የአምቦ ጉባኤና በፊንፊኔ ዙሪያ ላይ ያለው የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም ይናገራሉ ሙሉዉን ስምምነት ከቪድዮው ይከታተሉ::

የአምቦ ጉባኤና በፊንፊኔ ዙሪያ ላይ ያለው የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም ይናገራሉ ሙሉዉን ስምምነት ከቪድዮው ይከታተሉ::

የኦሮሞ ህዝብ በፊንፊኔ ጉዳይ ላይ በምንም አግባብ ከማንም ጋር አይደራደርም።

የኦሮሞ ህዝብ በፊንፊኔ ከተማ ላይ ያለውን የባለቤትነት ሙሉ መብት በህጋዊ መንገድ ያስከብርልኛል በማለት ለመንግስት ሙሉ ሀላፊነት በመስጠት በትዕግስት በመጠባበቅላይ መሆኑ
ይታወቃል።

ፊንፊኔን እና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ የኦሮሞ ህዝብ ከገዢው
መደብ ጋር ዕልህ አስጨራሽ እና ወቅቱ የሚጠይቀውን ትግል በማድረግ በርካታ ምዕራፎችን ማለፉም ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ዛሬ በህግም ይሁን በታሪክ አጋጣሚ የፊንፊኔ ጉዳይ የማይመለከታቸው አካላት እንደትላንቱ ታሪክን በማዛባትና እንደቀማኛ አጼዎች ሌላ አሳፋሪ ታሪክ በመድገም የሌላውን መብትና ጥቅም የራስ ለማድረግ መሯሯጥና መላላጥ የትም የማያደርስ ከንቱ ልፋት መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል።

የኦሮሞ ህዝብ ካሉት መልካም እሴቶችና ቱርፋቶች የተነሳ ሁሉን በትዕግስትና በህግ አግባብ እልባት እንዲያገኝ ለማድረግ የሚያድርገው ጉዞ እንደተጠበቀ ሆኖ ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ግን አሁን በፊንፊኔ ጉዳይ እየታየ ያለው ጋጋታና ሩጫን ለማስቆም እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁላ ማናቸውንም መስዕዋትነት በመክፈል የራሱን መብትና ጥቅም ለማስከበር ይገደዳል።

ኦሮሚያ በፊንፊኔ ጉዳይ ላይ ልዩ ጥቅም የሚባል ሳይሆን ተፈጥሮአዊና ታሪካዊ የሀገር ባለቤትነት መብት መከበር ጥያቄ ነው።

By Abdisa Kabeto


Ethiopia: ሰበር መረጃ – ዶ/ር አምባቸው መሞታቸው ተረጋገጠ | አዴፓ “ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ጽጌ ታሰሩ” አለ | ተጨማሪ መረጃዎች

ነፍስ ይማር