የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ60 አውሮፕላኖች ግዥ ሊፈፅም ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ60 አውሮፕላኖች ግዥ ሊፈፅም ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 60 አዳዲስ አውሮፕላኖችን ከ3 ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን አምራች ኩባንያዎች በቀጣይ 8 አመታት ውስጥ ለመረከብ የሚያስችል የግዥ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ

አየር መንገዱ እኤአ 2025 በያዘው እቅዱ ከቦይንግ፣ ከኤርባስ እና ቦምባርዲየር ከተሰኙ የአውሮፕላን አምራቾች ነው የአውሮፕላኖቹን የግዥ ውል የፈፀመው፡፡

(EBC) — በእቅዱ መሰረት ተጨማሪ አውሮፕላኖቹ ወደ ስራ ሲገቡ የአየር መንገዱን አመታዊ ትርፍ አሁን ካለበት 2.71 ቢሊዮን ዶላር ወደ 25 ቢሊዮን ዶላር ያሳድገዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት በ92 አውሮፕላኖች ከ100 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን፣ አዳዲሶቹ አውሮፕላኖች ሲጨመሩ ያለውን የአውሮፕላን ቁጥር ወደ 152 በማሳደግ የመዳረሻዎቹን ቁጥር ከ140 በላይ ያደርሳል ተብሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 12 ሺህ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን በአመት 8.8 ሚሊዮን ተጉዋዦችን በ100 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችና 19 የአገር ውስጥ በረራ እያስተናገደ ይገኛል፡፡

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