወጣታቸው ላይ ያለውን ጥርጣሬ በምክነያት አስደግፎ ገልፆታል።. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከምርጫ ቦርዱ ባገኘው የምደብ ማስረጃ እንደ ገለፀው ለክልል የተመደቡት የምርጫ አስፈፃሚዎች ያልተመዛዘኑ መሆናቸውን ይገልፃል። በዚህ መሰረት የምርጫ ቦርዱ ለአማራ ክልል 552 አስፈፃሚዎች ያቀረበ ሲሆን ለኦሚያ ክልል ደግሞ 325 አስፈፃሚዎችን አቅርቧል። ይህም በፐርሰንት ሲገለፅ ለአማራ ክልል የተመደበው 38%፣ ለኦሮሚያ ክልል 22%፣ እንዲሁም ለአፋር ክልል 3%፣ ለሶማሌ ክልል 4.03%፣ ለደቡብ ህዝቦቾ ክልል 11.3%፣ ለሀረሪ ክልል 2.29%፣ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 0.97፣ ለፊንፊኔ 11.67%፣ የድራ ደዋ 2.22% ለሲዳማ ክልል 3% የሚሆን በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ተመድቧል።
 
በዚህ ምደብ ላይ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ባቀረበው ቅሬታ ኦሮሚያ በመሬት ስፋትና በህዝብ ብዛት ቀዳሚ ሆና እያለች በዚህ ምርጫ ላይ የአንድ ብሄርና የአንድ ቋንቋ የበላይነት የተንፀባረቀበት ምድብ በመሆኑ የምርጫ ቦርዱ የህዝብን አደራ መካዱን ይገልፃል በማለት ቅሬታውን አቅርቧል። የምርጫ ቦርዱ አደራን መሸከም ብቻ ሳይሆን በህዝብ እየቀለድ ስለህነ ተልዕኮዉን በብቃት መወጣት አለበት፣ ተልዕኮዉን በብቃት የማይወጣ ከሆነ ህጋዊ በሆነ መንገድ ተልዕኮዉን መወጣት ለሚችል አካል አሳልፎ መስጠት ለበት። ከዚህም ሌላ ኦነግ ያቀረበው ቅሬታና ነቀፊታ በሁለት የኦሮሚያ ዞኖች ማለትም በቄለም ወለጋና በምዕራብ ጉጂ ምንም ምድብ አለመኖሩ ነው። ይህ በንድህ እያለ የኦሮሚያ ዞኖች የተጣጠነ ምድብ እንደሌላቸው በመግለፅ እንደምሳሌ የጅማ ዞን 53 ሰዎች ምርጫ ለማስፈፀም ተመድበው አንደ ቄለም ወለጋና ምዕራብ ጉጂ ያለምድብ ቀርተዋል።
 
ኦነግ እንዳቀረበው ማስረጃ ለቦረና ዞን አንድ ሰው፣ ለቦኖ በደሌ አንድ ሰው፣ ለምስራቅ ወለጋ ሁለት ሰው ለምዕራብ ወለጋ ሰባት ሰው፣ ለሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሰባት ሰው መቅረቡ ነው። ኦነግ ህንን መሰረት በማድረግ ቅሬታውን ሲያቀርብ የምርጫ ቦርድ ታማኝነቱን፣ ነፃ መሆኑን፣ ለሃቅ መስራቱን፣ በህጉ መሠረት ሃላፊነቱን አለመወጣቱን በጥርጣሬ ውስጥ ነው በማለት ገልጿል። በመቀጠልም ኦነግ ባገኘው ማስረጃ እንደገለፀው በምርጫ ቦርዱ ምደብ ውስጥ የአንድ ቋንቋ የበላይነት መታየቱ ነው። እሱም አማረኛ የሚናገሩት 60-59% ሲሆኑ አፋን ኦሮሞ የሚናገሩት 20.7% ብቻ ስለሆኑ ምደባው ወደ አማረኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ያደላ በመሆኑ ቅሬታ አቅርቧል። ከዚህም ሌላ የምርጫ አስፈፃሚዎችና ታዛቢዎች የምርጫ ቦርዱ ለኦሮሚያ የመደበው ከ325 ሰዎች ውስጥ አፋን ኦሮሞ የትውልድ ቋንቋቸው የሆኑት 84ቱ ብቻ ሲሆኑ አማረኛ የትውልድ ቋንቋቸው የሆኑት ግን 223 ሰዎች ናቸው። የትውልድ ቋንቋቸው ትግረኛ የሆኑት ደግሞ 6 የሚሆኑ ሰዎች በምርጫ አስፈፃሚነት በኦሮሚያ ተመድበዋል። ለኦሮሚያ ክልል የተመደቡት የምርጫ ታዛቢዎችና አስፈፃሚዎች ውስጥ 6 ሰዎች በጭራሽ አፋን ኦሮሞ የማይችሉ ናቸው። ኦነግ ይህም ትክክል እንዳልሆነ ገልፆ የምርጫ ቦርዱ ስርዓት ያለው ምድብ እንዳልሰጠ በማስረጃ አስደግፎ ለምርጫ ቦርድ አስገብቷል።
 
