የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ በምዕራብ ኦሮሚያ ስለተቋረጠው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት በድጋሚ ይቅርታ ጠይቀዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ በምዕራብ ኦሮሚያ ስለተቋረጠው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት በድጋሚ ይቅርታ ጠይቀዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በሸገር ኤፍ 102.1 የሬድዮ ጣቢያ ሲናገሩ እንደተደመጡት የአግልግሎት መቋረጡ መንግስት በአካባቢው ፀጥታና ደህንነት ለማስፈን እየወዳሰደ ካለው እርምጃ ጋር በተያያዘ መሆኑን ዳግም አስታውሰዋል።

የኢተርኔት እና የስልክ አገልግሎቱ መቼ ነው የሚጀምረው ተብለው በሬድዮ ጣቢያው የተጠየቁት ወ/ሪት ፍሬህይወት ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል፦

“ይሄ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኃላ ዝም ብለን አላለፍንም ፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በተለይም ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጋር ውይይት አድርገናል እዛ አካባቢ ያለው ማህበረሰብ በቂ መረጃ ስለወረርሽኙ እንዲያገኝ አስፈላጊው ጥረት እንደረግ፤ በእኛም በኩል መውሰድ ያለብንን ነገር ካለ ውይይት አድርገናል። ስለዚህ ከሚመለከታቸው የደህንነት አካላት በአካባቢው ያለውን የፀጥታና ደህንነት ችግር ከተፈታ ወይም መከፈት ካለበት የቴሌኮም አገልግሎቱ ፤ አቅጣጫ ሲሰጠን እኛም እርምጃ የምንወስድ ይሆናል። አሁን ያለው በዚህ ሁኔታ ላይ ነው። ይህን ነው ልል የምችለው።”


Raji A Dinka


People just want to survive this pandemic, this sociopath dude blocked the Internet and phone. Abiy is too weak, irresponsible, ill-equipped, self centered and incompetent to handle this crisis. #Abiyvirus #COVID_19 #unblockinternet. #wollegga #Guji