የኦሮሞ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ላይ የተደረገውም ከዚህ የተለየ አይደለም።

የኦሮሞ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ላይ የተደረገውም ከዚህ የተለየ አይደለም። ጃዋር መሀመድ አስክሬንን ወደ አዲስ አበባ መመለስ በሚል ክስ ተጀምሮ
ወጣቶችን ግብፅ ድረስ ልኮ ማሰልጠን የሚል የፈጠራ ክስ ቀርቦበት ከታሰረ ሶስት ወር አለፈው። ጃዋርን ከፖለቲካ ምህዳሩ ለማውጣት ያልተሞከረ ነገር አልነበረም። መጀመሪያ አብይ አህመድ ጃዋርን ጠርቶ ላንተ ከፖለቲካው ይልቅ ወጣቶችን ማብቃቱ ላይ ብታተኩር ብዙ ትጠቅመናለህ። በመቶ ሚሊዮን ብሮች ስራ ማስኬጃ አስፈላጊው ገንዘብ ይመደብልሃል ብሎት ነበር። ጃዋር አለሰማህም አለው። ብዙ የቀድሞ “ታጋዮች” እዚህ ግባ በማይባል ጥቅማ ጥቅም ህሊናቸውን ሲሸጡ ጃዋር የምታገልለት ህዝብና አላማ አለኝ አለ። በገንዘብ ሊደልለው እንደማይችል የተረዳው አብይ ጠዋት ፓርላማ ላይ ዛቻ አሰምቶ ከሰአት ወደ ሶቺ (ራሺያ) ሲሄድ የጃዋር ጥበቃ በሌሊት እንዲነሳ ትእዛዝ ሰጠ። በጉዞው ላይ የሰሜን መአከላዊን ፖሊቲካል ኢንትሪግ የሚግተው ዳንኤል ክብረትም አብሮት ነበር። አብይ ከራሺያ መልስ እቅዱ ተሳክቶ ጃዋር የሌለባትን utopia እንቀላቀላለን የሚል ተስፋ ነበረው። አልሆነም። ነገሩ የገባው ጃዋር ሴራውን ለህዝብ አሳውቆ ህይወቱን አተረፈ። በነገራችን ላይ የግድቡ ጉዳይ ላይ አሜሪካ በአደራዳሪነት እንድትገባ የተሰማማው በዚሁ በሶቺው ስብሰባ ላይ ነበር። ምናልባት ቀልቡ የጃዋር ጉዳይ ላይ ስለነበር ጥቅምና ጉዳቱን የማሰላሰያ ጊዜ አላገኘ ይሆናል። አብይ ጃዋርን በፖለቲካ እውቀት ፤ ግንዛቤና ማህብራዊ መሰረት ብዛት ፈፅሞ ሊገዳደረው የማይችለው mortal enemy መሆኑን ይረዳል። ያለው ብቸኛ መንገድ በአጋጣሚ እጁ ላይ የወደቀውን የፀጥታ ተቋም ተጠቅሞ ወይ እሰከ ወዲያኛው ማሰናበት ወይ ማሰር ነው።
 
በገንዘብና በግድያ ሙከራ አልበገር ያለው ጃዋር ፖለቲካውን ለመቀላቀል ወስኖ ዜግነቱን regain ለማድረግ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀመረ። በዚህ የተደናገጠው አብይ ጃዋር የአሜሪካ ፓስፖርቱን መልሶ ማድረግ ያለበትን ሁሉ ቢያጠናቅቅም እንደ ኢትዮጵያ ዜጋ የፅሁፍ እውቅና ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀረ። በሶስቱ መንገዶች አልሳካ ያለው ሃይል ሃጫሉ ላይ እርምጃ ወስዶ ጃዋርና የኦሮሞ ተቃዋሚዎችን ባጠቃላይ ከፖለቲካ ምህዳሩ የማውጣት መላን ዘየደ። ለማመጣጠን ያህል ለስልጣን ያን ያህል ስጋት የማይሆኑ ሌሎችንም መረቀበት። የሆነው ይህ ነው።
ዛሬ የኦፌኮ ምክትል በቀለ ገርባና በርካታ አመራሮች ዘብጥያ ወርደዋል። ከኦነግ አብዲ ረጋሳና ሚካኤል ቦረንን ጨምሮ ሶስት የስራ አስፈፃሚ አባላት እንዲሁም በርካታ የአመራር አባላት በሃሰት ክስ እስር ቤት ታጉረዋል። በተለይ በኦሮሚያ ስጋት ይሆናሉ ተብለው የሚታሰቡ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ወጣቶች bogus በሆነ ክስ እስር ቤት ተወርውረዋል። እስር ቤቶች አልበቃ ብለው ትምህርት ቤቶች እስር ቤት ሆነዋል። በኢህአዴግ ጊዜ ይደረግ እንደነበረው ፓርቲዎች ውስጥ ሰርጎ ገብ በማስገባትና እርጥባን በመወርወር ፓርቲዎችን የማፈራረስ ስራ በስፋት ይታያል። አማራጭ ሃሳብ የሚያቀርቡ ሚዲያዎች ባጠቃላይ ተዘግተው “ከአመት አመት አንተን ነው ማየት” የሚሉ አምልኮተ አብይ ውስጥ ብቻ ቀርተዋል።