የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መንግስትና አገር ሽማግሎች በኦሮሚያ ጥቃት

የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መንግስትና አገር ሽማግሎች በኦሮሚያ ጥቃት ላይ የጋራ አቋም መግለጫ ይፋ አደረጉ
ጅግጅጋ(Cakaaranews)መክሰኞ መስከረም 23/ 2010ዓ.ም.የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መንግስት በጅግጅጋ ከተማ ካሊ1 አደራሽ ከክልሉ አገር ሽማግሎች ጋር በኦሮሚያ ጦርነት ዙሪያ አወያዩ፡፡በመድረኩ ላይም የክልሉ መንግስት ከፍተኛ አመራርና የክልሉ አገር ሽማግሎችም ተገኝቷል

በዛሬው እለት የክልሉ መንግስትና የክልሉ ሀገር ሽማሎችሁ በወቅታዊ ክልላዊ ጉዳዮችና በተላይ ኦሮሚያ በኢትዮጵያ ሶማሊ ህዝብ ላይ በቋሚነት እየፈፀመች ያለው ጥቃትና ጭካኔ የተሞላበት በደል ዙሪያ ውይይት ተካሄዷል፡፡የኢትዮጵያ ሶማሊ ህዝብ በቀድሞ አንባገነኑ የደርግ ሥርዓት ለማስወገድ የተደረገው ትግል ስማቸው፡ቋንቋቸው፡እምነታቸውና አኩሪ ባህላቸውም ሳይለወጡ ሀብታቸውና ነብሳቸው መፀዋትነት የከፈሉ ህዝብ ቢሆንም በአዲስቷ ኢትዮጲያ አዲስ የደርግ መንግስት ተቋቁሟል ብሎ በመድረኩ ላይ ሰጥቷል፡፡

በሌላ በኩል የክልሉ መንግሰት አሮሚያ በኢትዮጵያ ሶማሌ ላይ በቋሚነት የሚታወጃው ተከታታይ ጦርነት መንሰኤዎች እንደሚከተለው ገልፀዋል፡-1ኛ ኦሮሚያ የኢትዮጵያ ሶማሌ መሬት በኃይል ለመወሰድና ከጎሮቤት አገራት እንደሶማሊላንድና ሶማሊያ ጋር ግንኙነት በመፍጠርና እንደሁም የጎሮቤት አገራት ወደብ በመጠቀም ኢትዮጵያ የሚያፈራረሱበት ጦር መሳሪያ ለማስገባት ሲሆን በአሮሚያ ሴራ የክልሉ መንግስትና ህዝብ ከባድ ማቀብ ስለሆነበት ነው፡፡2ኛው የኦሮሞ ጦርነት በስተጀርባ ያለው ምክንያቱ ደግሞ በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልልን የፈጠረ ሰላምና ማረጋጋት እንደሁም በሻቢያ የጋራ መቀመጭያ የነበሩት ፀረ-ሰላም ኃይሎች እንደ አልኢተሓድ፡አልኢጃራ፡ኦቦ

(ኦብነግ)ኦነግና የመሳሰሉት ፅንፈኞች ኤርቴሪያ የሚትሰጠው ጦር መሳሪያዎችን በአንድ ጀልባ ሲትላክላቸው ስለነበርና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ስለተደመሰሱና የጦር መሳሪያዎች ማስገባቱ ስለታገደባቸው በኦሮሚያ ክልል ላይ ቁጭት ስላሳድባታል 3ኛው የኦሮሞ ጦርነት ምክንያቱ ደግሞ በቅርቡ አሮሞችሁ ሌላ ሸሚዝ በመልበስ የአዲስቷ ኢትዮጵያ ፍትህ፡እኩልነት፡ሰጥታና ልማትን ያጎፀፈው ኢህዴግን በቀላሉ ለመቀልበስና የፈዴራሊዝም ሥርዓትና የህግ የበላይኒናን ለመተራመስና አንባገነኑ የደርግ ሥርዓት ለማስመለስ ኦሮሚያ እያደረገች የነበረው ቀውስና ብጥብጥን በኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብና መንግስት ስለተወቀሱ ነው ተብሏል፡፡ከዚህ በተያያዜም የክልሉ መንግስት ኢትዮጵያነታችንም ከማንም ጀርባ ሆነን አንለምንም ብሏል፡፡

