የኦሮሞ ትግል ግብ ነጻነትና እኩልነት ስለመሆኑ ይህ ጥሩ ማስረጃ ነዉ::

የኦሮሞ ትግል ግብ ነጻነትና እኩልነት ስለመሆኑ ይህ ጥሩ ማስረጃ ነዉ::

“ጥብቅና ከቆሙልኝ አራቱ ጠበቆቼ ከአንደኛው ጋር ብቻ አንተዋወቅም። ሁለተኛ አሁን ባለው የፖለቲካ አሰላለፍም በጣም በተለያየ የፖለቲካ አሰላለፍ ውስጥ ነን ያለነው። አሁን በዋነነት ሁለት ጎራዎች ነን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለነው። ሁለት ጎራ ውስጥ ነው ያለነው። የፖለቲካ አመለካከቴን አይደግፉም እነዚህ ሰዎች። ሶስተኛ አሁን በዘመኑ አነጋገር በብሔር ማንነትም አንገናኝም። ከሁለቱ ጋር ደግሞ በሃይማኖትም አንገናኝም። ግን ይህን ሁሉ ነገር ቦታ ሳይሰጡት ይህ ጉዳይ የፍትህ ጉዳይ ነው፤ ለዚህ ሰውዬ ፍትህ ሊጓደልበት አይገባም ብለው ለሙያቸው ብለው ከጎኔ መቆማቸው ብዙ ያስተማረኝ ነገር ነው። ይኼ የኢትዮጵያን ፖለቲከኞች ማስተማር ይመስለኛል። የኢትዮጵያን ጋዜጠኞች ማስተማርያ ነው። ከዚያም አልፎ ህዝብን ማስተማር አለበት። የተለያየ ቋንቋ እንናገራለን፤የተለያየ ሃይማኖት አለን፤ የተለያየ ፖለቲካዊ አመለካከት አለን። በዚህ መሃል ግንኙነታችን ምንድነው የሚለውን ብዙ ነገር ያስተማረን ይመስለኛል። ያን ሁሉ ልዩነት ወደ ጎን ትተው ነው ከኔ ጋር የቆሙት። እውነቴን ለመናገር ፍትህ እኔ ላይ ሲጔደል እኔ አልነበርኩም የምቆጨውና የምበሳጨው፤ እነሱ ነበሩ። ••• በጣም ራሽናል የሆኑ ሰዎች ናቸው። ምክንያታዊ ሰዎች ናቸው። ፖዘቲቭ ሰዎች ናቸው። እና እነሱም እኔን በጣም አስተምረውኛል። ሁሉም ህብረተሰብ ከእነሱ ብዙ ትምህርት መቅሰም ያለበት ይመስለኛል። ለኔ ብለውም አይደለም እንደ ግለሰብ፤ ለፍትህ ብለው፣ ለሙያቸው ነው የቆሙትና መመስገን እና እውቅና ማግኘት ያለባቸው ይመስለኛል በዚህ በጎ ተግባራቸው።”
አቶ ልደቱ አያሌው በአባይ ሚድያ ከተናገሩት

1 Comment

  1. “… ለዚህ ሰውዬ ፍትህ ሊጓደልበት አይገባም ብለው ለሙያቸው ብለው ከጎኔ መቆማቸው ብዙ ያስተማረኝ ነገር ነው።” ኦሮሞች ነፍጠኛ በሚመራት ቅኝ ገዢዋ ኢትዮዽያ ፍትሕ አይጏደል ብለዉ ቢታገሉለትም አቶ ልደቱ አያሌው ግን እስከ አሁኑዋ ጊዜ ድረስ የምንሊክን ጨካኝ ወረራ እና ጭፍጨፋ ደጋፊ በመሆኑ ከነዚሕ ለፍትሕ ተሟጋች ኦሮሞዎች ተማርኩ የሚለዉ ምን እደሆነ አልገባኝም። እውነት ፍትሕ አይጏደል እንደ አቶ ልደቱ አያሌው ላሉ ለአቢሲኒያዎች የሚያሳስባቸዉ ከሆነ ፥ የፍትሕ መጏደል መነሻ መሰረት የሆነዉን የጨካኙ እና የአረመኔዉን ምኒሊክ የቅኝ ግዛት ወረራና ጭፍጨፍ በማዉገዝ መጀመር አይገባቸዉምን? ለ፻፶ ዓመታት በሗላ ቀር ነፍጠኛ ቅኝ ግዛት ስር በመዉደቃችን ፍትሕን እና ነዓነትን ስለምወድ ብቻ ሣይሆን እኛ ኦሮሞዎች በተፈጥሮ ስብዕና እና ፍትሕ ለሰው ዘር ቀርቶ ለእንሰሳ እንዲጏደልበት አንፈቅድም። ከምኒሊክ አፍቃሪ አቢሲኒያዎችም አንዱ ግዙፍ መለያችን ይህ ነው።

Comments are closed.