የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲ እንጂ ዳግማዊ ደርግ እንዲመጣ አይፈልጉም!

የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲ እንጂ ዳግማዊ ደርግ እንዲመጣ አይፈልጉም!!!!

ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ፣ “ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 54 መሠረት፣ ምክር ቤቱን በትኖ፣ ሕገ-መንግሥቱን አግዶ፣ በአዋጅ አገሪቱን ማስተዳደር ይገባዋል፤ ሕገ-መንግሥቱም ይፈቅድለታል” ይላል። ይኸ የለየት የወታደራዊ አስተዳደር ቅጥፈት ነው።

ምክንያት፦

1. ማንም ማንበብ የሚችል ሰው ሊገነዘብ እንደሚችለው፣ አንቀጽ 54 ምክር ቤት ስለማፍረስ የሚናገረው አንዳች ነገር የለም።

2. አንቀጽ 54ም ሆነ ማንኛውም የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ የትም ቦታ ሕገ-መንግስቱን ስለመገደብ አይናገርም። የመገደብን ሥልጣንም ለጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ ለማንም ሌላ ባለሥልጣን አይሰጥም።

3. ምክር ቤት የሚፈርስበትና ካቢኔው በባላደራ መንግሥትነት ከ6 ወር ላልበለጠ ጊዜ የሚያስተዳድርበት አግባብ በአንቀጽ 60 የተቀመጠ ሲሆን፣ ይህንንም የሚያደርገው ፕሬዚዳንቱ እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አይደለም (አንቀጽ 60(2))። ፕሬዚዳንቱም ይሄን የሚያደርገው፣ ምርጫ ተካሂዶ፣ በውጤቱ መሠረት የወንበር ብልጫ ያላቸው ፓርቲዎች የጥምር መንግሥት ለማቋቋም መስማማት ሲያቅታቸው ነው። ከዚህ በተጨማሪ፣ በአንቀጽ 60(1) መሠረት ፓርላማው (ከነጠቅላይ ሚኒስትሩ) በስምምነት እራሱን አፍርሶ ሌላ ምርጫ እንዲካሄድ መጠየቅ ይችላል።

4. በአንቀጽ 60 መሠረት፣ ፓርላማው በፈቃዱ እራሱን ሲያፈርስ፣ ወይም ፕሬዚዳንቱ እንዲፈርስ ሲያደርጉ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምርጫ እስከሚካሄድ ባለው ጊዜ ውስጥ፣ የባላደራው መንግሥት መሪ ሆኖ ያገለግላል። የባላደራው መንግሥትም ሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ፣ እንኳን ሕገ-መንግሥትን የማገድ ቀርቶ፣ አንድም አዲስ የፖሊሲ ሃሳብ፣ አንዲትም ተራ የሕግ ረቂቅ ማዘጋጀት፣ ማሳለፍና መተግበር አይችሉም (አንቀጽ60(5))። የመንግሥት የዕለት ትዕለት ሥራ እንዳይስተጓጎል ክትትል ከማድረግና ተራ የቢሮ እንቅስቃሴን ከሚመለከቱ ተግባራት (eg. signing payrolls, etc) ባለፈ፣ ካቢኔውን እንኳን እንደ ሚኒስትሮች ምክር ቤት የመሰብሰብ ሥልጣን የለውም።

5. ‘ፓርላማ በትነን፣ ሕገ-መንግሥት ገድበን፣ በአዋጅ እናስተዳድር፣’ የሚለው ሃሳብ ፍፁም ሕጋዊ ተቀባይነት የሌለው አምባገነናዊ አሰራር ነው። ለመሆኑ ፓርላማ ከተበተነ፣ ማን ባወጣው አዋጅ ነው አገር ሊያስተዳድሩ የሚያስቡት? ነው ወይስ፣ በግል፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚፅፉት ትዕዛዝ (edict) ለማስተዳደር ነው የተፈለገው?

6. ሻለቃ ዳዊት፣ ድሮ በ1966/7 መንግሥቱ ኃይለማርያምን ያሳሳቱበትን ምክር፣ ዛሬም በአብይ ላይ ባይደግሙት ጥሩ ነው። ደርግ ያለ ምንም የህግ ሥልጣን፣ ፓርላማውን በትኖ፣ ሕገ-መንግሥቱን ገድቦ፣ ንጉሠ-ነገሥቱን ከሥልጣን አውርዶ፣ በደርግ ምክር ቤት አዋጅ፣ በፍፁም ፈላጭ ቆራጭነትና በሽብር ማስተዳደር የጀመረው፣ በእንደዚህ ዓይነት ምክር ተነሳስቶ እንደሆነ ለመረዳት አያዳግትም።

ሻለቃ ዳዊት፣ በሁለት ትውልድ ላይ አንድ ዓይነት የአምባገነናዊ ሽብር ጥፋት ለማድረስ ከመምከርና ከመሞከር ቢታቀቡ ጥሩ ነው። ትምህርት፣ ሥራና የረጅም ዕድሜ ተሞክሮ የማያስተምረውን ሰው ሞት ካላሰናበተው በቀር መቼም አይማርም።

በመሆኑም ሕዝቡ በያለበት እንዲህ ያሉ ፋሽስታዊ ምኞቶችን እስከመጨረሻው መፋለም ይኖርበታል።

#No_to_fascists#Not_in_my_generation #No_2_dictatorship_again!
#Qeerroo_Rules!

Tsegaye Ararssa



BNN Special Program: በኢትዮጵያ ነጻ አውጪ ግንባር ታጥቆ ሲንቀሳቀስ ፍቃድ ማን ሰጠው ልዩ የፖለቲካ ብቃት የታየበት Part 2


Ethiopia: ጥብቅ መረጃ – በብሄራዊ ደህንነት ያኖሩት አደገኛ መርዝ ዓላማ ምን ነበር?


Shukshukta (ሹክሹክታ) – የነጀነራል ክንፈ የቡጢ ስጋት | Kinfe Dagnew | TPLF | Isaias Dagnew | Abdi Illey