Ethiopia: የኢትዮጵያ መንግስትና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስምምነት የጋራ መግለጫ

Ethiopia: የኢትዮጵያ መንግስትና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስምምነት የጋራ መግለጫ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ዶር. ለማ መገርሳ የሚመራውና የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር. ወርቅነህ ገበየሁ የሚገኙበት የልዑካን ቡድን፣
በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀ-መንበር ኣቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመራውና ኣቶ ኢብሳ ነገዎ፣ ኣቶ ኣቶምሳ ኩምሳ፣ ኣቶ ቶሌራ ኣደባና ኣቶ ገመቹ ኣያና የሚገኙበት የልዑካን ቡድን ነሃሴ 7 ቀን 2018ዓም በኣስመራ ኤርትራ በመገናኘት ወንድማዊ መንፈስ በተንጸባረቀበትና በሙሉ መተማመን በተካሄደ የእርቅ ውይይት ከዚህ በታች ያሉ ስምምነቶችና መግባባቶች ላይ ተደርሷል።

ሁለቱም ቡድን ስለኦሮሞና ኦሮሚያ እንዲሁም ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በውይይት ኣብረው ለመስራት ተስማምተዋል።

ለረዥም ዓመታት በኦነግና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል የነበረው ጦርነት ተገትቶ፡ ካሁን በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረው ሁኔታ ኦነግ በሃገር ውስጥ በግልጽ ሊሰራ የሚያስችለው መሆኑ ከግንዛቤ ገብቶ፡ ትግሉን በሰላማዊ መንገድ እንዲቀጥል ከስምምነት ተደርሷል።

በመጨረሻም ከስምምነት የተደረሰባቸውን ጉዳዮች ስራ ላይ እያዋሉ ምርመራና ጊዜ የሚጠይቁትን ቀስ በቀስ ለመጨረስ በቀጣይነት ከፍጻሜ የሚያደርስ ኮሚቴ በኣስቸኳይ እንዲቋቋም ተስማምተዋል።

ለማ መገርሳ አስመራ ገባ?

በሃምሌ ወር ወደ አሜሪካ ከመምጣቴ በፊት ፈረሰኛው የቃጅማ ጊዮርጊስ ምነው እግሬን በሰበረው ኖሮ? ስንት ነገር አመለጠኝ? ለማንኛውም የአባኦ(OLF) እና የዳዴኡኦ (OpDO) ውይይት የተሳካ እንዲሆን እመኛለሁ። ለማ መገርሳ ማለት የኦሮሞን ህዝብ ትግል አንድ እርምጃ ወደፊተ ያራመደ እንደመሆኑ የማይግባቡበት ምክንያት አይኖርም ብዬ ተስፋ፡አደርጋለሁ።

ቶሎ ወደ አስመራ መመለስ አለብኝ።

ኦቦ ዳውድ ወደ አገሩ የሚገባ ከሆነ ከታሪክ ሰሪው ጋር አንድ ታሪክ ጸሃፊ አብሮ መጉዋዝ አለበት። “ዳውድ ኢብሳ” የሚል ወፍራም መጽሃፍ ታይቶአችሁ ከሆነ አልተሳሳታችሁም። በአመት ሁለት መጽሃፍ መጻፍ አለብኝ። የ49 አመት ሰው ነኝ። ከጊዜ ጋር መሽቀዳደም አለብኝ። ትናንት በር ከፍቼ ከቤት ስወጣ እርጅና እንደ ታማኝ ውሻ ደጃፌ ላይ ተኝቶ አየሁት። እና የሞቀ ሰላምታ ሰጥቼው አለፍኩ።

Tesfaye Gebreab