Waa’een dokmantarii sobaa hojjatamuuf karoorfamee afaanuma

Waa’een dokmantarii sobaa hojjatamuuf karoorfamee afaanuma Abdi Illee dhaga’aa waan inni ja’u


በነቃ ሕዝብ መሃል እየኖረ ያልነቃው ሕወሓት በፈጠረው አጀንዳ ላይ በስጋት አንረማመድ ፤ በድፍረትና በልበ ሙሉነት ትግላችንን እንቀጥል። የአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም አዲሱ የሕወሓት አጀንዳ ከወሬነት አይዘልም። የከተማ ቦታ ዝርፊያ ላይ የተሰማራው ህወሓት ከፈጠረው ችግር ውጭ የኦሮሞና የአማራ ህዝብ ሌላ ችግር የለውም። ቢኖረውም ለመፍትሄ ፍለጋ ህወሓት ጋ አይሄድም። ችግሩ ህወሓት ነው። አጀንዳውም ችግሩን በማስወገድ ላይ መሆን አለበት።

በተለያየ መንገድ ሕዝብን ለማፈን የሚያደርገው ሙከራ በተለያየ መስመር ሕዝብን ለማጋጨት የሚያደርገው ሙከራ አልሳካ ያለው ሕወሓት ከኦነግ ጋር ያረቀቀውን በኦሕዴድ ሽፋን አሻሻልኩት ያለውን ዘግቶ ያስቀመጠውን የኦሮሚያ የአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም መዝገብ አቧራውን አራግፎ ለግጭት አዘጋጅቶ ይዞ መጥቷል። ሕወሓት አሁንም ከሕዝብ በኋላ የሚጎተት ሽማግሌ ደካማ መሆኑን ዘንግቶታል። በዚህ አጀንዳ የሚፋለስ ፍቅርም ይሁን አንድነት የለም። ልዩ ጥቅም እየተባለ የሚወራለት ሕወሓትና ጀሌዎችን ከመጥቀም ውጪ ለሕዝብ ምንም ፋይዳ የለውም።

MinilikSalsawi