የአውስትራልያ የፓርላማ አባል ማርክ በትለር በሀገሪቱ ፓርላማ ላይ ቀርበው ሕገ-ወጡ የአብይ አህመድ ቡድን

የአውስትራልያ የፓርላማ አባል ማርክ በትለር በሀገሪቱ ፓርላማ ላይ ቀርበው ሕገ-ወጡ የአብይ አህመድ ቡድን በኢትዮጵያ እየፈፀመው ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በማስመልከት እንዲህ ሲሉ አጋለጡ፡-
 
“አብይ አህመድ ከኤርትራ አድርጌዋለሁ ለሚለው የሰላም ስምምነት የኖቤል ሽልማት ተሰጥቶታል፡፡ አሁን ከአንድ አመት በኋላ ግን ክብሩንና አሜኔታውን አጥቷል፡፡ የገባውን ቃል ሳይፈፅም ቀርቶ ዜጎቹን በማሰቃየትና በማሰር ተጠምዷል፡፡ ሀገራዊ ምርጫውን ላልተወሰነ ጊዜ አራዝሞታል፡፡…..በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያውያን አሽቸጋሪ ጊዜ በማሳለፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ አውስትራልያ የረጅም ጊዜ የኢትዮጵያ አጋር ነች፡፡ ይህንን የተረዱ እኔ በተወከልኩበት ግዛት የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆች የአውስትራልያ መንግስት በአብይ አህመድ ላይ ጫና የሚያሳርፍበት ሂደት እንዲጀመር ጠይቀውኛል፡፡ በዚህም መሰረት፡-
– ስርዓቱ በንፁሃን ዜጎች ላይ እየወሰደው ያለውን ወታደራዊ እርምጃ እንዲያቆም
– ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ
– በምዕራብ እና በደቡብ ኦሮሚያ ላይ የጣለውን ወታደራዊ ኮማንድ ፖስት ቶሎ እንዲያነሳ
– በ2020 ነፃና ተአማኒ ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጁ እንዲሆን
– ከላይ የተዘረዘሩ ቅድመ-ሁኔታዎች የማይተገበሩ ከሆነ የዓለምአቀፉ ማሕበረሰብ በስርዓቱ ላይ ማእቀብ እንዲጥል የአውስራልያ መንግስት ጫና ማድረግ አለበት፡፡” ሲሉ ሀሳባቸውን ቋጭተዋል።

1 Comment

  1. I’m proud of those Oromos who made Hon. Mark Butler a voice of Oromia in Australia. I hope Australia and DRO will establish bilateral relations and open diplomatic missions in each other’s capital (Canberra and Finfine).

Comments are closed.