የአማራና የቅማንት ህዝቦች ተቀላቅለው በሚኖሩባቸው ቀበሌዎች ህዝበ ውሳኔ እየተካሄደ ነው

የአማራና የቅማንት ህዝቦች ተቀላቅለው በሚኖሩባቸው ቀበሌዎች ህዝበ ውሳኔ እየተካሄደ ነው

የቅማንት ህዝቦች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራና የቅማንት ህዝቦች ተቀላቅለው በሚኖሩባቸው ቀበሌዎች ህዝበ ውሳኔ ድምፅ እየተሰጠ ነው።

ህዝበ ውሳኔው እየተካሄደ ያለው በአራት ወረዳዎች በሚገኙ ስምንት ቀበሌዎችና 24 ምርጫ ጣቢያዎች።

የህዝበ ውሳኔው ድምፅ አሰጣጥ ዛሬ ከማለዳው 12፡00 ሠዓት ላይ ተጀምሯል።

ህዝበ ውሳኔውን ፍትሃዊ ለማድረግ ከደቡብ፣ ኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችና ከአዲስ አበባ ገለልተኛና ልምድ ያላቸው ምርጫ አስፈጻሚዎች ተመርጠው በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ህዝበ ውሳኔው የጎንደር ከተማን እንዲሁም የጭልጋ፣ የመተማና የቋራ ወረዳዎችን አስተዳደሮች የሚያካትት ነው።

ቀደም ሲል በአራቱ ወረዳዎች በሚገኙ 12 ቀበሌዎችና 34 ምርጫ ጣቢያዎች ህዝበ ውሳኔ እንዲደረግ የተወሰነ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መግባባት ተደርሶ ህዝበ ውሳኔ እየተካሄደ ያለው በስምንት ቀበሌዎችና 24 ምርጫ ጣቢያዎች ነው።

የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በጭልጋ ወረዳ የሚገኙ አራት ቀበሌዎች ላይ ተጨማሪ ውይይትና መግባባት በማስፈለጉ መመዝገብ አለመቻላቸውንና በህዝበ ውሳኔው ላይ መሳተፍ አለመቻላቸውን ነው የተናገሩት።

Source  fanabc.