ኦነግ ባገኘው ተጨማሪ ማስረጃ ቅሬታና ነቀፌታውን አቀናብሮ ሲያቀረብ እንደ አስፈፃሚዎች ወይም ታዛቢዎች ለኦሮሚያ የተመደቡት ሰዎች ብዙዎቹ በተላያዩ ሴክተሮች የሚመሩ የመንስት ሰራተኞች መሆናቸው ነው። ይህም ልክ እንዳልሆነና ምድቡ ለገዢው የመንግስት እያደላ ያለ መሆኑን ኦነግ አመላክቷል። በምሳሌ ሲገልፅ ኦነግ ኢሉ አባቦራ ላይ የኦሮሚያ ልማት ማሀበር ሂሳብ ሰራተኛ የሆነ ሰው እንደ ምርጫ ታዛቢና አስፈፃሚ ሆኖ ቀርቧል። የኦሮሚያ ልማት ማሀበር የገዢው መንግስት አካል ስለ ሆነ ነፃ ሆኖ ምርጫ ማስፈፀም እንደማይችል ገልፆ ማንነታቸውና የስራ ድርሻቸው ያልተገለፁ ሰዎችም በዚህ ምድብ ውስጥ ይገኛሉ።
 
በመጨረሻም የምርጫ ቦርዱ አስፈፃሚዎችንና ታዛቢዎችን መርጦ ያቀረበበት መንገድ ግልፅ እንዳልሆነ፣ በዚህ ላይ ምርጫ ቦርዱ መልስ እንዲሰጥ፣ ምርጫ ቦርዱ እነዚህን ሰዎች ካቀረበበት መንገድ ውስጥ አንዱ የፊንፊኔ ሴቶች ማሀበር እንሆነ በመጥቀስ ይህ ማሀበር ከአሁን በፊት እንደ መንግስት አካል በመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ሲስራ ስለቆየ ገለልተኛና ነፃ አካል እንዳልሆነ ኦነግ ገልጿል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ስራ እድል ፈጣሪ ኮምሺን እንደሆነ በመግለፅ ኮምሺኑ የስራ ሃላፊነቱን ወደጎን በመተው ለስራ የመዘገባቸውን ሰዎች ለመንግስት በመስጠት የገዢው የፓርቲ አባል እንሚያደርጋቸው ግልፅ አድርጓል። በዚህ ምድብ ውስጥ በኦሮሚያ አንዳንድ የዞን ከተሞችን ለየት ባለ ሁኔታ ማቅረቡን ገልፆ በምን ምክንያት ለይቶ እንዳቀረባቸው ኦነግ ግልፅ አይደለም ብሏል። ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ነፃና ገለልተኛ እንዲሆን፣ ነፃና ታማኝ ሆኖ የሚጠበቅበትን ስራ እንዲሰራ፣ በዚህ ሀገር የፖለቲካ አካላት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው መሆኑን በመረዳት ግዴታውን እንዲወጣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አሳስቧል።
OLF,