በተመሳሳይም ከአሁን በፊት በክልሉ የሚገኙ ወረዳዎችና ዞኖች ለመሄድ በሌላ ክልል ተቋርጦ ከረጅም ጉዞ በሆላ ሲደርሱ የነበሩ የክልሉ ወረዳዎችና ዞኖች በክልሉ መንግስት በአጭር ግዜ ውስጥ የተከናወኑ ዘርፈ-ብዙ ልማትን በተላይ መንገድና ድልድዮች በመገንባትና ሁሉም የክልሉ ወረዳዎችና ዞኖች በማስተሳሰሩና ከሌላ ክልል መዞሩ በክልሉ መንግስት ማቅረፉ በኦሮሚያ መንግስት ላይ ቁጭት ስለፈጠርበትና በተላይ በመንገድ መስረተ ልማት እጥረት በኦሮሚያ ክልል ተቋርጦ ሲገኝ የነበሩ የኢትዮጵያ ሶማሌ ወረዳዎች እንደ ለጋሂዳ፡ሰለሃድ፡ቁቢ፡መዩሙሉቆ፡ቀርሳዱላና ፊልቱ ወረዳዎች ከክልሉ ዋና ከተማ በመንገድ መስረተ-ልማትና በትላልቅ ድልድዮች ከማስተሳሰሩ ባሻገር የኢትዮጲያ ሶማሌ ክልል መንግስት በጥቅት አመታት ውስጥ በክልሉ ያከናወናቸው ትላሊቅ የውሃ ማቆሪያዎችና ሜጋ የመስኖ ግድቦችሁ ለግብሪና ምርትና ምርታማነትን ስለሚያገለገሉና ከኦሮሚያ ሲቀርብ የነበሩ አትክልትና ፊራፍሬዎችሁ በሶማሌ ክልል ገበያ እንዳይኖቸው የአሮሚያ ክልል መንግስት ለሶማሌ ገበያ የሚየቀረርቡት ምርት ትሊቅ ስጋት ስለሆነበት የኦሮሚያ ጦርነት አንዱ ምክንያት ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል የክልሉ መንግሰትና አገር ሽማግሎች በመድረኩ ላይም 8 የቱሊ ጉሌድ ወረዳ ልጆችና በሞያሌ ወረዳ 147 በሚትታወቅ አከባቢ 2 የሶማሌ ልጆች ከመኪና አውሪዶ በላይ ላያቸው ጋዝ በማርከፍከፍና ጭካኔ በተሞላበት እንደቡርማዎችሁ በእሳት የተገደሉት ልጆች ኦሮሚያ መንግስት የሀዘን መልእክት ባለመላካቸውን ሌላ ክፋት መሆኑም በመድረኩ ተገልፀዋል፡፡ሌላው በያቤሎ ሆስተፕታል ላይ እየታከሙ የነበሩትና በዶክተሮች በፊት ለፊት የታረዱት 8ቱ ሶዎችና በኢትዮጵያ ታሪክ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቅ በኣወዳይ ላይ በዘግናኝ መልክ በእሳት የተቃጠሉና የታረዱ18 ሶማሎች ሜቼም ከሶማሌ ህዝብና መንግስት ህልውና የማይጠፋ ቁሱል ከመሆኑ ባለፈ እስካሁን የት እንዳሉ ያልታወቁ 27 ግለሰቦችና በመከላኪያ ሰራዊት የተረፉትና በጅግጅጋ ከተማ ህክምና እየተከታተሉ የሚገኙ 300 ሶዎችና በአጠቃላይ የኦሮሚያ ክልል አመራርና ፀጥታ ኃይሎችሁ በሶማሌ ንፁሃን ዜጎች ላይ የፈጸሙት በደል፡ጭካኔና ኢ-ሰብዓዊ ድርግቶች በሶማሌ፡ በፈዴራል መንግስትና በሰብዓዊ ድርጅት የተመዘገቡና ከ ሁለቱ ክልሎች ወሰን ጋር የማይገናኝ ፀያፍ ድርጊት መሆኑን የክልሉ መንግስት አስሚሮበታል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ክልል አገር ሽማግሎች፡የክልሉ መንግስትና ብሎም የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.ከፍተኛ አመራሩ የኢትዮጵያዊነታቸው መብት የማይደራደርና በሌላ ሰበባሰበብ የማይሸፋፈን ጉዳይ መሆኑን እና በሶማሌነታቸው እንደሚኮሩም ተገንዝቦ የፈዴራሊዝም ሥርዓትም ሆነ ህግመንግስታችን ለማደፍረስ የሚመከር ማንኛውም አካላት ቀጥታ ጦርነት እንደሚያወጁና አፍሮ ለህግ እንደሚያቀርቡም አሳወቁ፡፡ በሌላ በኩል የክልሉ አገር ሽማግሎች፡የክልሉ የቀድሞ አመራር አባላትና የክልሉ የቀድሞ ፕሬዝደንቶች የክልሉ መሬት ሲፋት 353,000ኪ.ሜ2 መሆኑና በኢትዮጵያ ክልሎችም በቆዳ ሥፋት 2ኛ ክልል ሲሆን በህዝብ ብዛትም የኢትዮጵያ ሶማሌ ቤሔረሰብ 3ኛ ደረጃ እንደሚያዙና ፈዴራሊዘም ሥርዓት ከተቋቋመበት ቀን ጀምሮ የሀገራችን ሰላምና ፀጥታ ከመጠበቅና ከማስጠበቅም ከፍተኛ አስታዋፀኦ ያደረጉ ህዝብና መንግሰት መሆናችን ከማንም አልተሰወርም ብሏል፡፡

