“የኔ ደም ለኦሮሞ ሕዝብ መብት መከበር የሚፈስ በመሆኑ፣ በከንቱ አይቀርም፤ ባልሰራሁት ስራ፣ በሀሰት ወንጅለው የሞት ፍርድ የፈረዱብኝ ሁሉ፣

“የኔ ደም ለኦሮሞ ሕዝብ መብት መከበር የሚፈስ በመሆኑ፣ በከንቱ አይቀርም፤ ባልሰራሁት ስራ፣ በሀሰት ወንጅለው የሞት ፍርድ የፈረዱብኝ ሁሉ፣ በዚህቹ ስፍራ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ፣ በቅርቡ የእጃቸውን እንደሚሰጣቸው አምናለሁ፤ በዋቃ (በእግዚአብሄር) ፍቃድ፣ በኦሮሞ ልጆች ብርታት “ጉማዬ” (የደም ካሳ) ይመለሳል፡፡ ይዋል ይደር እንጂ፣ የኦሮሞ ሕዝብ መብት፣ በልጆቹ ትግልና ጥረት መከበሩ እንደሆነ የማይቀር ነው” ማሞ መዘምር እ.ኤ.አ በ1967 የሞት ፍርደኛ ሆኖ፣ ስቅላቱ ሊፈፀም ጥቂት ጊዜ ሲቀረው፣ ወደ ገመዱ በኩራት እየተራመደ የተናገረው የመጨረሻ ቃል።

የቄሮ ስህተት…!!

ጀግናው ቄሮ የሰራው አንድ ስህተት ቢኖር እስክንድር ነጋን በትግሉ ከእስር ማስፈታቱ ነበር። እርሱ ግን ፀረ-ኦሮሞ እና ፀረ-ቄሮ አቋሙን ማሰማት ቀጥሎበታል ያጎረሰውን ጣት መንከስ ገፍቶበታል በህትመት ሚድያ ላይ ከ1985 ጀምሮ ከ 25 አመት በላይ ቆይቷል ከባለቤቱ ሰርካለም ፋሲል ጋር “ምኒልክ” እና “ጃንሆይ” የሚሉ ጋዜጦችን በማሳተም ይታወቃል እርግጥ ነው ምኒልክ እና ጃንሆይ የሚል ርዕስ ያላቸውን ጋዜጦችን ያተመ ሰው ጥገኛ ፊውዳላዊ አስተሳሰብ ያለው እንደመሆኑ ስለኦሮሞ መልካም ይፅፋል ብሎ ማሰብ ስህተት ነው። አሁን ደግሞ ህትመት በጀመረበት “ኢትዮጲስ” ጋዜጣ ፀረ ኦሮሞ ዘመቻውን ገፍቶበታል። እርግጥ መፃፍ መብቱ ነው ስለ ኦሮሞ ሲፈተፍት መስመሩን ያለፈ ሰዓት ግን ውጤቱንም ለመቀበል ዝግጁ መሆን አለበት !!!


ኦነግ ለኦሮሞ ህዝብ ምኑ ነው?
