የነፍጠኞችና የኢትዮጵያ የከተማ ፖለቲከኞች (የዘረኞች) ድድብና (የአሥመራና የፊንፊኔ የአጥር ለአጥር የውሽማ ፖለቲካ)

የነፍጠኞችና የኢትዮጵያ የከተማ ፖለቲከኞች (የዘረኞች) ድድብና (የአሥመራና የፊንፊኔ የአጥር ለአጥር የውሽማ ፖለቲካ)
 
ተስፋፊና የመሬት ናፋቂ አቢሲኒያዊ ደናቁርት፦ “ዐድዋ የኢትዮጵያ ነው ግን ወልቃይት የአማራ ነው፣ ወለጋ የኢትዮጵያ ነው ግን ወሎ የአማራ ነው፣ ጂንካ የኢትዮጵያ ነው ግን ሁመራ የአማራ ነው፣ አክሱም የኢትዮጵያ ነው ግን ጎንደር የአማራ ነው፣ ጂግጂጋ የኢትዮጵያ ነው ግን ራያ የአማራ ነው፣ ውቁሮ የኢትዮጵያ ነው ግን ዳንሻ የአማራ ነው፣ አርባምንጭ የኢትዮጵያ ነው ግን ደባርቅ የአማራ ነው፣ ወዘተ” ይሉሃል። ብቻ “እኛም የእኛ ብቻ፥ ኢትዮጵያም የእኛ ብቻ፤ እኔም የእኔ ብቻ፥ አንተ የጋራ” ይሉሃል። ከዚህ በላይ ድንቁርና ከየት ይምጣ? ይህ እጅግ በጣም መሠረታዊ አመለካከት (elementarily thinking) ነው። ይህ ከማህበራዊ ውልና ከግብርናው አብዮት በፊት የነበረ እጅግ ንጣፋዊ ዝቃጭነት ነው። አቢሲኒያውያን ይህ ዛሬም አልለቀቃቸውም። ይህ የማዕከላዊነትና የገድሎ መውረስ ጠኔ ነው።
 
በጣም የሚያስስቀውና የሚያስታዝበው ደግሞ እዚያ ካምፕ ያሉ ደናቁርት “የኢትዮጵያ አንድነት ኃይሎች፣ የኢትዮጵያ ጠበቆችና መቼም በኢትዮጵያዊነት የማይደራደሩ ናቸው” መባላቸው ነው። እውነቱ ግን ኢትዮጵያ በታሪኳ የፈረሰችው በእነዚህ የዘቀጡ ዘረኛ ጭንቅላቶች እብሪት ነው። አገርንና የአገሩን ዜጋ በፉከራ/ቀረርቶና ግዘታ፣ በወረራና ግድያ፣ በመውረስና በመማረክ፣ በአፈናና ጭቆና ለረጅም ጊዜ መግዛት ይቻል እንደሁ እንጂ ለዘላለም መግዛት አይቻልም። በዓለም ዙሪያም ሆነ በኢትዮጵያ አብዮቶችም ያየነውና ያረጋገጥነው ይህንኑ ነው፥ ጥቂት ገዥዎች ሰፊውን ሕዝብ ለዘላለም መጨቆን አይችሉም። ትንንሾቹ EPLF እና TPLF ግዙፉን የኢትዮጵያ መንግሥት ያሸነፉት በዓላማና ትክክለኛ ምክንያት ነበር እንጂ በመንጋ ብዛት አልነበረም።
“መሬት የኢትዮጵያ ነው እንጂ የብሔር አይደለም” ብለው ሲያደነቁሩን ይከርሙና፥ ወደ አማራ አካባቢ ሲሆን ምድሩና ሰማዩ የአማራ ብሔር ይሆንባቸዋል። “መታወቂያ ካርድ ላይ የብሔር ስም አይጻፍ” ሲሉ ይከርሙና ወልቃይት፣ ፀገዴ፣ ዳንሻ፣ ሁመራ የአማራ መታወቂያ ያድላሉ። እውነት ብሎ ነገር አያውቁም። ውሸታም ቀጣፊዎች ብቻ ናቸው። በደቦ ያስባሉ። እነሱ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብሮነትና የግዛት አንድነቷ በተጨባጭ ፀር ናቸው። የእነሱ ተስፋፊና ወራሪ ባህርይ የሕዝቦችን አብሮነት አያጠናክርም። ዐለቃ የሆነ ማንም ለእነሱ ልክ ነው። አገራቸውና ሃይማኖታቸውም ከጥንት ጀምሮ ‘Patrimonial, Patriarchal, Highly centralized, Critique and interrogation are highly prohibited, even in a family, etc. ነበር/ነውም። የኢትዮጵያ ሌሎች ሕዝቦች (e.g: የኩሽና የኡማቶ) መንግሥታቸውም ሆነ ሃይማኖታቸው በተነጻጻሪ ግንኙነታቸው ያልተማከለና ለሕዝቡ ተነጻጻሪ ነጻነት ያለው፣ fairly egalitarian, democratic, etc. ነበር።
 
