“የአሜሪካ የብሔራዊ የደሕንነት ክፍል በኢትዮጵያ ውስጥ 3 ድብቅ የስለላ …

“የአሜሪካ የብሔራዊ የደሕንነት ክፍል በኢትዮጵያ ውስጥ 3 ድብቅ የስለላ ማዕከላትን ከአገዛዙ ጋር በመተባበር እንደገነባ ተጋለጠ”።
“Jiddagalli Basaasa Ameerikaa mootummaa Wayyaanee waliin walii galuudhaan Itoopiyaa keessa tti Wiirtuu Waajira Basaa dhoksaa ta’an bakka sadii tti ijaaree jira” jedha odeeffannoon arganne.

በእቅድ እየታረደ ያለ ህዝብ
ላለፉት 25 አመታት ሥልጣን ላይ የቆዬው ህወኃት ከበታችነትና ከቡድነኝነት ስሜት ተነስቶ አንድን ህዝብ እንደ ህዝብ የሚጠላ፣ የሚጠላውን ህዝብም ለመበቀል ተግቶ የሚሠራ የክፉዎች ስብስብ ነው የምንለው ማኒፌስቶው ላይ የጻፈውን፣ ወይም የድርጅቱ መስራች የነበሩት እነ ገብረመድህን አርአያ የነገሩንን ፣ ወይም ከመለስና ከስብሀት ጀምሮ የተለያዩ የድርጅቱ መሪዎች በህዝብ ላይ በተደጋጋሚ የሰነዘሩትን ዘለፋና ስድብ ወይም፣በጉራፈርዳና በሌሎች አካባቢዎች የተፈጸመውን እና አሁንም በኮንሶ እየተፈጸመ ያለውን ወንጀል በማዬት ብቻ አይደለም።
በእውነት እላችኋለሁኝ፦ የወቅቱ የሱማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ከጥቂት አመታት በፊት የጎሳ መሪዎችን ሰብስበው በአንድ ብሄር ላይ ጥላቻ የተሞላበት ቅስቀሳ ሲያደርጉ የሚያሳዬው ቪዲዮ በኢሳት ይፋ ሲሆን ቢያንስ ለማስመሰል እንኳ እርምጃ ይወሰድባቸዋል ብዬ ጠብቄ ነበር። ይሁንና እንኳን እርምጃ ሊወሰድባቸው በህወኃት ሰዎች ይበልጥ ፍቅርና አክብሮት ተቸራቸው።
በክልሉ ከተሾሙት ፕሬዚዳንቶች ሁሉ- አማራን ክፉኛ እንደሚጠሉትና ጥላቻቸውንም በሆዳቸው መያዝ አቅቷቸው በአደባባይ እንዳወጡት እንደ አቶ አብዲ በህወኃት መሪዎች የተወደደና ለረዥም ጊዜ ሥልጣን ላይ የቆዬ የለም። ”አማራን መጥላት” የሚለውን የአለቆቻቸውን ቀዳሚ መስፈርት አሟልተዋላ። አቶ አብዲ ይህን ጥላቻ የተመላበት ብቻ ሳይሆን ከአንድ የክልል ርዕሰ መስተዳድር ቀርቶ ነፍስ ካወቀ ልጅ የማይጠበቅ መርዝ ንግግር ያደረጉት፤ ህወኃቶች በሚነግዱበት በትግራይ ብሄር ላይ ቢኾን ኖሮ ምን ይከተል እንደበር አስቡት።
እናም… ጠባቡና ከጥጋበኛ የመንደር ጎረምሳ አተያይ አርቆ የማያስበው ህወኃት ለዚች ታሪካዊና ሰፊ ሀገር አይመጥንም የምንለው ከጥላቻ ወይም እንዲሁ ከባዶ ሜዳ ተነስተን አይደለም። የኛን ስፋትና ብዝሀነት ማስተናገድ የሚችል ሰፊ ልብና አዕምሮ ስለሌለው ነው። ከእንግዲህ በኋላ እንዲህ ያለ ጠባብና አደገኛ ኃይል የዚችን ታላቅ ሀገር መሪ ለጥቂት ጊዜ እንኳ ይዞ እንዲቆይ መፍቀድ ፤ሀገርንም ራስንም ገደል ውስጥ መክተት ነው።
እስኪ በህወኃት መሪዎች እቅፍ ልዩ እንክብካቤ እየተሰጣቸው ያሉትን አቶ አብዲን ስሟቸው፦