የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር በይፋ ከግንቦት 7 ጋር መለያየቱን አስታወቀ፤

የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር በይፋ ከግንቦት 7 ጋር መለያየቱን አስታወቀ፤

በጎንደር ከተማ ዛሬ የድርጅቱ ሰብሰቢ አርበኛ እና ጋዜጠኛ መንግሥቱ እንዳሉት የግንቦት 7 አመራሮች ከአማራ ሕዝብ ጥቅም በተቃራኒ የቆመና አካሔዱም ሥልጣን እንጅ የአማራን ሕዝብ የማያካትት በመሆኑ አብረን መጓዝ አልቻልንም ብለዋል

ከኤርትራ የወጡት የድርጅቱ ወታደሮች ሙሉ በሙሉ ከግንቦት 7 ጋር ተለያይተው ከአርበኞች ግንባር ጋር መሆናቸውን አሳውቀዋል።

ግንባሩ ከአዲኃን፣ ከፋኖ አርበኞችና ከሌሎች የአማራ ድርጅቶች ጋር በመዋሐድ የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎችን ለማስመለስ እንደሚሠራ እንደሚታገል አስታውቆ የአማራ ሕዝብም ከጎኑ እንዲቆም ጠይቋል።

በዕለቱ አርበኛ ተፈሪ ካሳሁን፣ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ፣ አርበኛ ዘመነ ካሴ፣ አርበኛ ማዕዛው ጌጡ፣ አርበኛ አበበ ካሴ፣ አርበኛ ቴዎድሮስና ሌሎችም አርበኞች ተገኝተዋል።


ከብዙ በጥቂቱ፤

አበበ ካሴ፣ ተፈሪ ካሳሁን፣ መብራቱ ጌታሁን፣ ፓይለት መ/አለቃ ማስረሻ ሰጤ፣ መንግሥቱ ወ/ሥላሴ፣ ማእዛው ጌጡ፣ ቴዎድሮስ ፣ ክፈተው አሠፋ፣ ዘመነ ካሴ

Via: Muluken Tesfaw