የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የጂቡቲ መሪዎች የጅማ ዩኒቨርሲቲ የሜዲካል ማዕከልን መረቁ

የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የጂቡቲ መሪዎች የጅማ ዩኒቨርሲቲ የሜዲካል ማዕከልን መረቁ

የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ጅቡቲ መሪዎች የጅማ ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን 131 የህክምና እጩ ምሩቃን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 2 ሺህ የድህረ ምርቃ ፕሮግራም ተማሪዎችን አስመረቁ።

Via: FBC


የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የጂቡቲ መሪዎች የጅማ ዩኒቨርሲቲ የሜዲካል ማዕከልን መረቁ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጅማ ዩኒቨርሲቲ የሜዲካል ማዕከል በዛሬው እለት በይፋ ተመርቆ ተከፍቷል።

ጅማ ዩኒቨርሲቲ የሜዲካል ማዕከልን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽርና የጅቡቲ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ ናቸው በይፋ መርቀው የከፈቱት።

የሜዲካል ማዕከሉ 800 የመኝታ ክፍሎች ያሉት ሲሆን፥ በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል ለሚገኙ ከ20 ሚሊየን በላይ ሰዎች የህክምና አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል።

ማዕከሉ እንደ ደቡብ ሱዳን ላሉ ጎረቤት ሀገራትም አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ የተገነባ መሆኑም ተነግሯል።

ዩኒቨርሲቲው ያስገነባው ይህ የሜዲካል ማዕከል በጤናው ዘርፍ የምርምር፣ የማስተማሪያ እና የማህበረሰብ አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል።

በተያያዘ ዩኒቨርሲቲው 131 የህክምና እጩ ምሩቃን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 2 ሺህ የጤናና የድህረ ምርቃ ፕሮግራም ተማሪዎችን በማስመረቅ ላይም ይገኛሉ።

በአልአዛር ታደለ


Preezdaantiin Jibuutii Ismaa’eel Oomar Giillen Jimmaa galaniiru.

Buufata Xiyyaaraa Abbaa Jifaaris yammuu ga’an muummee ministiraa Dooktar Abiy Ahimad dabalatee hoggantoonni olaanoon simannaa taasisaniifiru.

በጋራ የመኖሪያ ቤት ልማት ግንባታ ከእርሻ መሬታቸዉ የተነሱና በኮዬ አቦ አካባቢ የሰፈሩ አርሶ አደሮች በርካታ ችግሮች እያጋጠሙን ነዉ አሉ፡፡
በተለያዩ ምክንያቶች የካሳ ክፍያና ምትክ መሬት ያልተሰጣቸዉ አርሶ አደሮች ላለፉት ሰባት አመታት ኑሯቸዉን በአስቸጋሪ ሁኔታ እየመሩ መሆናቸዉን ይናገራሉ፡፡
አዲስ ቴቪ አርብ ህዳር 28/2011ዓ.ም