የኢትዮጵያ የከፍታ ዘመን!

“የኢትዮጵያ የከፍታ ዘመን”!!
 
ኢትዮጵያ በዘመኗ ገጥመዋት የማያዉቅ ቅርቃር ዉስጥ ናት ብሎ ብዙ አዋቂዎችና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች እያስጠነቀቁ ናቸዉ፡፡ ከሁሉም በላይ ሁለት ነገሮች በጣም ያሳስቡኛል፡፡ የአለም አቀፍ ክራይስስ ግሩፕ ኢትዮጵያን ከዓለም በሚቀጥለዉ አመት ከፍተኛ ግጭቶች ከሚያስተናግዱ ሀገሮች ከአፈጋንስታን ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ አስቀምጠዋል፡፡ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ድርጅቶች ኢትዮጵያ በ2021 ምንም ዓይነት የኢኮኖሚ እድገት አታሳይም ወይም እድገተዋ ዜሮ ፕረስንት መሆኑን የጥናት ዉጤቱን አስቀምጠዋል፡፡
 
ኩሁሉም የሚያሳዝነዉ ደግሞ
 
1. በኦሮሚያ ላለፉት ወደ ሶስት ዓመታት ድሀዉ ገበሬ ጎጆዉ እየተቃጠለ ሰዎች በማንነታቸዉ ብቻ ከፍተኛ ግድያ ተፈጽመዋል፡፡
2. የቅማነት ህዝብ የአገዉ ህዝብ የጉሙዝ ህዝብ ላይ ከፍተኛ የዘር ጭፍጨፋ ተከናዉነዋል፡፡
3. የሲዳማ የወላታ ህዝቦች መፍታቸዉን በመጠየቃቸዉ ተጨፍጭፈዋል፡፡
4. ከአማራ ክልል ባላስልጣናት ጀምሮ እስከ ዒተማጆር ሹም እና ዉዱ አርትስት እና የሰብዓዊ መብት ተመዋጋች ሀጫሉ ሁነዴሳ ድረስ የፖለቲካ ግድያዎች ተጧጥፎ ቀጥለዋል፡፡
5. በትግራይ ክልል ላይ ለማሰብ እንኳን በሚያዳግት መልኩ የጠላትን የሻቢያን ነብሰ በላ ጦር በማስገባት በአረብ ድሮን ጭምር የጦር ወንጀልና ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል መንግስት ነኝ በሚል አካልና በጃሌዎቹ ተፈጽሟል፡፡ የሀገር ነብረት ወድሟል፡፡ ተሰርቋል፡፡
6. ሕዝብ ማሪዎቼ ናቸዉ ብሎ የተከተሏቸዉ ተዋቂ ፖለቲከኞች ታስሯል፡፡የኦረሞ ወጣቶች ሞትና ዕስር ከልክ ያለፈ ነዉ፡፡
ይሄ ሁሉ ሆኖ ሳለ በከፍታ ዘመን ነን ካዚህ እንዳንወርድ በቤተመንግሰቱ ባለሟል ዲያቆን ነግሮዉናል፡፡
የህዝባችን ስቃይና ሞት የኢትዮጵያ የከፍታ ዘመን ከሆነ ይህ ኢትዮጵያዊ ማነዉ???!!! የህችስ ኢጥዮጵያ???? ግዜ ደጉ መልስ ይስጠናል!!!!!!!!