ጥቅምት 18-2011 ዓ.ም: አደጋ የደረሰበት የነዳጅ ቦቲ ህገ ወጥ መሳሪያ ተገኘበት።

ጥቅምት 18/2011 ዓ.ም: አደጋ የደረሰበት የነዳጅ ቦቲ ህገ ወጥ መሳሪያ ተገኘበት።
ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዝ የነበረው የነዳጅ ቦቲ በገንዳውሀ ከተማ አስተዳደር በተለምዶ ኢንዱስትሪ መንደር በሚባል አካባቢ በትናትናው ዕለት ጥቅምት 17/2011 ዓ.ም ፍየል አድናለሁ በሚል ምክኒያት በመገልበጡ አደጋ ደርሷል። በዛሬው ዕለት ጥቅምት 18/2011 ዓ.ም የከተማ አስተዳደሩና የወረዳው የጸጥታ ሀይሎች ባደረጉት ፍተሻ መሰረት 97 ክላሽን ኮፍ 1291 የቱርክ ሽጉጥ እና 3 ብሬን መገኘቱን ከስፍራው ለመዘገብ ተችሏል።