~~~~~~~~~~~~~~~~~
ኦነግን ከኦሮሞ ህዝብ ማፋታት ከንቱ ድካም ነው። የኦሮሞ ድርጅቶች ሁሉ ለህዝባቸው ነፃነት፣ አንድነት፣ ህልውና እና ክብር ያደረጉት ትግል ሲመዘን የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ነው።

* ገዥዎች “ኦሮሞ” የሚለውን ስም አጥፍተው አፀያፊ ፍቺዎች የሰጡትን ስም በግዴታ በህዝቡ ላይ ጭነው ነበር። ይህንን ሆን ተብሎ የኦሮሞ
ህዝብን ለማዋረድ የተደረገውን ሴራ ተዋግቶ ህዝቡ “ኦሮሞ” በተሰኘው ትክክለኛ ስሙ ብቻ እንዲታወቅ ያደረገው ኦነግ ነው።

* በታሪክ ሂደት ተበታትነው ወደ መረሳሳት ደረጃ ደርሰው የነበሩትን የምስራቅ፣ የምዕራብ፣ የሰሜንና የደቡብ ኦሮሞዎችን ሙሉእ በሆነ ሁኔታ አንድ ላይ ያሰባሰበው ድርጅት ኦነግ ነው።
አሁን ያለው የኦሮሞ ህዝብ አንድነት የኦነግ የስራ ውጤት ነው።

* የኦሮሞ ህዝብ በባህሉ፣ በቋንቋው በትውፊቱና በታሪኩ ሳያፍር ማንነቱን እንዲገልጽና ኦሮሞነቱን በየትኛውም መስክ እንዲያሳውቅ ከማንም በላይ የጣረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ኦነግ ነው።

* ኦነግ የኦሮሞ ብሄርተኝነት አባት ነው። Orommumaa እና Sabboonummaa የሚባሉትን ጽንሰ ሐሳቦች በመቅረጽ የኦሮሞ ብሄርተኝነትን ያበለፀገው ኦነግ ነው። ከሰላሳ ዓመታት በፊት ኢብሳ፣ ቶላ፣ መገርሳ በሚሉ ስሞች ልጆቹን መጥራቱን አቁሞ የነበረው ሙስሊሙም ሆነ ክርስቲያኑ ኦሮሞ ዛሬ ኮራ ብሎ “ሃዊ፣ ቀነኒ፣ ፊራኦል፣ ኦብሰን፣ ሳርቱ” የሚሉ ስሞችን ለልጆቹ እየሰጠ ያለው ኦነግ በቀየሰው መንገድ inspire ስለሆነ ነው።

* ኦነግ “የቁቤ አፋን ኦሮሞ” አባት ነው። አፋን ኦሮሞ በላቲን ፊደል እንዲጻፍ ምርምር አርገው ውጤቱን ይፋ ያደረጉት ሼኽ ሙሐመድ ረሻድ እና ኃይሌ ፊዳ ናቸው። እነርሱ ያጠናቀሯቸውን ጥናቶች በማዳበር ለመጀመሪያ ጊዜ በስራ ላይ ያዋለው ግን ኦነግ ነው።

* ኦነግ በሽግግሩ ዘመን ከሰራቸው ስራዎች መካከል ትልቁ አፋን ኦሮሞ የትምህርት ቋንቋ ሆኖ የኦሮሞ ልጆች በቋንቋቸው እንዲማሩ ማድረጉ ነው። በዚህ ረገድ የትምህርት ሚኒስትር የነበሩት አቶ ኢብሳ ጉተማ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።

*ኦነግ የዘመናዊው የአፋን ኦሮሞ ስነ ጽሑፍ አባትም ነው። በቁቤ አፋን ኦሮሞ የተጻፉ
የግጥም እና የልብ ወለድ መጻሕፍትን ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳተመው ኦነግ ነው።
በቁቤ የሚዘጋጁ ጋዜጦችና መጽሔቶችንም ለመጀመሪያ ጊዜያሳተመው ኦነግ ነው።

*አሁን የስራ ቋንቋ ሆኖ የሚያገለግለውን የተማከለ የአፋንኦሮሞ ዘይቤንም የፈጠረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ነው።ለቢሮክራሲ ስራ የሚያስፈልጉና በሂደት ለመጥፋት ተቃርበው