እነዚህ አቢሲኒያውያን ራሳቸውንና የራሳቸው የሆነን ባህል (ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ታሪክ፣ ትምህርት፣ ኪነጥበብ፣ ሙዚቃ፣ ወዘተ) ልከ-ነገር አድርገው የማቅረብ አድሏዊ ምቹ ሁኔታ ስለተፈጠረላቸው ቤተክህነታቸውና ቤተመንግሥታቸው የረከሰ ጋብቻ በመፍጠር ኢትዮጵያ በሙሉ አንድ ዓይነት እብደት እንድታብድ አስገድደዋል። ከዚህም በመነሳት ነው የራሳቸውን ማንነትና ነገር “ኢትዮጵያዊ ማንነት፣ የኢትዮጵያ ብሔርተኝነት፣ የኢትዮጵያ ባህል፣ የኢትዮጵያ ይህ፣ የኢትዮጵያ ያ፣ ወዘተ” የሚሉ የውሸት ግንቦችን ደርድረው ለዘመናት ደንቁረው ያደነቆሩን። እነዚህ ሰዎች ዘረኞች ናቸው፥ የንግግራቸው ማዕከል የማን ማንነት እንደ ሆነ እናውቃለን። አንድ ቋንቋ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ዓይነትነት ለዘመናት ከማስፋፋትና ሌላውን ሕዝብ ከዋናው መስመርና መድረክ ከማጥፋትና ከማራቅ በላይ ዘረኝነት ካለ እኔ ልወቀው።
 
የነፍጠኛው ምልምል ገልቱዎች (imperial converts) ግን ከየቦታው ተመልምለው ዛሬም በበሉበት ሁሉ ይጮኻሉ። ባለቤት ያለውና ውሻ እንኳን በበላበት ሁሉ አይጮኽም፥ ጌታው ግቢ ደርሶ እንጂ። ይህ የኢትዮጵያውያን የዘረኝነት መርዝ ሰሜኑን ይዞ (ትግራይ ስትቀር) የኢትዮጵያ ከተሞችን እያሰሰ የሚገኝ ክፉ በሽታ ነው። ቶሎ ተቆርጦ ካልተጣለ ወደ ካንሰርነት ይዞርና አገር ያጠፋል። በዚህ ለኢትዮጵያ እንደ አገር አስጨናቂ በሆነ ወቅት ላይ ባዕዳን እንኳን “ተነጋገሩ፣ አትተላለቁ፣ ቁጭ በሉ፣ ተኩስ አቁሙ፣ ወዘተ” ሲሉ እነዚህ ነፍጠኞችና ጥሩምባ ነፊ ልውጥ ከተመኞቹ “ጦርነት ብቻ” ይላሉ። ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሠሩ “ለኢትዮጵያ ቆሜያለሁ” ይላሉ። ርጉማን ናቸው።
👉🏿 ኢሳይያስና ዐቢይ ከወዲህ ማዶና ከወዲያ ማዶ (የትግራይን ምድር ትተው ተቃቅፈው ) በሠላምና በጤና ግን አይለያዩም፥ ይጠፋፋሉ እንጂ!!!!
@በዓይናለም ታደሰ