የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ እና ሌሎች ጓደኞቹ በመኪና ሲንቀሳቀሱ በፀጥታ ኃይሎች ተተኩሶ 2ቱ መሞታቸውን ቤተሰቦቻቸው፣ ጓደኞቻቸው ፣የስራ ባልደረቦቻቸው ተናግረዋል።

የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ እና ሌሎች ጓደኞቹ በመኪና ሲንቀሳቀሱ በፀጥታ ኃይሎች ተተኩሶ 2ቱ መሞታቸውን ቤተሰቦቻቸው፣ ጓደኞቻቸው ፣የስራ ባልደረቦቻቸው ተናግረዋል።
 
ከሞቱት 2ቱ በተጨማሪ ሁለቱ ታስረዋል። ሁለቱ ሟቾች እና በመኪና ውስጥ የነበሩት ሌሎች ሰዎችን የጫነችው መኪና ከአንደኛው ሟች ቤት በቅርብ ርቀት በጥይት ተመታ ከዛፍ ጋር ተጋጭታ ቆማለች።
ቦታው ኣደሃውሲ አካባቢ ፤ ከትራፊክ መብራቱ ከፍ ብሎ ነው።
 
ጋዜጠኛ ዳዊት ቅዳሜ ዕለት ለሰዓታት ታስሮ ቆይቶ ተለቋል፤ ሰኞ ዕለትም እንዲመለስ ተናግሮት ሲመላለስ ነበር ብለዋል ቤተሰቦቹ።
ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከ1990ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ በኢቲቪ ለበርካታ አመታት ሰርቷል ፣ በትግራይ ክልል የግል መፅሄት መስራችም እንዱሁም ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሰርቷል፤ በመቀጠልም በትግራይ ቴሌቪዥን በአማርኛ ክፍል ሲሰራ ነበር።
ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ የ45 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት ነበር።
ነፍስ ይማር!!


አንጋፋው ጋዜጠኛ ጌታቸው ደስታ አረፈ
 
በኢትዮጵያ ራዲዮና በቀድሞው የጀርመን ድምፅ በአሁኑ ዶቼ ቬለ ለረዥም ዓመታት ያገለገለው አንጋፋው ጋዜጠኛ ጌታቸው ደስታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ጋዜጠኛ ጌታቸው ደስታ ባደረበት ህመም ምክንያት በሀገር ውስጥና በጀርመን ሀገርም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በተወለደ በ86 ዓመቱ ለረጅም ዓመታት በኖረባትና በሙያው በሠራባት ጀርመን ሀገር ፍራንክፈርት ከተማ ነው ሕይወቱ ያለፈው። ጌታቸው ደስታ ከቀደምት የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች አንዱ ሲሆን በተለይ በዘርፉ ፈር ቀዳጅ ከሚባሉትና እጅግ ዝናን ካተረፉ ጋዜጠኞች አንዱ ነበር። አንጋፋው ጋዜጠኛ ጌታቸው ደስታ ባሕላዊ ትምህርቱን ለድቁና በሚያበቃው ደረጃ ተምሯል: ዘመናዊ ትምሕርቱንም በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት እና በባሕር ዳር ፖሊቴክኒክ ትምሕርት ቤት ተከታትሏል፡፡ ከዚይም ተመርቆ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በኢትዮጵያ ሬዲዮ በወጣው ማስታወቂያ ተወዳድሮ በመቀጠር ለረጂም ዓመታት አገልግሏል፡፡ እዚያ በሥራ ላይ እያለ የተባበሩት መንግሥታት ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ተወዳድሮ፤ አብላጫ ውጤት በማግኘት ኒውዮርክ በሚገኘው የመንግሥታቱ ሬዲዮ ጣቢያ ላይ በትጋት ሠርቶ ኮንትራቱ በማለቁ ተመልሶ ወደ ነበረበት የኢትዮጵያ ሬዲዮ መጥቶ በማገልገል ላይ እንዳለ፤ እንደገና ወደ ጀርመን በመሄድ በቀድሞ አጠራሩ የጀርመን ድምፅ በአሁኑ ዶቼ ቬሌ ሬድዮ ለዓመታት ሲሠራ ቆይቶ በራሱ ጥያቄ የጡረታ መብቱ ተጠብቆለት ወደ ሀገሩ ተመልሷል።
 
ተወዳጁ ጋዜጠኛ ጌታቸው፤ ከአብራኩ የተገኙ ሁለት ልጆች ሲኖሩት፤ ከእነሱ ሌላ እንደልጆቹ ያሳደጋቸውና በስስት አባታችን እያሉ እሱም ልጆቼ የሚላቸው በሕመሙ ሳይለዩት በሀገር ውስጥና ጀርመንም ከሄደ አንስቶ ካጠገቡ ያልተለዩ አምስት ልጆችም አሉት። ቤተሰብ ወዳጆቹ በህመሙ ወቅትና ወደ ውጭም ለህክምና በሄደበት ጊዜ በአካልም በስልክም በኢሜይልም ጥየቃችሁ ላልተለያቸው ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ ብለዋል::
ከእናቱ ከወ/ሮ በላይነሽ ሀብተ ማርያምና ከአባቱ ከግራአዝማች ደስታ አርአያ አዲስ አበባ ፈረንሳይ ኤምባሲ አካባቢ የተወለደው የታዋቂው ጋዜጠኛ ጌታቸው ደስታ አስከሬኑ በዛሬው ዕለት ከጀርመን ወደ ሀገሩ የገባ ሲሆን የቀብር ስነ ስርአቱም ነገ ዓርብ ጥር 14ቀን 2013 ዓም ከቀኑ በ9.00 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሤ ካቴድራል እንደሚፈጸም ቤተሰቦቹ ገልጸዋል። ከቀብሩ ሥርአት በሁዋላ በቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ባለው አዳራሽ የተዘጋጀውን ጠበል ጠዲቅ በመቅመስም ስንብቱ በዚያው እንደሚሆን ቤተሰቦቹ ገልጸዋል። ሠልስትም አይኖርም:: ዶቼ ቬለ በአንጋፋው ባልደረባው ሕልፈት የተሰማውን ሀዘን በመግለጽ ለወዳጅ ዘመዶቹና ቤተሰቦቹ መጽናናትን ይመኛል።

1 Comment

  1. Congratulations to all enemies of Tigray people who pass hate speech in an attempt to ignite genocide and starvation . To my personal knowledge this hate speech started earlier before the noble prize winner came to power by the warmonger media outlets like ESAT, Zehabesha and borkena .

    EAST staff boldly told to their fans and amhara people to create man-made starvation and economic hardship on Tigray in their TV program .

    Sooner or later , they and their fans will not evade the consequences of their crime and act of precipitating war and warcrime on Tigray including those socalled church men , mahibrekidusan who are silently watching those crimes .

    Last but not least, they hatespeech was propagated by Eritrean refugees who live in and outside ethiopia. Once again , men and women who were happy to see the downfall TPLF, and tigray congratulation for your success .

Comments are closed.