የኦሮሚያ ፖሊስ: Tigiroonni Magaalaa Ambootti uuffataPoolisii Oromiyaa uffachuun uummata saamaa kan turan hirmaannaa uummata fi poolisii magaalattiin too’annaa jala oolan
“ጎይቶም በርሄ ፣ ገ/ኪዳን ሃዱሽና ሀይሌ ፍሰሃ በአምቦ ከተማ የኦሮምያ ፖሊስን ዩኒፎርም በመልበስ በርካታ ዝርፊያና ሰው ድብዳባ ላይ ተሰማርተው በህዝብ ጥቆማ ተይዘዋል ”
Via: Yaya Beshir
Then the ‘fake news’ of the regime described as

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአምቦ ከተማ የኦሮሚያ ፖሊስ ድንብ ልብስን በመልበስ ህብረተሰቡን ሲዘርፉ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።
የአምቦ ከተማ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው፥ በዚህ ተግባር ላይ ተሰማርተው የተያዙት ተጠርጣሪዎች ሶስት ናቸው።
ተጠርጣሪዎቹ በከተማዋ ነዋሪዎች ላይ የተለያዩ አካላዊ ጉዳት ማድረሳቸውን እና የዝርፊያ ወንጀሎችን መፈፀማቸውንም ፅህፈት ቤቱ ገልጿል።
ሶስቱ ተጠርጣሪዎች ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ የኦሮሚያ ፖሊስ አድማ በታኝ ሀይል የደንብ ልብስን በመስረቅ ዘረፋ ሲያካሂዱ ነበር ያለው ፅህፈት ቤቱ፥ ይህም በኦሮሚያ ፖሊስ ላይ ጥርጣሬ እንዲኖር አድርጎ እንደነበረ ገልጿል።
ግለሰቦቹ በትናንትናው እለት ታህሳስ 19 ቀን 2010 ዓ.ም ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ በተለመደው መልኩ ዝርፊያ ለመፈፀም በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ የከተማዋ ህብረተሰብ ባደረገው ርብርብ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አስታውቋል።
ፅህፈት ቤቱ ህብረተሰቡ የኦሮሚያ ፖሊስ እና የወጣቶችን ስም ለማጠልሸት የሚንቀሳቀሱ አካላትን በንቃት እንዲከላከል አሳስቧል።
Source: fanabc