ሌላዉ የአየርመንገዱ ጉድ:የአየር መንገዱ ሀላፊ እያስገነቡት ያለዉ ዘመናዊ የእንግዳ ማረፊያ አነጋጋሪ ሆነዋል።

ሌላዉ የአየርመንገዱ ጉድ!! የአየር መንገዱ ሀላፊ እያስገነቡት ያለዉ ዘመናዊ የእንግዳ ማረፊያ አነጋጋሪ ሆነዋል። በቦሌ ገርጅ አካባቢ እየተገነባ ያለዉ ባለ አምስት ኮኮብ የእንግዳ ማረፊያ ባለቤት እንደሆኑ የሚነገርላቸዉ አቶ ተወልደ ገ/ ማርያም የእንግዳ ማረፊያዉን ለመጎብኘት በቀን ሁለት ጊዜ ይመላለሱ እንደነበር የሚከታተሏቸዉ ሰዎች ገልፀዋል። ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ግን ግንባታዎቹ ወደሚካሄዱበት ስፍራ እምብዛም እንደ ማይመጡ ተነግሯል።የ እንግዳ ማረፊያዉ ወጭ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያሰራ ካለዉ ዘመናዊ ሆቴል እየተቆረሰ እንደተገነባ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት ምንጮች ጠቁመዋል። የበርካታ አዲስአበባ ነዋሪዎችን ትኩረት የሰባዉ ደግሞ ለብዙ ሺህ የቀበሌ ነዋሪዎች የሚሆን ትራንስፎርመር ለዚህ ህንፃ ብቻ መተከሉ ነዉ። አዲስአበባ የትራንስፎርመር እጥረትና ብልሽት በወለደዉ በከፍተኛ የሀይል እጥረት እየተመታች ባለችበት በዚህ ወቅት ለአንድ ባለሃብት የግል ትራንስፎርመር ተከላ ማካሄድ ያሳዝናል።የእንግዳ ማረፊያዎች ግንባታ አላማ ከዉጭ የሚገቡ የአየር መንገዱ ተጓዦች እና ተራንዚት የሚያደርጉ መንገደኞችን በቀጥታ ወደ ባለሃብቱ(የአየር መንገዱ ስራ አስኪያጂ አቶ ተወልደ) እንግዳ ማረፊያዉ በመመደብ ዶላር ለመሰብሰብ የታለመ እንደሆነ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚያሰራዉ ሆቴልና የአቶ ተወልደ የእንግዳ ማረፊያ የግንባታ ሂደት እኩል የተጀመረ ሲሆን ሁለቱም ፕሮጀክቶች ተጠባብቀዉ እየተካሄዱ እንደሆነ ግንባታዎቹን የሚከታተሉት አካላት መረጃ ያሳያል።

Telemt Neftegnoch Ayneberkekum