የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጪው ምርጫ የሚካሄድበትን አውድ ለማሻሻል የሚያደርገውን ጥረት የሚመለከታቸው አካላት ሊያግዙት ይገባል!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጪው ምርጫ የሚካሄድበትን አውድ ለማሻሻል የሚያደርገውን ጥረት የሚመለከታቸው አካላት ሊያግዙት ይገባል!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፓሊስ ከህጋዊ የስልጣን ወሰኑ ውጪ ያለምንም የፍርድ ቤት ትእዛዝ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ጊቢ በር ላይ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላትን ለማሰር መሞከሩ ችግሮችን ለመፍታት የሚደረገው ጥረት የሚያሰናክል እና አሳሳቢም ከመሆኑም በላይ የህገመንግስታዊውን የቦርዱን ተቋማዊ ሃላፊነት እና ስልጣን ንቀትን ማሳየት ጭምር ነው።
~ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጪው ምርጫ የሚካሄድበትን አውድ ለማሻሻል የሚያደርገውን ጥረት የሚመለከታቸው አካላት ሊያግዙት ይገባል!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመጪው ምርጫ ዝግጅት በፖለቲካ ፓርቲዎች የሚነሱ አቤቱታዎችን በማሰባሰብ ችግሮቹን ለመፍታት ጥረት ሲደርግ እንደነበር ይታወቃል። ከነዚህም ጥረቶች መካከል የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትን ለአቤቱታዎቹ ምላሽ እንዲሰጡ ማድረግ፣ ምላሽ ላልተሰጠባቸው አቤቱታዎች የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ችግሮችን ለመፍታት ጥረቶችን አድርጓል። ከዚህም በተጨማሪ በቅርቡ በፓርቲዎች እና ከመንግስት ጋር በተደረገው ውይይት ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረቡ አቤቱታዎችን በማጠናቀር ያቀረበ ሲሆን ይህንን መሰረት አድርጎ ፓርቲዎች፣ ገዥው ፓርቲ እና ቦርዱ በጋራ በመገኘት ችግሮችን የሚፈቱበት የሶስትዮሽ ችግሮችን እና አቤቱታዎችን የሚፈታ አሰራር እንዲቋቋም ስምምነት ላይ መደረሱ ይታወሳል።
 
በዚህም መሰረት የመጀመሪያው የሶስትዮሽ ውይይት ትላንትና ታህሳስ 02 ቀን 2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቢሮ የተከናወነ ሲሆን የቤኒሻንጉል ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች እና ገዥው ፓርቲ እንዲሁም ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተገኝተዋል። በተቃዋሚ ፓርቲዎች በኩል የመንቀሳቀስ የአባላት እስር እና ሌሎች ችግሮች የተነሱ ሲሆን፣ በገዥው ፓርቲ በኩል የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ሆነው በወንጀል እና በትጥቅ ትግል መሳተፍ ችግሮች አሉ የሚል አቤቱታ ቀርቧል፡፡ በውይይቱ ማጠቃለያም በክልሉ ውስጥ ያለውን የፓርቲዎች ችግር ለመፍታት ቦርዱን ጨምሮ ሁሉም አካላት የሚሳተፉበት ቡድን ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል በመሄድ ለማጣራት ስምምነት ተደርጎ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡
ነገር ግን ውይይቱ ተጠናቆ በቤንሻንጉል ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት የምርጫ ቦርድ ዋና መስሪያ ቤት ጊቢን ለቅቀው ለመውጣት ሲሞክሩ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፓሊስ አባላት የእስር ሙከራ አድርገውባቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይህ ገንቢ እና ችግሮችን ለመፍታት ተስፋ ሰጪ አቅጣጫ ከነበረው በተቃራኒ በተከናወነው እርምጃ ከፍተኛ ቅሬታ ተሰምቶታል፡፡
 
