አቶ ሙሴ አብርሃም፤ የአገው ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) የውጭ ግንኙነት ኃላፊ፤ ስለ ፓርቲያቸው አላማና ሚናዎች

አቶ ሙሴ አብርሃም፤ የአገው ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) የውጭ ግንኙነት ኃላፊ፤ ስለ ፓርቲያቸው አላማና ሚናዎችእንዲሁም ፓርቲያቸው በአገው ሕዝብ ስም አቅርቦት ስላለው የራስን ዕድል በራስ የመወሰን የክልላዊ መስተዳደር ጥያቄ ይናገራሉ።

How the Zagwe (Agaw) dynasty lost its power to the fictitious Solomonic dynasty (i.e., Amhara regime) in 1270, via a conspiracy coup orchestrated by the Orthodox church elite.

Take a listen to what Prof. Laphiso says: https://www.youtube.com/watch?v=TPCKLODQYIE

I support the question of the Agaw people for statehood in the Ethiopian federation.

Do you?


AgawMusic Gigi Shibabaw (Gole)

I support the question of the Agaw people for statehood in the Ethiopian federation.


Ethiopian Gojam Agaw new song-Tastasimbao [HD]

የአገው ህዝብ የራሱን እድል በራሱ ለመወሰንና በህገ መንግስቱ በተሰጠው መብት መሰረት “የአገው ብሄርዊ ክልላዊ መንግስት” ለማቋቋም የጠየቀውን ጥያቄ መደገፍ አለብን የሚል ሃሳብ አለኝ። እኔ በበኩሌ በደንብ ነው ምደግፈው። ይሄን የምደግፈው በመርህና በታሪክ ላይ ተመርኩዤ እንጂ ማንንም ለመጥቀም ወይም ለመጉዳት አይደለም።

የአገው ህዝብ ታላቅ ስልጣኔ የነበረውና የመንግስትነት ታሪክም ጭምር ያለው ነው (ዛጉዌ ዘመነ መንግስት የሚባለው ነው በታሪክ)። በርግጥ እዚ ደብዳቤ ላይ እንደተጻፈው የዛጉዌ መንግስት ለ300 ዓመታት ጥንታዊት አቢሲኒያን ካስተዳደረ በኋላ በዲሞክራሲያዊ መንገድ አልነበረም ለአማራው አገዛዝ (በተለምዶ የሰለሞናዊ ስርወ መንግስት ለሚባለው) በ1272/8? ስላጣኑን ያስረከበው። ፕሮፌሰር ላጶሶ ደለቤና ሌሎችም እንደጻፉት የዛጉዌ ስርወ መንግስት ተገርስሶ የአማራው ስርወ መንግስት ስልጣን ላይ የወጣው በ1272/8? በኦርቶዶክስ ቸርች በታገዘ መፈንቅለ መንግስት ነበር። የዛጉዌ መንግስት መሪ የነበረውም የተገደለ ሲሆን፣ ይሄንን ግድያ ያቀነባበረውም ቀጥሎ ወደ ስልጣን የመጣው የዩክኖ አምላክ አጎት የነበረው ፍሰሃጽዮን (በክርስትና ስሙ ተክለሃይማኖት— short: ተክልዬ) እንደበረ በታሪክ የሚታወቅ ነው። ለዝርዝሩ የላጲሶን መጽሃፍ አንብብ።

ስለሆነም፣ አሁን ላይ የዛጉዌ ስርወ መንግስት ታሪክ ወራሽ የሆነው የአጎው ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እንዲቋቋም አጎዎች ከጠየቁ ሁላችንም መደገፍ ያለብን ይመስለኛል። መደገፍ ያለብን ደግም በሌላ ማናቸውም ምክኒያት ሳይሆን ጥያቄው ከታሪክም ሆነ ከነባራዊው ሁናቴ አንጻር ፍትሃዊ ስለሆነ ነው::

#AgowStateNow #ZaguweStateNow