በተጨማሪም የአሮሚያ ክልል አመራር አባላት የኦሮሚያ ህዝብና መለሺያ አባላት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መሬት በጉልበት ለመያዝ እገፋፉና ተከታታይ ወረራዎችና ጥቃትም እየፈፀሙ እንደሚገኙም ተረጋግጧል፡፡ነገር ግን የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መንግስት እስካሁን የሀገሪቱ ህግ ከማክበሩ ባለፈ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተራችን አቶ ኃይለማርየም ደሳለኝ የሁለቱ ክልሎች ርዕሳን መስተዳደር ስምምነት ላይ የሁለቱ ክልሎች ሚዲያዎች የሀገሪቱ ሚዲያ ህግና ደንቦች እንድጠበቁና የተጋጩ ህዝቦች የማረጋጋት ሥራ እንደሳራ ያቀረቡ ጥሪ በማክበር ላይ ነን ሆኖም ግን ኦሮሚያ ክልል የራሳቸው ሚዲያ ተቋማት ከማንም ሳይደበቁ ሆን ብሎ የቀውስና የጦርነት መጠቀሚያ ሚዲያ ከማድረጋቸው ባሻገር በኦሮሚያ ክልል ውስጥና በአዋሰን አከባቢውች የሚኖሩ ሶማሌ ማህበረሰብን ከመጨፍጨፍና ከወረራ አልቆጠቡም ብሏል. በተያያም የክልሉ መንግስትና አገር ሽማግሎቹ በጭካኔ የተጨፈጨፉ ዞጎቻችን ከህልውናችን ሳይጠፋ ከአሁን ጀምሮ ኦሮሚያ በህዘባችን ላይ እያደረጉ ያለው ጥቃትና የሥርዓት አልበኝነት ወረራን ለአንድ ደቂቃ ያህል አንታገስም ብሏል፡፡በመጨረሻም የአትዮጵያ ሶማሌ ክልል አገር ሽማግሎች ኦሮሚያን እየጠበቃችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦች ቤሔራዊ ቃልኪዳን የሆነው ህግመንግስታችንና የፈዴራሊዝም ሥርዓታችን አደጋ መሆኑን ለፈዴራል መንግስት ጥሪ አቀርቧል፡፡

 

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል