የአህዮች ትግል (qabsoo harrootaa) ከወራት በፊት እንድ “የትውልድ ስንቅ

የአህዮች ትግል (qabsoo harrootaa) ከወራት በፊት እንድ “የትውልድ ስንቅ ( Galaa dhalootaa)”

የሚል መፅሃፍ በአፋን ኦሮሞ ታትሞ ገበያ ላይ ውሏል።የመፅሃፉ ደራስ ታዬ
ከወራት በፊት እንድ “የትውልድ ስንቅ ( Galaa dhalootaa)” የሚል መፅሃፍ በአፋን ኦሮሞ ታትሞ ገበያ ላይ ውሏል።የመፅሃፉ ደራስ ታዬ ደንደኣ ( Taye Dendea ) ነው።ታዬ ደንደኣ ወጣት ቢሆንም በፖለቲካ ሰበብ አዲስ አበባ ዩንቭሪሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ትምህርት ላይ እያለ ሁለት ጊዜ በፖለቲካ ሰበብ ታስሮ የተለቀቀ ነው።ታዬ በመጀመሪያ ትምህርቱን አቋርጦ ምሥራቅ ኦሮሚያ እያለ ተይዞ ለ3 ዓመት ታስሮ ተፈታ።በሁለተኛው ዙር ደግሞ እዚሁ ሸገር ትምህርቱን ጨርሶ ልመረቅ ቀናት ስቀሩት ተይዞ አሥር ዓመት ተፈርዶበት ሰባት ዓመት ከግማሽ አከባብ ታስሮ የፍርድ ጊዜውን ካጠናቀቀ በኃላ ከወራት በፊት ከእስር ቤት ተለቋል።ታዬ ከእሥር ቤት እንደወጣ አንድ የትውልድ ሥንቅ የሚል በአፋን ኦሮሞ የተፃፈ መፅሃፍ ለንባብ አብቅቷል።መፅሃፉ ብዙ አጫጭር ታሪኮችን የያዘ ነው።ከነዚህ አጫጭር ታሪኮች መካከል አንዱ የአህዮች ትግል የሚለው ዛሬ Fb ላይ Babsa Tula በአፋን ኦሮሞ ለጥፎት ስላየሁ እና ስለተመቸኝ ወደ አማሪኛ ለመተርጎም ሞክሪያለሁ።
ታሪኩ እንድህ ነው።
ብዙ አህዮች ከከተማ ራቅ ባለ እና ገደላማ በሆነ አከባቢ ይኖሩ ነበር።እነዚህ አህዮች የሰው ልጅ ከከተማ የተለያዩ እቃዎችን እየጫነባቸው ይገለገልባቸዋል።የአከባቢው ገደላማ መሆን እና ከከተማ መራቅ የአህዮቹን ህይዎት አሰቃቂ አደረገው።በዚያ ላይ የሰው ልጅ እነሱን ለጭነት ከመጠቀም ውጭ ለቀለባቸው አይጨነቅም።ከአቅማቸው በላይ ሸክም ጭኖባቸው ስደክማቸው ይነርታቸዋል።ካቃታቸውም ጭነቱን ከአንዱ ወደ ሌላ አህያ በመቀየር የደከመውን አህያ ሜዳ ላይ ትቶ ስለምሄድ የጅብ ሲሳይ ይሆናሉ።
አህዮች መረራቸው ።ከዚህ የበሰ የለም ብለው በወደል አህያ መሪነት ተሰብስበው ተወያዩ።ከሰፊ ውይይት በኃላ የትጥቅ ትግል ጀምረው ለነፃነታቸው ለመዋደቅ ወደ ጫካ አመሩ።ትግል እንደጀመሩም አልተሳካላቸውም ።አህዮች ህብረት አጡ።ድል ራቃቸው።ይባስ ብሎም በፊት በረት ውሥጥ ስያስፈራራቸው የነበረው ጅብ ሜዳ ላይ አግኝቶ አቅራራባቸው። የመጀመሪያ ሰሞን ሦሥት አህዮች በጅብ ተበሉ።በመቀጠል አምስት አህዮች በጅብ ተበሉ።ቀጥሎም አራት አህዮች በጅብ ተበሉ።አሁንም አህዮቹ ያሰቡት ስላልተሳካላቸው እና ዘራቸውም አደጋ ላይ ሥለወደቀ በእድሜ ጠና ባለ አህያ መሪነት ጉባዔ ተቀመጡ።በጉባዔውም ላይ ትግሉ እንዳልተሳካላቸው እና ቢያንስ ዘራቸውን ከጥፋት ለመታደግ ትግል በማቆም ወደ በፊቱ ኑሮዓቸው ለመመለስ ወሰኑ።የትግል መሪያቸውን ወደል አህያንም በተከተለው ሥልት ደካማነት አምርረው ወቀሱ።በውሳኔያቸው መሰረትም ከወደል አህያ በስተቀር ሌሎቹ አለቆቻቸውን ይቅርታ ጠይቀው ወደ በፊት ህይዎታቸው ተመለሱ።ወደል አህያ ግን አልመለስም ብሎ ለብቻውን በረሃ ቀረ።ትግሉንም እንደሚቀጥል እና አንድ ቀን እነሱንም ታግሎ ነፃ እንደሚያወጣቸው ዛተ ።ወደል አህያ እንዳሰበው ሳይሳካለት ቀርቶ እሱም ወዲያዉኑ በጅብ ተበላ።ወደ መደበኛ ህይዎት የተመለሱት አህዮች ግን አንድ ቀን ወደል አህያ እንደዛተው ታግሎ ነፃ ያወጣናል ብለው እየጠበቁ ነበር።በተገናኙ ቁጥርም በረሃ የቀረው ወደል አህያ ምን ላይ እንዳለ ይጠያየቃሉ።የተስፋ ቃልም ይለዋወጣሉ።
አንዱ አህያ በረሃ የቀረው ጓዳቸው ድል እያደረገ እና እየደረሰ ሳይሆን አይቀርም የሚል መላምት ይናገራል።በማስረጃነትም ትላንትና ማታ የወደል አህያ የሽንት ሽታ እንዳየ ያቅርባል። ሌላኛው ደግሞ በሌላ ቀን አሁንስ እየመጣ ነው ። ማታ በቅርብ ርቀት ድምፁን ስምቻለሁ እያለ ያፅናናቸዋል።ወደል አህያ ግን በመጀመሪያው ቀን በጅብ ስለተበላ ልመጣ አልቻለም ።ልመጣም አይችልም።አህዮቹ የማይመጣ ነገር በተስፋ እየጠበቁ እራሳቸውንም ነፃ ለማውጣት ምንም ጥረት ሳያደርጉ ህይዎታቸውን ገፉ።
መልዕክቱ ምንድነው የማይመጣ ነገር አትጠብቁ።እራሳችሁ የቻላችሁትን አድርጉ የሚል ነው ብሏል ታዬ።
የኔ መልዕክት ደግሞ መፅሃፉን ገዝታችሁ የተቀሩትን ታሪኮች አንብቡ የሚል ነው።አፋን ኦሮሞ የማትችሉት ደግሞ በአስተርጓምም ቢሆን ሞክሩት።ቆንጆ መፅሃፍ ነው።

Via: Dereje Gerefa Tullu