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፓሊስ ከህጋዊ የስልጣን ወሰኑ ውጪ ያለምንም የፍርድ ቤት ትእዛዝ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ጊቢ በር ላይ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላትን ለማሰር መሞከሩ ችግሮችን ለመፍታት የሚደረገው ጥረት የሚያሰናክል እና አሳሳቢም ከመሆኑም በላይ የህገመንግስታዊውን የቦርዱን ተቋማዊ ሃላፊነት እና ስልጣን ንቀትን ማሳየት ጭምር ነው፡፡ ቦርዱ ችግሩን ለመፍታት ከሰአታት ጥረት በማድረግ ከአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን እና ከፌዴራል ፓሊስ ኮሚሽን በተገኘ እገዛ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፓሊስ ሃይል ከምርጫ ቦርዱ ዋና መስሪያ ቤት በር ላይ ከ3 ሰአት ቆይታ በኋላ አንዲነሳ ለማድረግ ቢቻልም የተከናወነው የህግ ጥሰት እና ተቋማዊ ስልጣንን አለማክበር እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ቀጣዩ ምርጫን ተከትሎ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በተደረገው ውይይት ገዥው ፓርቲም ሆነ መንግስት በመዋቅሮቹ የስነስርአት ደንብ አክብረው እንደሚንቀሳቀሱ በይፋ ያረጋገጡትን የሚቃረን በመሆኑ መስተካከል የሚገባው መሆኑን ያምናል፡፡
 
የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያቀርቧቸው አቤቱታዎች ላይ የሚደረገው የሶስትዮሽ ችግሮችን መፍታት ሂደት የሚቀጥል ሲሆን መጪው አገራዊ ምርጫ አለም አቀፍ ተቀባይነት ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በዚህ ሂደት አዎንታዊ ሚና እንዲጫወቱ ቦርዱ በአጽንኦት ያስገነዝባል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ


ሁልህም ፋሽስት ነበርህ፤ ነህም።
 
የፋሺዝምን መሠረተ ጠባያት ከህወሓት—ኢህአዴግ ሁኔታ ጋር በማሰናሰን የዛሬ 5 አመት ግድም “ፋሺዝም በኢትዮጲያ” በሚል ርዕስ በፌስ ቡክ ገጼ ላይ አውጥቼ ነበር። የነበረው ስርአት ፋሺስትነት ከጥያቄ የሚገባ አለነበረም፤ እንዲያውም በየትም ከታየው ያስንቃል።
እንዲህም ሲባል በህወሓት መራሹ የ27 አመታት ዘመን በኢትዮጲያ ለተፈፀመው ሰብአዊ ወንጀሎችና ዘረፋዎች አሁን አየሩን የያዘው ህወሓቶችን ብቻ የመወንጀል ተረክ ከሂሊናም ፣ ከይሉኝታም፣ ከሎጂክም የተፋታ ነው የሚል ሙግት አለኝ ። ሌሎች የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የነበሩት ስማቸውን ስለቀየሩ እንደ ጲላጦስ ከደሙ ንፁህ ነን ሊሉ አይችሉም ባይም ነኝ።
 
በስነ ጽሁፍ ዘርፍ የጣምራ ተረክ (co—narrative) የሚባል ነገር አለ። የትዳር ወይም የፍቅር ታሪካችንን ተጣማጃችንም የሚጋራው ነው —ይህ ነው co–narration የሚባለው— ለጠፋውም ለለማውም ይብዛም ይነስም ባለድርሻም ነው። ዛሬ የሚተረከው የህወሓት የሰቆቃ ታሪክም ለእኔ የተናጥል ወይም የብቻ ትረካ (sole narrative) ሳይሆን (co–narrative) ነው።
 
ኦህዴዶችን፣ ደህዴኖችን፣ ብአዴኖችን ትላንት የኢትዮጲያ ማረሚያ ቤቶች ከቶውንም ወደ ሰብአዊ ቄራነት ተቀይረው ዜጎች ሲቆራረጡ የት ነበራችሁ ብዬም እጠይቃለሁ። እነ ዓቢይ በግል በተፈፀመው የወንጀል ድርጊት ውስጥ አልተሳተፉም ቢባል እንኳ ከሀላፊነት አይወጡም። ምክንያቱም የፋሽስቱ ስርአት አካል ነበሩ። ሲፈፀም የነበረውም ከእነሱ እውቀት ውጪ አልነበረም። ከ1924—53 ዓም የቀድሞዋ ሶቪዬት ህብረትን ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ የገዛት ጆሴፍ ስታሊንን የተካው ኒኪታ ክሩስቼቭ በኮሚንስት ፓርቲው 20ኛ ጉባኤ ላይ ስለ ስታሊን ኃጢያት መዘክዘክ ያዘ (ክሩስቼቭ በስታሊን ዘመን የፓርቲው ፖሊት ቢሮና ባለሟሉ መሆኑ ልብ ይሏል)። በመሀሉ “ይህ ሁሉ ጉድ ሲፈፀም እርሶስ የት ነበሩ?” የሚል ድምጽ ከአልታወቀ ሰው በጉባኤው አዳራሽ ውስጥ ተሰማ። ክሩስቼቭ “ ማን ነው የጠየቀኝ?” አለ። ምላሽ የሰጠ አልነበረም። ማን ይፎገራል? ስታሊን ቢሞት የፍርሀቱ ድባብ ገና አልገፈፈም። ከጉባኤተኞቹ መልስ ያጠው ክሩስቼቭ “ጠያቅዬ አሁን ያለህበት ቦታ ነበርኩ” የሚል አስገራሚ ነገር ተናገረ። አንተ አሁን ፈርተህ ዝም እንዳልህ እኔም ያኔ እንዲሁ አለፍሁ ማለቱ ነው። ክሩስቼቭ በዘመነ ስታሊን ከሆነው “እኔ የለሁበት” ለማለት ሲዳዳ የገጠመው ተግዳሮት አድርባይነቱን በራሱ አንደበት እንዲመሰክር አስገደደው። ከተጠያቂነት ግን አያስመልጠውም።
 
