የኢሳት ጉዳይ:-ኢሳት ከአየር ላይ የወረደው በገንዘብ እጥረት አይደለም::

የኢሳት ጉዳይ:- ኢሳት ከአየር ላይ የወረደው በገንዘብ እጥረት አይደለም::
 
አሁን ባለው ሁኔታ ለአብይ አስተዳደር ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በላይ ትልቁ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ኢሳት ነው::
የአብይ የብልፅግና ፓርቲ ለመንግስት ሚዲያዎች ከሚመድበው በጀት ይልቅ በእጅ አዙርም ቢሆን ኢሳትን ቢደግፍ ይመርጣል::
በተለይ ምርጫው ሲቃረብ ለብልፅግና ፓርቲ ስልጣን መወጣጫ ትልቅ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ተደርጎ የሚወሰደው ኢሳት ነው::
በመረጃ መሰረት አሁን የተፈለገው ኢሳት በተወሰኑ ሰዎች ያጣውን የተዓማኒነት ችግር ለመመለስ ፋይናንስ አጠረኝ በሚል ከለውጡ ሀይል ጋር ግንኙነት የለኝም የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ነው::
ገለልተኛ መስሎ የህዝብን ቀልብ የመሳብ የፓለቲካ ሴራ መወጠኑን ውስጥ አዋቂዎች ያጋሩኝን እኔም ሹክ ልበላችሁ ብየ ነው::
እናም ወገኖቼ እራሳችሁን ከእንዲህ አይነት የፖለቲካ ሴራ ብትጠብቁ መልካም ነው::
እናም ከተወሰነ የፓለቲካ ጨዋታ በኃላ ኢሳት በቅርቡ ወደ አየር ይመለሳልና አትሸወዱ!!!
ኢሳት የብልፅግና አይን እና ጆሮ ነው::