የነበሩ የኦሮምኛ ቃላትን ከልዩ ልዩ የኦሮሚያ ዞኖች አሰባስቦበመዝገበ ቃላት በመሰነድ በመላው ዓለም በሚኖሩ ኦሮሞዎች
ዘንድ እንዲታወቁ ያደረገው ኦነግ ነው።

*ኦነግ የዘመናዊው የኦሮሞ የታሪክ ጽሑፍ አባትም ነው።ለመጀመሪያ ጊዜ በመላው የኦሮሚያ ዞኖች ላይ ያተኮረ የታሪክ
መጽሐፍ አሳትሞ ያቀረበው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ነው (ከዚያ በፊት ይወጡ የነበሩት የታሪክ መጻሕፍት በአንዱ የኦሮሚያ ዞን፣
ወይንም በአንድ የኦሮሞ ነገድ ላይ ብቻ ያተኮሩ ነበሩ)።

*ለመጀመሪያ ጊዜ የገዳ ስርዓትን አተገባበር በተሟላ ሁኔታ የሚተርክ መጽሐፍ የጻፉት ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ናቸው።የገዳ ስርዓትን በዓለም ዙሪያ በስፋት ያስተዋወቁት ግን በውጭ ሀገራት የነበሩት የኦነግ የውጭ ግንኙነት ቢሮዎች ናቸው።

*ኦነግ ሁሉን አቀፍ የኦሮሞ ጥናት አባትም ነው። በኦሮሞ ህዝብ ባህል፣ ታሪክ፣ ኢኮኖሚ፣ ቋንቋና የነፃነት ትግል ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሑፎች የሚቀርቡበትን ዓለም አቀፍ ኮንፈረስ
ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀው የኦነግ የውጭ ግንኙነት ቢሮ ነው። በዛሬው ዘመን በዚህ ዘርፍ ተጠቃሽ ሆኖ የወጣው የኦሮሞ ጥናት ማህበር (Oromo Studies Association)የተመሠረተው ኦነግ ሲያዘጋጃቸው በነበሩት ኮንፈረንሶች ላይ ሲገናኙ በነበሩት ምሁራን አማካኝነት ነው።
—–
ኦነግ በነፃነት ትግሉ ዘርፍ ያደረገው አስተዋጽኦ ሲገመገም ደግሞ ከላይ ከሰፈረው በእጅጉ ይበልጣል። ስለዚህ ወደ ዝርዝሩ መግባቱ ለጊዜው አያስፈልገንም። በአጭሩ “ኦሮሞዎች በነገድ፣ በጎሳ፣ በክፍለ ሀገርና በሃይማኖት ሳይለያዩ በኦሮሙማ መንፈስ አንድ ላይ ሆነው በተደራጀ ሁኔታ እንዲኖር ያደረገው የኦሮሞ ህዝብ መንፈስ ኦነግ ነው።


ከብሔር እና ከሀገር የቱ እንደሚቀድም ግራ የገባቸው ሰዎች መልሰው ግራ ያጋቡኛል። ለማስረዳት ያህል ራሴን በምሳሌ ብውሰድ እኔ ሀዊሻ ቤተሰቦች አሉኝ እነዚህ ቤተሰቦቼ በደም የተሳሰርን ነን።መርጬያቸው አልተወለድኩም ግን ከልቤ እወዳቸዋለሁ፣ድጋሚ መወለድ ቢኖር ከእነርሱ ነው መወለድ የምፈልገው። በሌላ በኩል እኔ ሀዊሻ የምኖርበት ወረዳ አለ ይህ ወረዳ የተለያዩ ቤተሰቦች ምንም አይነት የደም ትስስር የሌለን፣ በጋራ የምንኖርበት፣ አስፈላጊ ከሆነ መቀየር የምንችለው፣ አስተዳዳሪዎች ያሰመሩልን የአብሮነት ግዛት ነው። ከላይ ባለው ምሳሌ በመነሳት ብሔር በቤተሰብ፣ ሀገር ደግሞ በሰፈር ይመሰላሉ።
ታዲያ እንዴት ሆኖ ነው ሰፈር ከቤተሰብ፣ ሀገር ደግሞ ከብሔር የሚቀድመው? ወገኖቼ አይምታባችሁ!! ቤተሰቤን ከሰፈሬ፣ ብሔሬን ከ ሀገሬ፣ ሰፈሬን ከሌላ ሰፈር፣ ሀገሬን ደግሞ ከሌላ ሀገር ብቻ ነው ላስበልጥ የምችለው።