ስታሊን ሞቶ በሌላ ስታሊን ባይተካ ኖሮ የክሩስቼቭ ቦታ ወህኒ ቤት ነበር፤ ‘ያ ሁሉ ሲፈፀም ባውቅም ለህይወቴ ፈርቼ ዝም አልሁ‘ የሚለውን የክሩስቼቭን ምክንያት በፍርድ ወንበር ላይ ለሚቀመጥ ዳኛ ትርጉም የለውም።
በእኛ የወንጀል ህግ በሌላ የተፈፀመ ጥፋትን በማንኛውም ምክንያት እያወቁ አለማሳወቅ በአባሪ ተባባሪነት ያስጠይል።
በህወሓት ኢህአዴግ ለተፈፀመው ዐቢይና ግብረአበሮቹ በግልና በወል ተጠያቂነት እንዳለባቸው አያከራክርም።
 
እነዚህ ወገኖች የህዝብን ተቃውሞ ተንተርሰው ወያኔን ስልጣን ቀሙት እንጂ ግፉን ሲቃወሙ አይታወቁም። እንኳን ትላንት ዛሬም የህዝብ ስቃይ ሲቆረቁራቸው አልታየም። እንዲያውም ባለፉት ሶስት አመታት ግድም ህወሓት በሌለበት የተፈፀሙ የትየለሌ መንግስታዊ ወንጀሎች ተጎርዶ በቤተመንግስት የቀረው የዐቢይ አህመድ ቡድን የነበረውን ፋሽስታዊ ስርአት አስቀጣይ እንደሆነ እንጂ የተለየ እንደሆነ የታየበት አይደለም።
እንዲህ ያለ ተጠየቅ የሚቀርበው ጠንጋራ የፍትህ ስሜት ከሌለን ነው። ወይም ማስተዋላችንን አደርባይነት ካልሰወረብን ነው። የዐቢይ ቀለብተኛ መጂኑኖች የ“ወያኔ ተላላኪ” ይሉናል ብለን የሂሊና ጥያቄ ከመጠየቅ ወደኋላ አንልም። ትላንትም ወያኔዎችን ፋሽስት ለማለት ድፍረት ነበረን። ወገናችን ሲጨፈጨፍ ዝም አላልንም። የታሰሩትን ፍቱልን ብለን ከአደባባይ ወጥተን ጮኸናል። ዛሬም ህዝባችን እየተገደለና እየተፈናቀለ ዝም አንልም ። ወንጀለኛው ቋንቋው መቀየሩ ለእኛ የሚያጽናና ነገር አይደለም።

Hawwii Daraaraa


በሙኒራ አብዱልመናን አዘጋጅነት በኢትዮትዩብ የሚቀርብላችሁ #አፈርሳታ መሰናዶ የዚህ ሳምንት እንግዳችን ቤቲ ታፈሰ በቅርቡ “እኔ እና የLTV ምስጢሮቼ” በሚል ርእስ ባሳተመችው አነጋጋሪ መጽሀፏ ላይ ባንዲራን በተመለከተ ስላሰፈረችው እና ብዙዎችን ስላስቆጣው ጽሁፍ የሚከተሉት ጥያቄዎች ቀርበውላት ነበር።
ሙሉ ቃለ ምልልሱን ለመከታተል፦