የአማራ ግዛት አስፋፊዎች “ቤኒሻንጉል ጉሙዝን የመውረር” እቅድ..

የአማራ ግዛት አስፋፊዎች “ቤኒሻንጉል ጉሙዝን የመውረር” እቅድ ከወዲሁ በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ አመራር ውግዘት ገጠመው:: ከሁለቱ የትኛውን “ጁንታ” እንበል እንግድህ?

ተንቀሳቃሽ ሣጥናኤል አይቶ የማያቅ ካለ ጠ/ሚ ተብዬው ነብሰ ገዳይ ይኸውሎ!!!!


 

ከወለጋና ከቤኒሻንጉል የዘር ፍጅት ጀርባ ላለፉት 3 ዓመታት ኦሮሚያ ውስጥ ለተከናወነው የዘር ማፅዳት ዘመቻ በዋነኝነት ተጠያቂዎቹ “ህወሓትና ሸኔ/ኦነግ” ናቸው የሚለውን የመንግስት ፕሮፓጋንዳ ባይዋጥልንም ለሀገር ቅድሚያ በመስጠት መታገስ በማይገባን ጉዳይ ላይ ታግሰን ቆይተናል። ምክኒያቱም ዘር ማፅዳትና ተራ የፖለቲካ ችግርን ለመለየት የምንቸገር አይደለንምና። ይሄው ዛሬ የግፍ ፅዋው ሞልቶ በመፍሰሱ የዘር ማፅዳቱ ስጋ ለብሶ ለማንም ግልፅ ሆኖ ተከስቷል። መንግስትም ማስተባበል ከማይችለው አውነታ ጋር ተፋጧል። የዚህ ችግር ዋና ምክኒያት የስግብግቡ ኦነጋዊ መንፈስ ሲሆን ለጉዳዩ ገሃድ መውጣት ደግሞ የህወሓት በአጭር ጊዜ ከመድረኩ ገለል ማለቱ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርጓል።

በህወሓት እያሳበብኩ ዓላማዬን አሳካለሁ ብሎ ዕቅድ ነድፎ ሲንቀሳቀስ የነበረው የነአብይ መንግስት ኦነጋዊ ጉዞ ህወሓት ራሱ ተንቀልቅሎ በለኮሰው ጦርነት በፍጥነት በመበላቱ የነአብይን ድብቅ ጉዞ ሳያስቡት እርቃኑን ሜዳ ላይ አስጥቶታል። እስከዛሬ የአብይን መንግስት በሂሳዊ ድጋፍ አብረነው የዘለቅነው ከስህተቱ ይማራል ብለን እንጅ ከነግሳግሱ የተሸከመው የኦነግ የነተበና የከረፋ አጀንዳ እየተንጠባጠበ ሀገር ሲያግማማ አፍንጫችንን ሳይሰነፍጠን ቀርቶ አልነበረም። ህወሓትን “ከመኪና አስወርደን ዋሻ ውስጥ ቀብረናታል” ተበሎ “ሸጎዬ” በተጨፈረ ማግስት የተፈፀመን የንፁኃን ጥቃት ቢመረውም መንግስት ይህን መራራ ክኒን ራሱ ውጦ ከመፈወስ ውጭ ወደማንም ሊወረውረው አይችልም። ብቸኛው መዳኛውም ነው። አሁን በወለጋና በቤኒሻንጉል ጉምዝ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማፅዳት በህወሓት ማሳበብ ፈፅሞ አይቻልም። የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳና የቤኒሻንጉል ክልል ፕሬዚዳንት አሻድሊ ሀሰን በጋራ ኃላፊነቱን ይወስዳሉ። እነኝህ ሶስቱም በይፋ ይቅርታ ጠይቀው ጉዳዩ ወደ ህግ ይቅረብ። ይህንን ማድረግ ከተቻለ ብቻ ስለሀገር ልናወራ እንችላለን። የዕለቱ መልዕክት ነው!

Via: Dan Dimension???????????????????