የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደሩን ካቢኔ እንደ አዲስ ለማዋቀር የቀረቡለትን ዕጩዎች ሹመት አጸደቀ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደሩን ካቢኔ እንደ አዲስ ለማዋቀር የቀረቡለትን ዕጩዎች ሹመት አጸደቀ
ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ያቀረቧቸውን ዕጩ ተሿሚዎች የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ተቀብሎ በ3 ተቃውሞ፣ በ7 ተድምፀ ተዓቅቦ እና በአብላጫ ድምፅ ዛሬ ከሰዓት በኋላ አጽድቋል።

በዚሁ መሠረት:-

1. ኢንጅነር እንግዳወቅ አብጤ – በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ

2. ኢንጂነር ሰናይት ዳምጠው -የቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ሓላፊ

3. ወ/ሮ ነጂባ አክመል -የፋይናንስ ቢሮ ሓላፊ

4. አቶ ሺሰማ ገብረሥላሴ -የገቢዎች ቢሮ ሓላፊ

5. አቶ አብዱልቃድር መሐመድ – የዓቃቤ ሕግ ሓላፊ

6. ወ/ሮ ኤፍራህ ዓሊ – የባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ሓላፊ

7. አቶ ኃይሉ ሉሌ-የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት አስተዳደር ቢሮ ሓላፊ

8. አቶ ዘላለም ሙላት – የትምህርት ቢሮ ሓላፊ

9. አቶ አዱኛ ደበላ -የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ሓላፊ

10. አቶ አብርሃም ታደሰ -የወጣቶች እና በጐ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሓላፊ

11. አቶ ዋቁማ አበበ- የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር

12. አቶ ታምራት ዲላ – የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር

13. አቶ ታዜር ገ/እግዚአብሔር- የኢንዱስትሪ ቢሮ ሓላፊ

14. ኢንጅነር ደመላሽ ከበደ – የኮንስትራክሽን ቢሮ ሓላፊ

15. አቶ ስጦታው ታከለ – የትራንስፖርት ቢሮ ሓላፊ

16. አቶ ነጋሽ ባጫ – የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ሓላፊ

17. አቶ ይመር ከበደ- የሥራ እድል ፈጠራ ኢንተራፕራይዝ ቢሮ ሓላፊ

18. አቶ ሙሉጌታ ተፈራ- የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሓላፊ

19. አቶ አብዱልፈታህ የሱፍ -የንግድ ቢሮ ሓላፊ

ምክር ቤቱ ውይይት ካደረገ በኋላ የካቢኔ ሹመቱን አጽድቋል፡፡

በንብረቴ ተሆነ

Via: EBC